Get Mystery Box with random crypto!

“የአበባየሽ ወይ” ሽልማት ውድድር! “የአበባየሽ ወይ” ጨዋታ የተስፋ፣ የአብሮነት እና የደጋግ ም | Bank of Abyssinia

“የአበባየሽ ወይ” ሽልማት ውድድር!
“የአበባየሽ ወይ” ጨዋታ የተስፋ፣ የአብሮነት እና የደጋግ ምኞቶች መገለጫ በመሆን ለዘመናት የአዲስ ዓመት መወድስ በመሆን ዘልቋል፡፡ ባንካችን አቢሲንያም ለዚህ ድንቅ ዕሤት ጥልቅ አክብሮት ስላለው፤ አርማውን በአደይ አበባ ወክሏል፡፡ አሁንም ይኽንን ድንቅ ዕሤት የበለጠ ለማጉላት የሽልማት ውድድር በማሠናዳት ተሳታፊዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
ተሳታፊዎች ጨዋታቸውን ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመላ ሀገራችን በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች ያቀርባሉ፤ ባንካችንም ከ1 አስከ 10 ለሚወጡ አሸናፊ ቡድኖች ከብር 100 ሺህ እስከ 10ሺህ ሽልማት ይሰጣል፡፡
መልካም ዕድል፤ መልካም በዓል!
ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች የተያያዙትን የመወዳደሪያ መስፈርት እና ቅፅ ይመልከቱ።
አቢሲንያ ባንክ የሁሉም ምርጫ!

#BankofAbyssinia #BankinginEthiopia #newyear #2015 #gift #giveaway #contest #adeyabeba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ