Get Mystery Box with random crypto!

ሰሙነ ትንሣኤ ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ያሉ ቀናት መጠሪያቸው የሚከተለውን ይመስላል፡፡ | ዝክረ ብሒለ አበው

ሰሙነ ትንሣኤ
ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ያሉ ቀናት
መጠሪያቸው የሚከተለውን ይመስላል፡፡
እሑድ፦ በዓለ ትንሣኤ ሲሆን ። ጌታችን
መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ሦስት ሌሊት
ሦስት መዓልት በከርሠ መቃብር አድሮ መነሳቱን
የምናስታውስበትና የመስቀል መርገምነቱ ቀርቶ
ትንሣኤነቱ የታወቀበት፤ ሙስና መቃብር
የተሻረበት ትንሣኤያችንን በትንሣኤው
ያረጋገጥንበት ዕለት ነው።
ሰኞ፦ ፩ኛ ማዕዶት ይባላል።
ማዕዶት ማለት (መሻገሪያ፣ መሻገር) ማለት
ነው። ምሳሌው ቀድሞ እስራኤላውያን ባሕረ
ኤርትራን ተሻግረው ምድረ ርስት ገብተዋል።
ምሳሌውም ፈርዖን የዲያብሎስ፣ ሠራዊቱ
የሠራዊተ ዲያብሎስ፣ ግብፅ የሲኦል፣ ባሕረ
ኤርትራ የባሕረ ሲኦል፣ እስራኤል የምእመናን፣
ሙሴ የወልደ እግዚአብሔር፣ በትረ ሙሴ
የመስቀል ምሳሌ እስራኤላውያን በሙሴ መሪነት
ተሻግረው ምድረ ርስት እንደገቡ ነፍሳትም
በክርስቶስ መሪነት ባሕረ ሲኦልን ተሻግረው ገነት
የመግባታቸው ምሳሌ ነው። በዚህም ማዕዶት
ይባላል።
፪ኛ ዕለተ አብርሃም (ዕለቱ ለአብርሃም) ይባላል።
አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ከነዓን ገብቷል።
በዚህም አንጻር ምእመናንም ባሕረ ሲኦልን
ተሻግረው ገነት የመግባታቸው ምሳሌ ነው።
አንድም አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ቢሄድ
መልከጼዴቅ ኅብስተ አኰቴት ጽዋዐ በረከት ይዞ
ተቀብሎታል። ነፍሳትም ባሕረ ሲኦልን ተሻግረው
ቢሄዱ ኅብስተ በረከት ጽዋዐ አኰቴት ወልድን
የማግኘታቸውና ወደ ቀድሞ የበረከት ርስት
የመመለሳቸው ምሳሌ ነው። ስለዚህ ትንቢቱ
ምሳሌው መድረሱን ለማጠየቅ ዕለቷ ማዕዶት
ትባላለች።
ማክሰኞ፦ ቶማስ ይባላል።
ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ የጌታችንን ጐን
የዳሰሰበትና እጁ የደረቀችበት እንደገና መልሳ
የዳነችበት መታሰቢያ ነው። ለቶማስ ታሪክ
መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ዕለቱ ቶማስ ይባላል።
ምንም እንኳን ታሪኩ የዳግማይ ትንሣኤ ቢሆንም
አበው ታሪክ ከታሪክ እንዳይደራረብ ብለው ነው።
ዩሐ20፤27-29
ረቡዕ፦ አልዓዛር ይባላል። ዮሐ ፲፩፥ ፵
አልዓዛር ጌታችን በጥንተ ስብከት ያስነሳው ሲሆን
ታሪኩ በዮሐንስ ወንጌል በሙሉነት ተመዝግቧል።
ከሞት የተነሳው መጋቢት ፲፯ ቀን ነው። በዚሁ ቀን
መታሰቢያ እንዳያደርጉለት የግርግር ወራት ሆነ
በ፳፪ም ሆሳዕና ሆነ፤ በ፳፫ም ርግመተ በለስ
አንጽሖ ቤተ መቅደስ ሆነ በዓሉ ከበዓል ይዋል
ብለው አበው የውኃ በዓል ከውኃ ብለው ቃና
ዘገሊላን ከጥምቀት ጥግ እንዳዋሉ ትንሣኤው
ከትንሣኤ ጋራ እንዲሄድ አደረጉ። አንድም
አልዓዛር በትንሣኤ ሥጋ እንደተነሣ እኛም ትንሣኤ
ልቡና፣ እንነሣለንና። ይቀጥላል . . .