Get Mystery Box with random crypto!

የተቀዳሚ ደንበኞች ፤ የ”እንሸልምዎ”፤ ”መቆጠብ ያሸልማል” ፤ እንዲሁም የ”አበባ -አየሽ ወይ”የ | Bank of Abyssinia

የተቀዳሚ ደንበኞች ፤ የ”እንሸልምዎ”፤ ”መቆጠብ ያሸልማል” ፤ እንዲሁም የ”አበባ -አየሽ ወይ”የሽልማት እና ዕውቅና ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ፡፡
ሐሙስ መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ፤ ሸራተን አዲስ በላሊበላ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ ዝግጅት ፤ ከተለያየ ዘርፍ የተመረጡ የባንካችን ተቀዳሚ ደንበኞች የዕውቅና ሰርተፍኬት፣ የዋንጫ እንዲሁም የቅድሚያ ሰርቪስ የሚያገኙበት ፕላቲንየም ኮርፖሬት ካርድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የ”እንሸልምዎ”እና ”መቆጠብ ያሸልማል” የሽልማት ክዋኔ የእለቱ ሁለተኛ ዐብይ ዝግጅት ነበር፡፡ በ”መቆጠብ ያሸልማል” የሽልማት መርሐ-ግብር ፤ ባለሁለት መኝታ አፓርታማ ቤትን ጨምሮ 147 ሽልማቶች ለዕድለኞች የተላለፉ ሲሆን፤ የ”እንሸልምዎ”የሽልማት መርሐ-ግብር ደግሞ የቤት አውቶሞቢልን ጨምሮ 42 ሽልማቶችን የተካተቱበት ነበር ፡፡ በዝግጅቱም ላይ በቁጥር 16 የሚደርሱ ዕድለኞች በመድረኩ በመገኘት ሽልማቶቻቸውን ከባንካችን የበላይ አመራር እጅ ተቀብለዋል፡፡
የዕለቱ ሶስተኛው አብይ ዝግጅት በባንካችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰናዳው የ”አበባ -አየሽ ወይ”የሽልማት ውድድር አሸናፊዎችን መሸለም ሲሆን ፣ በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ አሸናፊዎች በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ ተገኝተው ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡