Get Mystery Box with random crypto!

የቦርሳሽ ላይ ሥእል ካነገትሽው ቦርሳ ፥ ከጀርባሽ ላይ ካለው የዚያ ዘፋኝ ምስል ፥ ደምቆ የታተመ | በእውቀቱ ስዩምና ግጥሞቹ

የቦርሳሽ ላይ ሥእል

ካነገትሽው ቦርሳ ፥ ከጀርባሽ ላይ ካለው
የዚያ ዘፋኝ ምስል ፥ ደምቆ የታተመው
ልብ ብዬ ሳየው ፥ ሁሌም ይገርመኛል
እንደ ኪነት ተውኔት ፥ ማርኮ ያስቀረኛል

ያንን የጨርቅ ቦርሳ ...
በደብተር በመፅሃፍ ፥ የወጠርሽው ለታ
በድምፃዊው ፊት ላይ ፥ ይታያል ፈገግታ!
ባዶ ሲሆን ደ'ሞ ፥ ወይ አንድ-ሁለት ደብተር፤
ጨርቁ ተጨማዶ...
አያለሁ ስእሉን ፥ ደርሶ ሲኮሳተር!

ይህ አይደለም ወይ? የእኛስ ህይወት ዳራ
ሁለት አይነት ምስል ፥ በአንድ የስእል ሸራ!
ትንግርቱ ገፃችን፤
በቀን አስር ጊዜ ፥ ተቋጠሮ 'ሚፈታ
ሲጎድል ትካዜ ፥ ሲሞላ ፈገግታ!!

እራሱ ገጣሚዉ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ይቀላቀላሉ! ➢➢➢
Join
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem
@bewketuspoem