Get Mystery Box with random crypto!

ከተባባልንበት ፣ከቀጠሮ ቦታ ካሊ ታንጎ ደጃፍ ፣ከባሱ ፌርማታ ያልጠበኳት መጣች፣የጠበኳት ቀርታ ጥር | በእውቀቱ ስዩምና ግጥሞቹ

ከተባባልንበት ፣ከቀጠሮ ቦታ
ካሊ ታንጎ ደጃፍ ፣ከባሱ ፌርማታ
ያልጠበኳት መጣች፣የጠበኳት ቀርታ
ጥርሴን እያፏጨሁ፣በቀረችው ቀጥራኝ
ሌላ የደም ገንቦ ፣ደሞ እንዳዲስ ጠራኝ
ለካ ለሀጣን ነው ፣የሚሉት ቀጠሮ
ፃድቅ ይገናኛል ፣ ቢጠፋፋም ዞሮ
እናማ የኔ ዉድ፣ እንችም ቶሎ ድረሽ
እሷም አርፍዳ ነው፣ አንቺ የተገኘሽ


የአብ ካሳ

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
Join
@bewketuspoem
@bewketuspoem
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟