ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኡራጓይ የአለም ከ20 አመት በታች እግር ኳስ ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች
በአርጀንቲና አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየዉ የ2023 ከ20 አመት በታች የአለም እግር ኳስ ዋንጫ ዉድድር ሲጠናቀቅ ኡራጓይ ጣሊያንን 1ለ0 በመርታት በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ20 አመት በታች የአለም እግር ኳስ ዋንጫ አሸናፊ መሆን ችላለች።
ሉቺያኖ ሮድሪጌዝ በ86ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት ያስቆጠራት ብቸኛ ጎል ኡራጓይን ሻምፒዮን ስታደርግ በውድድሩ የአውሮፓ ቡድኖችን ለአራት ተከታታይ ጊዜ ሻምፒዮን የሆኑበትን ጉዞ ያስቆመችም ሆናለች።
በዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ከ40,000 በላይ ተመልካቾች የታደሙ ሲሆን የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖም ተገኝተዋል።
ኡራጓይ በ1997 እና 2013 በዉድድሩ ለፍፃሜ ደርሳ ዋንጫዉን ማጣቷ የሚታወስ ነዉ።
ብራዚል በ2011 ከደቡብ አሜሪካ የመጨረሻው የዉድድሩ አሸናፊ የነበረች ሀገር ናት።
ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ በዉድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችዉ እስራኤል ደቡብ ኮሪያን 3ለ1 በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃን ማግኘት ችላለች።
Website : www.hattricksportofficial.com
Website : www.bestsportet.com
Facebook : facebook.com/hattricksportofficial
Facebook : facebook.com/bestsportet
Telegram : t.me/bestsportet
Twitter : twitter.com/bestsportet
#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...