Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቅምት_14_ታላቁ_መናኝ_አቡነ_አረጋዊ_ወደ_ብሔረ_ሕያዋን_የገቡበት_ወይም_የተሰወሩበት_ዕለት_ነው | ዝክረ ብሒለ አበው

#ጥቅምት_14_ታላቁ_መናኝ_አቡነ_አረጋዊ_ወደ_ብሔረ_ሕያዋን_የገቡበት_ወይም_የተሰወሩበት_ዕለት_ነው።

¹ አቡነ አረጋዊ ከአባታቸው ይስሐቅ እና ከእናታቸው አድና በሮም ሀገር ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ይባላል፡፡ በዘመኑ የነበረውን መንፈሳዊ ትምህርት እየተማሩ አደጒ፡፡

¹ እድሜያቸው አሥራ አራት ዓመት ሲሞላ ቤተሰቦቻቸው ከነገሥታት ቤተሰብ ሚስት አጩላቸው፡፡  ነገር ግን አቡነ አረጋዊ ይህን ሲሰሙ ወደ ድርጌ (ግሪክ) ሀገር ኮበለሉ፡፡፡ ዳውናስ የሚባል ገዳም ገብተው መነኮሱ፡፡ አቡነ አረጋዊ እጅግ በጣም መንፈሳዊ ሰው ነበሩ፡፡ በሕይወታቸው እና ለመንፈሳዊ ሕይወት በነበራቸው ብዙዎችን ቅንዓት ወደ እግዚአብሔር መልሰዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ስማቸው አቡነ አረጋዊ ተባለ አረጋዊ ማለት ብልህ (አዋቂ) ማለት ነው፡፡

¹ ከዚህ በኋላ እናታቸው ንግሥት አድና ዜናቸውን ሰምታ አቡነ አረጋዊን ልትይጠይቃቸው ወደ አሉበት መጣች፡፡ ‹‹እናቴ ስለምን መጣሽ?›› ሲሉ ጠየቋት፡፡ እናታቸውም እርሳቸው የናቁትን ዓለም ንቃ እንደመጣች ነገረቻቸው፡፡

¹ አቡነ አረጋዊ በእናታቸው ውሳኔ በጣም ተደስተው፤ እናታቸው የምንኲስና ማእረግ እንዲቀበሉ እና በሴቶች ገዳም እንዲኖሩ አደረጒአቸው፡፡

¹ ከሰባት ዓመት በኋላ ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ የሀገራችንን የኢትዮጵያን ዜና ሰምተው ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡

¹ በብዙ ቦታዎች እያስተማሩና ሕሙማንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ የሚባል ስፍራ ደረሱ፡፡ ነገር ግን መውጫ የሌለው ረዥም ተራራ ስለነበር “አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ?” እያሉ ሲጨነቁ እግዚአብሔር ዘንዶ ተሸክሞ እንዲያወጣቸው አደረገ፡፡

¹ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔርን እያገለገሉ በጸሎትና በጾም ኖሩ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦላቸው፤ ሰማያዊ መንግሥትን እንደሚያወርሳቸው፣ በእርሳቸው አማላጅነት ለሚታመኑም የእርሳቸውን ጸጋ እና በረከት እንደሚያገኙ ቃል ገባላቸው፡፡

¹ አቡነ አረጋዊ ደቀ መዝሙሮቻቸውን ሰብስበው ‹‹ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም›› ብለው ነግረዋቸው ጥቅምት 14 በ99 ዓመታቸው ተሰወሩ፡፡

#እግዚአብሔር_በጸሎታቸው_ይማረን!!!