Get Mystery Box with random crypto!

#ለብ ባለ ውሃ፥ ገላውን ለመታጠብ ገንዳ የሚሞላ ሰው፥ ገንዳው ውስጥ ዘሎ ከመግባቱ በፊት፥ የውሃው | ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

#ለብ ባለ ውሃ፥ ገላውን ለመታጠብ ገንዳ የሚሞላ ሰው፥ ገንዳው ውስጥ ዘሎ ከመግባቱ በፊት፥ የውሃውን ሙቀት እጁን ወይም ክንዱን እያስገባ ይለካል። ደርግም ንጉሱን አውርዶ ስልጣን በእጁ እስካስገባበት - እስከ መስከረም 2፣ 1967 ዓ.ም ያደረገው ነገር፥ የገላ ታጣቢውን ምሳሌ የሚመስል ነው። ከነገሌው የወታደሮች አመጽ ጀምሮ፥ ከታህሳስ 1966 ዓ.ም እስከ መስከረም 2፣ 1967 ዓ.ም ድረስ የነበረው ጊዜ፥ ለወታደሮቹ የውሃውን ሙቀት የመሞከሪያ ጊዜ ነበር። ወታደሮቹ "ዘሎ ስልጣን መያዝ የሚፋጅ ነገር ሊሆን ይችላል" የሚል ትልቅ ስጋት ነበራቸው።

#ገጽ 420
#ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር
#አንዳርጋቸው ፅጌ

https://t.me/binibook