Get Mystery Box with random crypto!

@Book for all

የቴሌግራም ቻናል አርማ bookfor — @Book for all B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bookfor — @Book for all
የሰርጥ አድራሻ: @bookfor
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.53K
የሰርጥ መግለጫ

ማንበብ ማንበብ ማንበብ ‹‹ሰፊ ይለበሳል ጠባብ ይቀደዳል››
@መባ
ለማንኛውም አስተያየት
@Dasolo

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-13 11:52:57
ትጋት!
.
.
የእነሱን ልፋት ብቻ አስበን መንገድ ላይ ቆሻሻ አንጣል!!

Bored cellphone Addis Ababa

@Bookfor
@Bookfor
1.3K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 22:59:37 እግረ መንገድ ከተሰኘው የጋሽ ስብሀት መጽሐፍ የተቆነጠረች ንባብ...



<<…ልጅ ሆኜ ነብሴን እጅግ ደስ የሚላት ጢቢ፣ ጢቢ ስጫወት ነበር። ጎረምሳ ሆኜ ነብሴን እጅግ ደስ የሚላት ሴት ልጅን ሳቅፍ ነበር። ዛሬ አርጅቼ ነብሴን እጅግ ደስ የሚላት ልጄ ስትስቅ ሳይ ነው። አሁን እነዚህን ሶስት እኔዎች ሳስተያያቸው አንድ ሰው ናቸው? እርግጠኛ መሆን ያስችላል። እኔ ሽማግሌውስ አንድም፣ አራትም ብሆን ይኸው እዚህ አለሁ። ያ እኔ የምለው ልጅና ያ እኔ የምለው ጎረምሳ ግን የት ሄዱ? የኔ ትውስታ ውስጥ ከልጅየውም ከጎረምሳውም ከብዙ በጥቂቱ እንደ ፊልም ተቀርፆ ይገኛል እንጂ እነሱ ግን የሉም። እኮ እንዴት እኔ ውስጥ ተቀርፀው ሊገኙ ቻሉ? ያን ጊዜ ልጅየው ሆነ ጎረምሳው ሲኖሩ እኔ እዚያ አልነበርኩም'ኮ። ገና አልመጣሁም ነበራ። ያን ጊዜ ያልነበርኩ ሰውዬ ትውስታ ውስጥ አሁን የሌሉ ያን ጊዜ የነበሩ ሰዎች ተቀርጸው ይገኛሉ። ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ? የጊዜና የትውስታ ምስጢራዊ ምትሀት ነው። ለመሆኑ ጊዘና ትውስታ ምንና ምን ናቸው?...>>



ምንጭ ፦ እግረ-መንገድ...ገጽ 206-207

ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር
ጋሽ ስብሃት እቺን መጠይቃዊ ሃሳብ ያሰፈራት ከጆ እና ሀሪ "አራቱ እኔዎች" ፍልስፍና ተነስቶ ነበር...እኛም በጋሽ ስብሀት ሀሳብ ውስጥ እራሳችንን ልንመለከትበት እንችላለን...እሄንን ስናነብ ያለንበትን የዕድሜ ደረጃ እና ያ ካለፈ በኋላ የሚኖረን ስሜት...አሁን በአፍላነታችን የምንመለከትበት አይንና በዕሜው በሰል ስንል የሚኖረን ትርጓሜ ልዩነት እንደሚኖረው የሚካድ አይደለም...

እግረ-መንገድ የሀሳብ እና የፍልስፍና ባህር ነው...እስካሁን ያልሰጠማችሁ ስመጡበት ለማለት እወዳለሁ...!

@Bookfor
@Bookfor
1.5K views19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 22:53:33 #የጊዜ ትርጉም እና አስፈላጊነት#
.
.
.
የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ክፍሉን የደገመ ተማሪ ጠይቀው።

የአንድ ወር ዋጋን ማወቅ ከፈለክ ካለወሩ የተወለደን ህፃን የወለደችውን ሴት ጠይቃት።

የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በየ ሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቅው።

የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ የወሳኝ ፈተና ውጤት ነገ ለመውሰድ የሚጠብቀውን ተማሪ ጠይቀው ።

የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኛሞችን ጠይቃቸው ።

የአንድን ደቂቃ ለማወቅ ከፈለክ አውቶቡስ ለትንሽ ያመለጠውን ሰው ጠይቀው።

የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ከአደጋ ለጥቂት የተረፈን ሰው ጠይቀው።

የአንድን ማይክሮ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀው።
.
.
.
.
.
.
.
......ዶክተር እዮብ ማሞ/Dr eyob mamo
Time management wisdom page 10 and 11
@Bookfor
1.4K views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 09:11:56
ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ወገኖች በሙሉ እንኳን ለ1443'ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

#ዒድ_ሙባረክ!

@Bookfor
1.4K views06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:05:38
ልክ እንደ ትላንቱ
አጥብቄ ብመኝም መሆን እንዳሻዬ
ይኸው በየቀኑ
ሀገሬን ቢገድለዋት ጠፋኝ መድረሻዬ።

@Bookfor
1.7K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 22:04:40
@Bookfor
2.2K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 22:04:23 "ቻው ቻው ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ
ደሞ ትመጣለች ካለእኔ አልችል ብላ
ቻው ቻው ትልና በቃኝ በቃኝ
ደሞ ትመጣለህ አይኔ ለአፈር ብላኝ
ኧረ ጉድ ናት!"

እሱቤን በአልበም የሚያስናፍቅ ከፍ ያለ ስራን "ቻው ትልና" በሚል መጠርያ ነጠላ ዜማ ለቋል፤ ዜማው እንዴት ደስ እንደሚል የእሱቤ አዛዜም ደሞ ሲጨመር ደሞ ዘፈን ከነ ሙሉ ስሜቱ ቁጭ ብሏል በ"ቻው ትልና"፤

"ቀን ሲያልፍ አመረረች በቃ አትመጣም
አልቆባታል የፍቅሬ ጣዕም
ከእንግዲህ እኔም ልተው ከተወችኝ
ፍቅሬን ትታ ከረሳችኝ
በአደባባይ ቆሜ ስለምናት
ማሰብ ከብዶኝ እሷን ማጣት
ጭላንጭል ተስፋ እንኳን በእሷ ጉዳይ
የሚያሳየኝ በር ባላይ"
ይህ ዘፈን ብዙ ሰዎች አንዴ ወይም ከዛም በላይ ቢሆን በሪሌሽን ውስጥ አጋጥሟቸው ያቃል ተብሎ ይገመታል። እሱቤ በግጥሙ ያሰፈረሁ አፍቃሪ ደሞ እሷን መቀበል የማይደክመው ፍቅር በሚል ትራኮማ የተያዘ ነው . . . ስትመጣ ተቀባይ ብቻ የሆነው አፍቃሪ የፈረደበትን ነገር እንዲህ ይገልፃል።
"ዞሬ ከእግሯ ስር ስር ከደጃፏ
አይደለችም ልክ እንደ አፏ
ስትመጣ ተቀባይ ሸኚ ስትሄድ
ሆኗል ልቤ አሽከር መንገድ
ምን እንደሚያለያየን አላውቅም
ስትመጣም አልጠይቃትም
መውደድ አስሮ ገዝቶ ለጉሞኛል
እንደ ግዑዝ አስቀምጦኛል"

ይቀጥላል . . . አንዴ ሄዶ መመለስ ይሆን ደጋግሞ ቻው ብሎ ተመለሱ መምጣት ለይሁን ይከብዳል
"ልቤ በእጁ ፍቅር እየዘወረው
ትንፋሽ ውስጤን እያጠረው
እኔ እያልኩ ለሰዎች አሸማግሉኝ
እሷ እያለች ወይ ገላግሉኝ
ከዚህ ኃላ ብዬ ተገዝቼ
ስትርቅ ከዓይኔ ስንት ዝቼ
ገብቷት ማጠፍያ መዘርግያው ልቤ
አልውል በእሷ እንደ ሀሳቤ"

ወይ ጥላ አትሄድ ወይ ወዶው እሱን ብቻ መርጣው አትቆይ ለያዥ ለገናዥ የቸገረች ሴት
"ጎራ እያለች ስዘጋጅ
እንደልለምድ ሌላ ወዳጅ
ሀሳቤን ስትሄድ አስታኝ
ወይ ትተኝ አታወአኝ ረስተኛ
ደኙኝ አዋዩኝ እባካችሁ
የምታውቁ አፍቅራችሁ
እሷ ብልጥ የቆቅ ዘመድ
እኔ ያለኝ አንድ መወደድ"

ዞራ ዞራ የኔ ናት ብሎ መረጋጋት ያልቻለሁ አፍቃሪ ይህን ጠይቋል
"ቻል ቻል ቻል አድርጌው እንጂ
ባጣ ሰው አስረጂ
ቻው ቻው ብሎ የሄደ ሰው
መመለሱ ምነው?"

Tsion Tamerat


@Bookfor
2.1K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 23:34:31 ...ፍቅር መሸነፍ ነው። ፍቅር መያዝ ነው። ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው። ፍቅር ከምክንያት ውጭ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው። ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጭ መሆን ነው” ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው። ያስፈራል ፍቅር፤ የማይታከሙት ህመም፣ የማይጠገን ቁስል፣ የማያባራ እንባና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል።”

የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን፤ ማፍቀር ራሱ ነው። ካፈቀርሽ በኋላ “እኔ” የምትይው ሁሉ ይጠፋል። ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ። በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።”

ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፤ እጅ መስጠት፣ ወዶ መግባት፣ ከራስ መነጠል፣ መጥፋት፣ በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ። አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል።” ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው። ሰው ስለሆንን ነው። ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን። አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው። አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና ያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ ምን እንደሚመጣ፣ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም። ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጭ ነው”

አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል። ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩት ባለሁበት ሁኔታ፤ ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው። ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ በሰላም እኖራለሁ” ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል። ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ስራዬ፣ ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመሰያዎች በሙሉ ትርጉም ያጣሉ። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ
ታውቂያለሽ” አላት...

ከ <አለመኖር >

@Bookfor
@Bookfor
2.5K views20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ