Get Mystery Box with random crypto!

በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ለሁለትዮሽ ውይይ | ብስራት ሚዲያ

በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ለሁለትዮሽ ውይይት ሩሲያ /ሞስኮ/ መግባቱ ተገለፀ ።

በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ከብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ጋር ለመወያየት እና የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክትን ለማድረስና በሁለትዮሽ የአብያተ ክርስቲያናቱ ቀጣይ ግንኙነት ላይ ውይይት ለማድረግ ሞስኮ መግባቱ ነው የተገለፀው።

የልዑካን ቡድኑ አባላት የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጊዜያዊ እና ቋሚ ፕሮጀክቶች መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

@Bisrat_Midea