Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ስዩምና ግጥሞቹ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bewketuspoem — በእውቀቱ ስዩምና ግጥሞቹ
የቴሌግራም ቻናል አርማ bewketuspoem — በእውቀቱ ስዩምና ግጥሞቹ
የሰርጥ አድራሻ: @bewketuspoem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.47K
የሰርጥ መግለጫ

📝የበእውቀቱ ስዩምን ግጥምና ወጎች
የተለያዩ ገጣሚያንን ፅሁፎች
📖📚አዳዲስ መፅሐፎችን
join 👉👉👉@bewketuspoem
ለአስተያየት@yabang6

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-11-28 08:32:07
# ዛሬ ስለ ወጣቱ ተዐምረኛ ገጣሚ ልንገራቹ
ናትናኤል ግርማቸው ይባላል በሙዚቃ
ክሊፕ ግርጌዎች ላይ ስሙን ማየት የተለመደ ሆኗል። የሙዚቃ ግጥም ደራሲ ነው። የዘመኑ ይልማ ገብረአብ ቢባል አያንሰውም እልፍ ለሊቶችን ሳይተኛ ብዕሩን ሲያስለቅስ ያድራል በአካል ለማያውቀው ሰው እድሜውን በትልቁ ሊገምት ይችላል።ትልልቅ ሀሳቦችን በ አምስት ደቂቃ ገልፆአል።
ከሰራቸው ስራዎች
ዳዊት ፅጌ -እትቱ፣ውዴ ውዴ ፣ደሳለኝ እና ሌሎችን
አጫሉ እና አዲስ - እማ ውዴ
ተዐምር ግዛው- ምነዋ
ራሄል ጌቱ -ኢትዮጵያ
ብስራት ሱራፌል -አለና፣ኢትዮጵያዊ ነን፣ ዛሬሞ ከኋላ አና ሌሎችን
አዲሱን የሀገር ካስማ
ተመስገን ታፈሰ - ሳብየ
እና ሌሎች በጣም ብዙ ስራዎችን አድርሶናል።
"ጦር ይሰበቃል ወይ
ጋሻ በሌለው ሰው"
Respect
Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
4.8K viewsYabang, 05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-04 10:35:54
ሀገሩን በሙሉ ፣ ጨለማ ሲወርሰው
"ገጣሚ ነኝ" ያለ
ለጨረቃ ውበት ፣ ቢቀኝም ሰዋሰው
እኔ የማደንቀው
ክብሪትና ሻማ ፣ የሸጥሽልኝን ሰው!!
(በላይ በቀለ ወያ)
#SHARE
Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
2.7K viewsYabang, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-04 10:34:21 አንቺ ባለሽበት ፣ሚባለውን እንጃ
እኔ ባለሁበት ፣ ወሬ እንደጠብ መንጃ
የታጠቀ ሞልቷል ፣ ቢደላም ቢከፋም
ጆሮ አይሰማው የለም
የሚበላ እንጂ ፣ የሚባል አይጠፋም !
#ይባላል !
።።
ለምሳሌ ያህል
ትጥቃችን ባያልፍም
ከዱላ ከድንጋይ ፣ ግፋ ቢል ከክላሽ
ወዮለት ለጠላት ፣ ኋላ እንዳይበላሽ
ኒውክለር ሲመካ
አደቧን ትያዝ ግብፅ ፣ ትረፍ አሜሪካ
አላርፍም ካሉ ግን ፣ ወየው ለሁለቱም
ባለም ፊት ፈስ በፈስ
እንዳናደርጋቸው
በእጃችን ነው ያለው ፣ ደብተራም መተቱም
ይባላል
፣፣፣፣
ለምሳሌ ያህል
ሰማንያ ሺህ ዳቦ ፣ ሊያውም በአንድ ቀን
ሊጋገር ነው ሲሉን ፣
በምን መብራት ብለን ፣ አናውቅም ጠይቀን
እንዲሁ በማመን ፣ ሆዳችን ይሞላል
በመሪ አንደበት
ደም ያፀናው ሰንደቅ ፣ ጨርቅ ነው ይባላል።
።።።
እኔ ባለሁበት ፣ በመኖሬያዬ ሀገር
ከፀሐይዋ በታች ፣ የማይባል ነገር
አንዳች አይገኝም ፣ ሁሉ አፉን ያክላል
የሚለው ያጣ ሰው
የተባለን ነገር ፣ "አይባልም "ይላል
።።
የሆነው ሆነና ፣ ባለሁበት ሀገር
የማይባል ነገር
አጋጥሞኝ አያውቅም
ለምሳሌ ያህል
አባይ በአምስ አመት
ተገድቦ ያልቃል
በኢትዮጵያ ምድር ፣ ፀሀይ አትጠልቅም
አስራ አንድ ፐርሰንት
ሀገሪቱ አድጋለች ፣ በኑሮ ብንደቅም
ስልጣን የህዝብ ነው ፣ ግን ለህዝቡ አንለቅም
ይባላል

ለምሳሌ ያህል
ባይቆጥራቸው እንጂ፣ ዘንግቶ ምናልባት
ጠቢቡ ሶሎሞን
ከጠቢቡ በላይ ፣ አይበልጥም በእቁባት
#ይባላል
በላይ በቀለ ወያ

Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
2.6K viewsYabang, edited  07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-04 10:20:33
እንደ ጊዜው መክፋት
እንደ ግፉ መስፋት
እንዳገሩ ክስመት
እንዳገሬው ጥመት
እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ::

የበጎ ሰው ሀሳብ
ሲካድ እለት በእለት
ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር
በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር ::

ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ
ከዘብጥያ ወጥቶ
ዘብጥያ ወረደ
የሚል ዜና ብቻ ፥ አየሩን ሲሞላው
ሰው በገዛ ጥላው ፥
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር፥ አያስመኝም ነበር ፤

አዎ
ለጊዜውም ቢሆን ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ፥ ወደ ፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ፤ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፥ ሚስቱን ያስረግዛል ::

ይቅርታና ምህረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፥ ቢሆን የሞት ሽረት
ዳገት ይወጣሉ፥ በንጥፍጣፊ አቅም
የመኖር ፍላጎት
ዘመም ይላል እንጂ ፥ተገርስሶ አይወድቅም ::

( አዳምኤል )
Bewketu Seyoum
Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
2.8K viewsYabang, edited  07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-04 10:19:34 አርማሽ ይውለብልብ ፥ ይህ ቀለም
ከደጄ አልፎ ፣ በዓለም
እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ
ባገሬ ሀገር ናፈቀኝ !
።።፣፣
(የቴዲ አፍሮ ነጠላ ዘፈንን ሪሚክስ ሳደርገው)
Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
2.1K viewsYabang, 07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-31 14:54:17 የሰማይ ቤት ግሮሰሪ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ጨረቃ" ምንላት
ግሮሰሪ ቤት ናት
"ሰማይ" ለምንለው ፣ ቀውጢ ከተማ
ሥራ ምትጀምረው ፣ሲሆን ነው ጨለማ!!!
።።።።
ከዋክብት ደግሞ ፣ አብረዋት 'ሚወጡ
ሰካራሞች ናቸው ፣ እሷ ጋር ሚጠጡ!!!
።።።
በጣም የሰከረው...
ራሱን ከሰማይ ፣ ፈጥፍጦ ሲገድል
"ተወርዋሪ ኮከብ" ፣ ማለት ነው የኛ እድል!!!
ሼርርርር
Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
2.8K viewsYabang, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-31 11:10:48 "የኔ ሀገር ሲንኳኳ ፣ ላንተ ሀገር ይሰማል
የኔ ቤት ሲቃጠል ፣ ያንተም ቤት ይከስማል፡፡"
የሚል የቆየ ሐቅ ፣ ታዲያ ምን ይገርማል?!!
።።።።።።።
ይልቅ የሚገርመው ፣ ይልቅ የሚደንቀው
የኔ ቤት ሲቃጠል ፣ ያንተ ቤት ከሞቀው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይልቅ የሚገርመው ፣ የሚደንቀው ነገር
ያንተ ሀገር ሲንኳኳ ፣ ካልተሰማ እኔ ሀገር
ወይ ተሰድጃለሁ ፣
ወይ አውቆ ተኚ ነኝ ፣ ወይም አለ ነገር።
።።።።
(በላይ በቀለ ወያ)
Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
2.1K viewsYabang, edited  08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-28 21:59:58 ላንዲት ማስቲካ ሻጭ ህፃን

በደብተርሽ ምትክ
ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ
ካልፎሂያጅ እግር ስር፤
እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ
ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ አንጋጠሽ ወደ ላይ
ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ
ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው
ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው !!
አፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ
መስኩ ከነጎርፉ ፥
ሰማይ ከነዶፉ ፥ ለጌቶች ተሽጦ
አተር ነው እያሉ፤ አፈር ዘግኖ መፍጨት
ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት
ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት
ይህንን ማን ሰጦሽ
ገና በልጅነት፤ ልጅነት አምልጦሽ፡፡
በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ
በክራር ተማግሮ
በቆመ ከተማ
እምባሽ ቅኝት የለው ፤ ለሰው አይሰማ፡
ጠዋት የፎከረ ፤ ቀትር ላይ ሲረታ
ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ ትናንት የበረታ
ኑሮን ያህል ሸክም ፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡
ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡

በእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ይቀላቀላሉ! ➢➢➢
Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
3.3K viewsYabang, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-26 21:40:30 ሳቅ እንደ መክሊት
(በእውቀቱ ስዩም)

እንደ ቁልቋል ደም፤ የነጣው ጥርስሽ
ለዛ ተነቅሶ ፥
ለሳቅ ተፈጥረሽ- ጊዜው የለቅሶ ::
ጎጆሽ ግድግዳው ፤ በንባ ቢለሰን
የተጀመረ፤ ደሞ አለው ወሰን::
አዝነን ብንወጥን፤ አዝነን አንቀርም
ይባዛል እንጂ-
ሳቅ እንደ መክሊት አይቀበርም!


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
3.2K viewsYabang, 18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-26 21:36:28 አሁን እኔ ብሞት ፣ ከኔ ምን ይቀራል?
ስኖር "ክፉ" ያለኝ
"ደግ ሰው ነበረ " ፣ እያለ ያወራል።
"እሱ ሰው አይደለም" ፣ ሰይጣን ነው መሠሪ"
ሲለኝ የከረመ ፣
"መልካም ሰው ነበረ ፣ መልአክ መሥሎ ኗሪ"
ብሎ ቀብሬ ላይ ፣ እንባውን ይዘራል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የተናቀ ፣ ሲሞት ይከበራል ።
* * * *
የሚጠላኝ ሁላ
ተወዳጅነቴን ፣ ቀብሬ ላይ ያወሳል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የሚነቀፍ ፣ ሲሞት ይወደሳል
ሲኖር የተረሳ ፣ ሲሞት ይታወሳል!!!
* * * *
( በላይ በቀለ ወያ)
Join

@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
2.0K viewsYabang, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ