Get Mystery Box with random crypto!

#ይታተማሉ የተባሉቱ የዶ/ር እጓለ ገ/ዮሐንስ ሦስቱ መጻሕፍት ወዴት ገቡ? 'ብፁዓን ንጹሓነ ልብ' | ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

#ይታተማሉ የተባሉቱ የዶ/ር እጓለ ገ/ዮሐንስ ሦስቱ መጻሕፍት ወዴት ገቡ?

"ብፁዓን ንጹሓነ ልብ" በተሰኘው መጽሐፋቸው፥ "የጋሽ እጓለ ሦስት መጻሕፍት ወደፊት ይታተማሉ!" ተብሎ በገጽ 175 ላይ ተቀምጦ ነበር። የመጻሕፍቱ አርእስትም፦

1. ሥነ ምግባር (የጀርመናዊው ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንት ስለሞራል ፊሎሶፊ ከጻፋቸው ሦስት መጻሕፍት በአንደኛው ላይ የተመረኮዘ መጽሐፍ)

2. ከተረት ወደ ሕሊና (ስለፍልስፍና መንፈስ ልደትና እድገት በመተንተን ስለሰው መንፈስ የድል ጎዳና በሰፊው እሚያትት መጽሐፍ)

3. ፋውስት (ጀርመናዊው ባለቅኔ ጎተ፥ ለሃምሳ አመታት ደጋግሞ የጻፈው፥ የትራጀዲ ዘውግ ያለው መጽሐፍ)

#እነዚህን የመሳሰሉ መጻሕፍት የውሃ ሽታ ሆነው መቅረታቸው ያሳዝነኛል። ኧረ የጋሽ እጓለን ድካም፥ የህትመትን ብርሃን እንዲመለከቱ በማድረግ፥ መጻሕፍቱ ለትውልድ እንዲደርሱ እንረባረብ።

#የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤን በድጋሚ እንዲታተም ያደረጋችሁት በሞላ፥ ገለታ ይግባችሁ። በነካ እጃችሁ፥ ሦስቱንም መጻሕፍታቸውን የህትመት ብርሃን እንዲያገኛቸው ታትሩ። ስለንባብ አምላክ!

https://t.me/binibook