Get Mystery Box with random crypto!

#ጥር_7_ቅድስት_ሥላሴ_በሰናዖር_ምድር_ድንቅ_ተአምር_የፈጸሙበት_ዕለት_ነው፡፡ ከጥፋት ውሃ በኋ | ዝክረ ብሒለ አበው

#ጥር_7_ቅድስት_ሥላሴ_በሰናዖር_ምድር_ድንቅ_ተአምር_የፈጸሙበት_ዕለት_ነው፡፡

ከጥፋት ውሃ በኋላ የኖኅ ልጆች ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፡፡ በዚያም ጊዜ ምድር በአንድ ቋንቋ እና በአንድ ንግግር ነበረች፡፡ ዛሬ በምድራችን ያሉ ሰዎች የሚናገሩዋቸው የተለያዩ ቋንቋዎች ድሮ አልነበሩም ከዚያም ከምሥራቅ ተነስተው ሰናዖር በተባለ ቦታ አንድ ሰፊ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።

ብዙ ሥራዎችን ይሠሩ እና ይፈጥሩ ጀመር፡፡
ከነዚህም አንዱ ጡብ መሥራት ነበር፡፡ እርስ በርሳቸውም ‹ሳንሞት ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ› ብለው መክረው ታላቅ ግንብ ገነቡ፡፡

አለቃቸው ናምሩድ ይባላል! ‹‹ሞትን የሚያመጡብን ሥላሴ ናቸውና እነርሱን ወግተን ሞትን እናርቅ ›› ...አላቸው... ከዚያም ሆነው ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር ሰይጣን... ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል... እነርሱም ደሙን እያዩ ‹‹ አሁን አብን ወጋነው አሁን ወልድን ወጋነው ….›› ይሉ ጀመር ቅድስት ሥላሴ ምንም እንኳ ምህረታቸው የበዛ ቢሆንም በሕዝቡ ላይ ዲያብሎስ ስለሠለጠነባቸው .... እርስ በእርስ እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን ደበላለቁባቸው የማይግባቡ፣ የማይደማመጡ…… ሆነው ተበታትነዋል፡፡(ዘፍ.11:1-9)
ባለማስተዋል የሠሩትንም የአመጻ ሕንፃ  ነፋስ ጠራርጎ አጥፍቶታል፡፡ ይህን ያደረጉ ቅድስት ሥላሴ ስለሆኑ ጥር 7 በዓሉ ይከበራል ...

ሥልጣን ሁሉ የእግዚአብሔር መሆኑን እና በራስ ደካማ አመለካከት በመታበይ በሥላሴ ሥራ መግባት’ መጠራጠር ….. እንደሚጎዳ እንደዚሁም በጽኑ እምነት በመኖር እና በሥላሴ ስም የተጠመቅን ልጅነታችንን በኃጢአት ሳናሳድፍ በንስሐ ታጥበን እና በምግባር ጸንተን መጠበቅ እንደሚገባ የበዓሉ መልእክት ያስገነዝበናል፡፡ የአብርሐም ፣ የይስሀቅ ፣ የያዕቆብ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር በፈጠረው ሁሉ የተመሰገነ ይሁን!!!

ወ ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወ ለወላዲቱ ድንግል
ወ ለመስቀሉ ክቡር !
ይምሐረነ ወ ይስሀለነ በእንተ ርትዕት ሐይማኖት ያጽንአነ! ለይኩን! ለይኩን! ለይኩን