Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከ11ሺ በላይ የክላሽ፣ ከ6ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተ | Bisrat-Media - ብስራት ሚዲያ

በአዲስ አበባ ከ11ሺ በላይ የክላሽ፣ ከ6ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ!

ሦስት የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ሁለት ተሽከርካሪዎችን ተጠቅመው ሲያዘዋውሩት የተገኘ ከ11ሺ በላይ የክላሽ፣ ከ6ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ሃና ማርያም አካባቢ ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-69099 አ/አ ቶዮታ ተሽከርካሪ ብዛቱ 
6ሺ 494 የሽጉጥ ፣
11ሺ 275 የክላሽ ጥይት ፣
የ11 የተለያዩ መሳሪያዎች ጥይት ፣
በባለሙያ የተፈታቱ 9 የብሬን ሰደፍ ፣
4 የብሬን ተመላላሽ ሽቦ ፣
6 የብሬን ተመላላሽ ዘንግ፣
ልዩልዩ የክላሽ ኮቭ ጠብመንጃ አካሎች ፣ዝናር
ብዛቱ 37 የሽጉጥ ካርታ ከሌሎች የጦር መሳሪያዎች ጋር እንዲሁም በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B-01563 አ/አ ቶዮታ ሎንግ ቤዝ በሆነ ተሽከርካሪ 465 የስታር ሽጉጥ ጥይት እና 1 ኢኮልፒ ሽጉጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ክትትል መያዛቸውን የአዲስ አበባፓሊስ አስታውቋል፡፡

ከሁለቱ ተሽከርካሪዎች 11ሺ275 የክላሽ እና 6ሺ 959 የሽጉጥ ጥቶችን ከልዩ ልዩ ጦር መሳሪያዎች ጋር መገኘቱ ታውቋል ፡፡ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙት ሶስት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡