2022-06-29 18:02:38
የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2014ቱ የውድድር ዘመን የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ተስተካክሎ ይፋ ተደርጓል። የሊጉ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ የውድድር ደንብ አካሄዶችን ታሳቢ በማድረግ ተከታታይ ውይይቶችን ካደረገ በኋላ ከታች ያለውን ፕሮግራም ይፋ አድርጎ ዛሬ ሰኔ 22/2014 ዓ.ም ለክለብ ቡድን መሪዎች በተዘጋጀ መድረክ አሳውቋል።
በዚህ መሠረት ዓርብ ሰኔ 24/2014 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት ሶስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
በዓርብ መርሐ ግብር በባህር ዳር ስታዲየም የሚከናወነው ጨዋታ በሱፐር ስፖርት ቀጥታ ስርጭት ያገኛል። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሚስተናገደው ጨዋታ ደግሞ በአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን ቀጥታ ስርጭት ሲኖረው በአጼ ቴዎድሮስ የሚካሄደው ጨዋታ በሱፐር ስፖርት ቀረፃ ይደረግበታል።
የዋንጫ መርሐ ግብሩ በእለቱ አርብ ሰኔ 24/2014 ዓ.ም በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም በሚዘጋጅ መድረክ የሚካሄድ ይሆናል።
ሐሙስ ሰኔ 23 2014
- 04:00 ወላይታ ድቻ - ወልቂጤ ከተማ
(ባህር ዳር አስታዲየም)
- 07:00 ሰበታ ከተማ - አርባምንጭ ከተማ (ባህር ዳር ስታዲየም)
ዓርብ ሰኔ 24 2014
- 04:00 ሃዋሳ ከተማ - አዳማ ከተማ
(አፄ ቴዎድሮስ ስታዲየም)
- 04:00 ድሬደዋ ከተማ - ፋሲል ከነማ
(ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም)
- 04:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ - አዲስ አበባ ከተማ - (ባህር ዳር ስታዲየም)
ቅዳሜ ሰኔ 25 2014
- 04:00 ጅማ አባ ጅፋር - መከላከያ
(ባህር ዳር ስታዲየም)
- 07:00 ሲዳማ ቡና - ሀዲያ ሆሳዕና
(ባህር ዳር ስታዲየም)
- 10:00 ኢትዮጵያ ቡና - ባህርዳር ከተማ
(ባህር ዳር ስታዲየም)
ምንጭ:- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አማ
@Beki_Dish
@Beki_Dish
#call +251906856299
145 viewsBeki Dish, edited 15:02