Get Mystery Box with random crypto!

ይናገራል። በአጠቃላይ በዚህ መጽሐፍ የምሥራቁ ኦርቶዶክሳዊ ነገረ መለኮት ምን መልክ እንዳለው፥ በእ | ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA

ይናገራል።
በአጠቃላይ በዚህ መጽሐፍ የምሥራቁ ኦርቶዶክሳዊ ነገረ መለኮት ምን መልክ እንዳለው፥ በእግዚአብሔር መገለጥ ላይ የተመሠረቱት ምንጮቹንና የምንጮቹ ነገረ መለኮታዊ አረዳድ፥ ሰው ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ መሠረት ያደረገውና በነገረ መለኮት ሰፊ ሽፋን የሚሰጠውን ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሰብእን በማስረዳትና በመተንተን የሰው ልጆች ክብራቸውን አውቀው እግዚአብሔርን ወደ መምሰል(Theosis) የክርስትና ጉዞ እንዲያቀኑ የሚያደርግ ነው። እንዲሁም እግዚአብሔርን በመምሰል ሂደት ውስጥ የምናገኛቸውን ሰው እና ሌሎች ፍጥረታትን እንዴት ባለ አኳኋን መመልከት እንዳለብን ባጠቃላይ ከእግዚአብሔር እና የእርሱ ከሆኑት ፍጥረታት ጋር ምሥጢራዊ እና መንፈሳዊ ኅብረታዊ ግንኙነት እንዲኖረን የሚያግዝ የሚያስረዳ እና የሚራዳ መጽሐፍ ነው።
ለመምህራችን እግዚአብሔር ይስጥልን። ከእጅ ቁርጥማት ከደረት ውጋት ይሰውርዎት! ወርቃማ ብዕርዎት ትለምልም! ለመጽሐፍ ቀጠሮ ያብቃን!!!

መጽሐፉን ያንብቡ ያስነብቡ!!

እውነተኛ የነገረ መለኮት መግቢያ በሩ ይሄ ነው!