Get Mystery Box with random crypto!

#ቅዱሳት_ሥዕላት_በቤተክርስቲያን_ለምን_አስፈለጉ? ቅዱሳት ሥዕላት ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ መልእክት | ዝክረ ብሒለ አበው

#ቅዱሳት_ሥዕላት_በቤተክርስቲያን_ለምን_አስፈለጉ?

ቅዱሳት ሥዕላት ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡

የክርስትና አንደበት ናቸው፡፡

በመጀመያዎቹ ክርስቲያኖች ዘመን ቅዱሳት ሥዕላት ማስተማሪያ ነበሩ፡፡

ቅዱሳት ሥዕላት በጸሎት ጊዜ ሐሳባችንን ሰብስበን በእግዚአብሔር ፊት መቆማችንን አስበን እንድንጸልይ ይረዱናል፡፡

የእግዚአብሔር መገለጫዎች ናቸው፡፡
ለመንፈሳዊው የክርስትና መልእክት መገለጫ የሆኑት ቅዱሳት ሥዕላት ከዓለም ፎቶዎችና ምስሎች ይለያሉ፤ የእግዚአብሔር ኃይሉና ክብሩ ይገለጥባቸዋልና፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን የቅዱሳት ሥዕላት የአሣሣል ዘይቤና የኅብረ ቀለም ምርጫ ትውፊትን መሠረት ያደረገ ነው፡፡

የክርስትናው ትምህርት ማንፀባረቂያ በመሆናቸው ምሳሌዎችን በማመሳጠር ይሣላሉ፡፡

የሰማዕታት በቀይ ቀለም፣ የክርስቶስ በነጭ ቀለም፣ የድንግል ማርያም ነጭ፣ ሰማያዊ እና ቀይ በሆነ የቀለም ምርጫ ይሣላሉ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጋሻ አስይዞና ቅዱስ ሚካኤልን እግሩን አራቁቶ መሣል የቤተ ክርስቲያን ትውፊት አይደለም፡፡

በቤተ ክርስቲያን የሥዕላት አደራደር ክብርንና ምስጢርን መሠረት ያደረገ ነው፡፡

ከላይ፡- የሥላሴና የክርስቶስ ስቅለት
በግራ፡- የእመቤታችን ሥዕለ አድኖና የቅዱሳን መላእክት ሥዕል በቀኝ፡- የሐዋርያት፣ የዮሐንስ መጥምቅ፣ የቅዱሳንና የሰማዕታት በቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ የሰጎን እንቁላልና የመስቀል ምልክት ይደረጋል፡፡

 ቅዱሳት ሥዕላት የክርስትና ጥልቅ መልእክት ገላጮች ናቸው፡፡ በጸሎት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት መቆማችንን እንድናስተውል ይረዱናል፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሥዕላት አሣሣልና አቀማመጥ ትውፊትን መሠረት ያደረገ ነው፡፡

የሠራዊት አምላክ ሆይ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው፡፡ ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትናፍቃች፡፡” (መዝ.83÷1)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!