Get Mystery Box with random crypto!

#ጥር_15_ዕረፍቱ_ለቅዱስ_ቂርቆስ። ቅዱስ ቂርቆስ ከእናቱ ከቅድስት ኢየሉጣ ፤ ከአባቱ ከቆዝሞስ | ዝክረ ብሒለ አበው

#ጥር_15_ዕረፍቱ_ለቅዱስ_ቂርቆስ።

ቅዱስ ቂርቆስ ከእናቱ ከቅድስት ኢየሉጣ ፤ ከአባቱ ከቆዝሞስ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ነበር ነበር የተወለደው፡፡ ዲዮቅልጥያኖስ 303 ዓ.ም አካባቢ የጣዖት ቤቶች እንዱከፈቱ ቤተ ክርስቲያናት እንዱዘጉ አደረገ ፤ ይህ የዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት የክብር ባለቤት የሆነው ክርስቶስን በሚያምኑ ክርስቲያኖች ላይ ታላቅ መከራና ስደት የሆነበት ወቅት ነበር፡፡ በዚያም ሀገር ስሟ ኢየሉጣ የምትባል አንዱት ሴት ነበረች፡፡ ከታናሽነቷ ጀምራ ደግ ለደሀ ለተቸገረ የምትራራ ምስኪን ሴት ነበረች፡፡

በዚህም ሀገር በክርስቲያኖች ላይ ስደት እንደሆነ በሰማች ጊዜ መኮንኑን ከመፍራት የተነሳ ሕፃኗን ይዚ ከሮም ከተማ ተሰዳ ኪልቅያ አውራጃ ከሆነ ከጠርሴስ ደርሳ በዚያም በተለያዩ ሀገሮች ውስጥ እየተዘዋወረች ተቀመጠች፡፡በዚህ በጠርሴስ ተቀምጣ ሳለች ያ ከሮም እርሱን ፈርታ ሸሽታው የመጣችው መኮንን ወደ ጠርሴስ እንደገባ ሰማች፡፡ ይህ መኮንን ወደ ጠርሴስ የመጣው ከሮም የእርሱን ትዕዚዜ እምቢ ብለው ሸሽተው የመጡትን ክርስቲያኖች ፍለጋ ነበር፡፡ ኢየሉጣም ይህን በመስማቷ እጅግ በጣም ተረብሻ ቤቷን ዘግታ በፍርሃት ተውጣ ተቀምጣለች፡፡ የመኮንኑ ጭፍሮች ክርስቲያኖችን ፍለጋ በጠርሴስ አሰሳ ጀምረዋል፡፡ ኢየሉጣ በዚያ ቤት ውስጥ በፍርሃት ተቀምጣ ሳለ በሩ በድንገት ተንኳኳ፡፡

ኢየሉጣ ግን ተነሥታ ለመክፈት አልደፈረችም፡፡ ሉያንኳኩ የነበሩት ሰዎች በሩን በርግደው ገቡ፡፡ የእለእስክንድሮስ ጭፍሮች ነበሩ፤ ‹‹ተነሽ….ውጪ…..›› አለ አንደኛው ወታደር ፤ ከዙያም ይዘዋት እያንገላቱ ወደ መኮንኑ ወሰደዋት ፤ ለመኮንኑም የክርስቲያን ወገን እንደሆነች ነገሩት፡፡

መኮንኑም ‹‹ሴትዮ ተናገሪ ከወዳት ሕዜብ ነው የመጣሽው?….. ነገድሽስ ምንድን ነው? ሀገርሽስ ወዳት ነው?›› አላት፡፡ ኢየሉጣም ‹‹የአንጌቤን ሰው ነኝ ወገኖቼም ኤሳውሮሳውያን ናቸው፤እኔም በአንተ ምክንያት ሸሽቼ ነበር የወደዙህ የመጣሁት አነሆ ዚሬ ግን በእጅህ ውስጥ ነኝ›› አለችው፡፡ መኮንኑም ጏርነን ባለድምፅ ‹‹በእጄ ውስጥ እንደተገኘሽ ታውቂያለሽ አሁንም የማሸልሽን ምረሙ ስምሽን ተናጋሪ እኔንም እሺ በይኝና ለአማልክት ሠዊ›› አላት፡፡

‹‹ለረከሱ አማልዕክት እኔ አልሠማውም›› ብላ በድፍረት ተናገረች፡፡ ‹‹ለመሆኑ ስመሽ ማን ነው?›› ሲል መኮንኑ ጠየቃት ፤ እርሷም ‹‹የእኔ ስም ክርስቲያን መባል ነው›› አለችው፡፡ መኮንኑም መልሶ ‹‹ይህ ስንፍና ነው አይጠቅምሽም እንዳትሞቺ ስምሽን ተናገሪ›› አላት፡፡ የከበረች ኢየሉጣም ‹‹የኔ ስም ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞት የሚሽረው በሰዎች ዘንድ የምጠራበትን ከፈለግህ ስሜ ኢየሉጣ ነው›› ብላ መለሰችለት፡፡ መኮንኑም የቅድስት ኢየሉጣ አመላለስ በጣም አሰባጭቶት ‹‹ፅኑ የሆኑ ስቃዮችን በላይሽ ሳያመጡ ተነሥትሽ መሥዋዕትን ለአማልክት አቅርቢ›› አላት፡፡

ኢየሉጣም ‹‹እውነትን ለመሥራት የምትፈልግ ከሆነ የሦስት ዓመት ልጅ አለኝ እርሱን ፈልገው ያመጡ ዘንድ ጭፈሮችህን ላክ›› አለቸው፡፡ ያን ጊዜም መኮንት የሦስት ዓመት ልጅ ይፈልጉ ዘንድ ወታደሮችን ላከ የሀገር ሰዎችም ልጆቻቸውን ወታደሮች እንዳይገደለባቸው በመፍራት ደብቀዋልና አንዳችም ሕፃን አላገኙም፡፡ ከከተማው ቅጽር በፀሐይ መውጫ ወዳለው በረሃ ወጡ፤የቅድስት ኢየሉጣ ልጅ የሆነውን አንድ ሕፃን ልጅ አገኙት፡፡ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች ‹‹የስንት ዓመት ልጅ ነው›› ብለው ጠየቁቸው፡፡ ሰዎቹም ‹‹ይህ ሕፃን የሦስት ዓመት ልጅ ሲሆን ባሏ የሞተባት የክርስቲያናዊት ሴት ልጅ ነው›› አላቸው፡፡

ያንንም ሕፃን ይዘው ወደ መኯንኑ ወሰደት፡፡ መልኩ የሚያምርና ደም ግባት ያለው እንደሆነ መኮንኑም በአየው ጊዜ ‹‹ደስ የምትል አንተ ደስተኛ ሕፃን ሰላምታ ይገባሃል›› አለው፡፡ ‹‹ሕፃኑ እኔን ደስተኛ በማለትህ መልካም ተናገርክ አንተ ግን ደስታ የለህም እግዙአብሔር ለሚዘነጉ ለማይሰሙት ለማይቀበለት ደስታ የላቸውም›› ብል መለሰለት፡፡ መኮንኑም ሕፃኑን ‹‹ሳልጠይቅህ ይህንን ያህል ትመልስልኛለህን?›› አለው፡፡ ሕፃኑም ‹‹ገና ምን አይተህ ከዙህ የበዚ ነገር እመልስልሀለሁ›› አለው፡፡‹‹ስምህ ማነው?›› ሲል መኮንኑ ሕፃኑን ጠየቀው ‹‹ከንጹሕ አዘቅት እና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውኃ የተገኘ ሕፃን ስሜ ክርስቲያን መባል ነው›› ብል መለሰለት፡፡ መኮንኑም የእናትና የሕፃኑ መልስ አንድ መሆኑ በአንድ በኩል ገርሞታል በላላ በኩል ደግሞ አበሳጭቶታል፡፡ መኮንኑም በመቆጣት ‹‹ዳግመኛ እንዳትሞት ስምህን ንገረኝ አለው›› ቅስ ቂርቆስም ‹‹የከበረ ሕፃን ስሜ ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ መጠሪያ ስሜን የምትሻ ከሆነ እናቴ የሰየመችልኝ ስሜ ቂርቆስ የሚለው ነው›› አለው መኮንኑ ሕፃኑን ዜግ ባለ ድምጽ ‹‹እሺ በለኝ ለአማልክትም ሠዋ በስጋህ ስታድግ እሾምሀለሁ በብዙ ወርቅና ብርም አከብርሀለሁ›› ብል በተማጽኖ ቃል ሕፃኑን ሉያታል ጀመረ ፤ ሕፃኑም ‹‹የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠሎቷ የሆንክ ከኔ ራቅ›› አለው፡፡ መኮንኑም የልጁን ድፍረት ሰምቶ በጣም ተቆጣ ወታደሮቹንም ጠርቶ ሕፃኑን ወስደው እንዱያሠቃዩትና ያ ሲነኩት እንኳን እንደጥጥ የሚለሰልሱ ቆዳዎቹን ደሙ እንደ ውኃ እስከሚፈስ አስገረፈው ፤ የከበረች ኢየሉጣም የልጇን ትዕግሥት ባየች ጊዜ እግዙብሔርን አመሰገነች፡፡

እለእስክንድሮስ በተለያዩ ዓለማዊ ሀብት ለማታለል ቢሞክርም አለተሳካለትም ፤ የተለያየ ስቃይ እያደረሰባቸው እንኳን ለጣዖት አንሰግድም ስላለት ፤ በብረት ጋን ውስጥ ውኃ አፍልተው እንዱጥሏቸው አዘዘ፡፡ ጭፍሮቹም በትልቅ ጋን ውስጥ ውኃ አፍልተው አዘጋጁ ፤ የውኃው ፍላት እንደ ክረምት ነጎድጓድ በርኅቀት ላለ ሰዎች ሳይቀር ይሰማ ነበረ፡፡ ወታደሮቹም ሉከቷቸው ሲወስዶቸው ኢየሉጣ ልቧ በፍርሃት ታወከ ፤ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን ፍርሃቷ ይርቅላት ዘንድ ወደ እግዙአብሔር ይጸልይላት ነበረ ፤ እናቱንም ‹‹ሁለተኛ ሞት በሰማይ አያገኝንምና እናቴ ሆይ በርቺ ጨክኚ ፤ አናንያ አዚርያ ሚሳኤልን ያዳነ እኛንም ያድነናል›› አላት፡፡ ከዙህ በኋላ እሷም ጨክና በፍጹም ልቡ ሆነው ተያይዘው ወደ ፈላው ውኃ ገቡ ፤ ያን ጊዜ በማያምኑ ሰዎች ፊት በጽናት የመሠከሩለት የዓለሙ መድኃኒት ልዑል እግዙአብሔር ሐምሌ 19 ቀን አገልጋዩን የራማውን ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀለ እሳቱን አጥፍቶ የፈላውንና ውኃ አቀዜቅዝ አውጥቷቸዋል፡፡ ከውኃው በወጡም ጊዜ ልብሳቸው ሳይበሰብስ ሰውነታቸው ሳይሸበሸብ ታዩ ፤ በዚህም ምክንያት ከአሕዚብ (ከማያምኑ ሰዎች) ብዙዎች አምነው አንገታቸውን ለሠይፍ ፤ አካላቸውን ለእሳት ሰጥተዋል፡፡

መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም በረከትን እንደሚያገኝና ሌላ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው። ሲነጋ መኮንኑ ከመካነ ምኩናኑ ተቀምጦ ካለበት አስጠርቶ “የተመለስከው መመለስ አለን?” አለው:: ቅዱስ ቂርቆስም “አይሆንም አልመለስም” አለው:: ሰይፍ ጃግሬውን ጠርቶ “ንሳ ውደቅበት” አለው:: በሰይፍ መታው: ጌታም ነፍሱን ከመካነ ዕረፍት ሥጋውንም ነጥቆ በሰረገላ ኤልያስ አኑሮለታል:: እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም በማግስቱ (ጥር 16) በሰይፍ አስመትቷት በሰማዕትነት ዓርፋለች::