Get Mystery Box with random crypto!

#ሌሊሳ ግርማ የቀኗ አዲስ አበባ ሁሌ ለነገ የምትዘጋጅ ከተማ ናት። ነገ ለማማር ዛሬ ጸጉሯን ተተ | ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

#ሌሊሳ ግርማ

የቀኗ አዲስ አበባ ሁሌ ለነገ የምትዘጋጅ ከተማ ናት። ነገ ለማማር ዛሬ ጸጉሯን ተተኩሳ በቢጎዲን ጠቅልላ፣ ፊቷን ምናምን ለቅልቃ ተኝታለች። ለነገ ውበቷ ስታስብ ዛሬ በነጻነት ሊነካት ለፈለገው ባሏ እንደማትመቸው ሚስት። አዲሳባ ሁሌ ለነገ ነው የምትዘጋጀው።

የምሽቷ አዲስ አበባ ደግሞ ከቆሻሻ የጥበብ ቀሚሷ ስር የፈረንጅ ውስጥ ልብሷ የረዘመባት ባለንቅሳቷን ሴት ትመስላለች። ጸጉሯን ግማሹን ተተኩሳ ግማሹን ሹሩባ የተሰራች።

አፍሮጋዳ ገጽ 59

https://t.me/binibook