Get Mystery Box with random crypto!

የመጽሐፍት እና የእውቀት ማዕድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bookandknowledg — የመጽሐፍት እና የእውቀት ማዕድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ bookandknowledg — የመጽሐፍት እና የእውቀት ማዕድ
የሰርጥ አድራሻ: @bookandknowledg
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 461
የሰርጥ መግለጫ

║ እንኳን ደህና መጡ ║
#አዳዲስ መፃህፍት ጥቆማ
#ወግ
#ግጥም
#ድንቃድንቅ
ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያይት @NEVERSEYA
ይላኩልን ::

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-02 17:13:08 አትተርጉሙ!

አንድ አባት ከልጆቹ ጋር ወደ አንድ ካፌ ይገባል። ካፌው ውስጥ እንደገቡ ብዙም ሳይቀመጡ ልጆቹ መሯሯጥና እየተጯጯሁ መጫወት ይጀምራሉ። ይሄ ሁሉ ሲሆን አባት አንገቱን ደፍቶ በሀሳብ ጭልጥ ብሏል። ይሄን ሁሉ የሚመለከት አንድ ሰው በልጆቹ እንቅስቃሴ ተረብሾ ልጆቹን ስርአት የማያስይዝ ምን አይነት ቸልተኛ ሰው ነው እያለ በአባታቸውን ይናደዳል።

በዚህ ብስጭት ውስጥ ሆኖ የሚሯሯጡት ልጆች ድንገት የእሱን ጠረጴዛ ነክተውት ኖሮ ያዘዘው ሻይ ልብሱ ላይ ተደፋ። ይሄን ጊዜ ንዴቱን መቋቋም አቅቶት ውደ አባትየው ሄደ። ለግጭት እየተጋበዘ ሊያንቀውም እየዳዳው ”ምን አይነት የማትረባ ሰው ነህ? ልጆችህን ስርአት አታስይዝም?” ብሎ አምባረቀበት። አባትየው በረጅሙ ተንፍሶ በተረጋጋ አንደበት ”ወዳጄ የልጅነት ሚስቴ የልጆቼ እናት ታማ ከምትረዳበት ሆስፒታል አሁን ከመግባታችን ተደውሎ መሞቷን ነገሩኝ። ምን ማድረግ እንዳለብኝና ለልጆቼ ምን እንደምል ግራ ገብቶኛል” አለው። ይሄን የሰማው ሰው በትልቅ ድንጋይ እንደተመታ ሰው ራሱን አመመው።

በህይወታችን ከምንሰራቸው ስህተቶች ውስጥ አንዱ ስለ ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ሳይኖረን በራሳችን መተርጎምና መፈረጅ ነው። ሰዎች የሆነ ነገር ሲያደርጉ ስለማይወደኝ ነው፣ ስለማያከብረኝ ነው፣ ስልክ ሳያነሱ ወይ የሆነ ነገር ሲያደርጉ ሲቀሩ ደግሞ ሆን ብለው ነው ብለን በራሳችን እንተረጉማለን። የትርጉም ዋናው መዘዝ ከእውነታው አለም ያወጣንና የራሳችንን አለም እንደንፈጥር ያደርገናል። በህይወት ያሉትን ሰዎች እንገላቸውና ክፉ ናቸው አያከብሩኝም የምንላቸውን የራሳችንን ሰዎች በአዕምሯችን እንፈጥራለን። ሀሳባችንን ፊት ለፊት የመናገር ልምድ ስለሌለን በራሳችን ትርጉም በውስጣችን እንበሰለሰላለን፣ እንጎዳለን።

መፍትሄው ምንድን ነው?

1. ምቾት ያልሰጡን ነገሮች ሲኖሩ በራሳችን ከመተርጎም ይልቅ ፊት ለፊት መጠየቅን እንለማመድ።

2. ያሰብኩትና የተሰማኝ ሁሉ ትክክል ነው ማለትን እናቁም።

3. ሰዎች በብዙ ችግርና ውስብስብ የህይወት መንገድ ያልፋሉና ለመረዳት እንሞክር። በዚህ መልኩ ጤናማ ግንኙነታችንን ማዳበር እንችላለን።

ኤርሚያስ ኪሮስ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)


@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
110 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 09:36:03 ያለማቋረጥ ሌሎችን የሚወነጅሉ ሰዎች እነዛ ሰዎች አደረጉት ያሉትን ነገር እራሳቸው በተደጋጋሚ ሲፈፅሙት ይታያሉ ! Keep in mind


@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
273 views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 11:06:25 #የስኬት_መንገድ

ትህትና የሚመነጨው በራስ ከመተማመን ነው።

ተግዳሮቶችህን ሳይሆን በረከትህን ቁጠር።

የምር እንዲሳካልህ ከፈለክ ሳትጨርስ አታቁም።

አብዛኞቻችን እርግፍ አድርገን የምንተወው ሊሳካልን ጥቂት ሲቀረን ነው።

ለመባል ሳይሆን ለመሆን እንጣር ምክንያቱም ስንሆን መባሉ አይቀርም እና።

አብኛዎቹ ሰዎች የሚወድቁት ችሎታ ወይም ክህሎት ስላነሳቸው ሳይሆኑን ስለሚተውት ነው።


@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
342 views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 14:09:43
" አካውንቲንግ በአማርኛ " ሁለተኛው ዕትም ለንባብ በቅቷል ::

@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
395 viewsedited  11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 22:01:30 ብዙ ሰዎች ትክክለኛው ሰው በመሆን ፈንታ ትክክለኛውን ሰው ለማግኘት ይሞክራሉ !


@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
318 views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 14:30:23
@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
370 views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 14:00:21 የውሸት ጓደኛ ልክ እንደጥላ ነው ብርሃን ሲሆን ይከተልሃል፤ ጨለማ ሲሆን ጥሎህ ይጠፋል !


@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
375 views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 22:54:57 ጠንካራ ሰዎች ሌሎችን ወደ ላይ ከፍ ያደርጋሉ እንጂ ወደታች አይረግጡም !
-- Michael Watson --


@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
387 views19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 22:18:14
@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
427 views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 10:32:37 እባብ በህይወት እያለ ጉንዳንን ይበላል።እባብ ሲሞት ጉንዳኖች ይበሉታል ጊዜ በማንኛውም ሰአት ይለወጣል።በህይወትህ የማንንም ዋጋ አታሳንስ. ምን አልባት የበለጠ ሀያል ነው።አንድ ዛፍ መቶ ሺ ክብሪቶችን ሲሰራ አንድ ክብሪት ግን መቶ ሺ ዛፎችን ታቃጥላለች።አንድ መጥፎ ስራ ጥሩ ድርጊቶችን ታጠፋለች።ዋናው ነገር ሰዎችን የምታከብር በአስተሳሰብህ ዘመናዊ እና ጥሩ አመለካከት ያለህ ሁን!!


@BookandKnowledg
@BookandKnowledg
392 views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ