Get Mystery Box with random crypto!

BBC አማርኛ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amaric — BBC አማርኛ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amaric — BBC አማርኛ
የሰርጥ አድራሻ: @bbc_amaric
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.65K
የሰርጥ መግለጫ

Broadcast & media production company
━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━
WELL COME
ቢቢሲ አማርኛ 🇪🇹
━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━
Verified official channel ®
@BBC_Amaric
https://t.me/joinchat/AAAAAE7S0z4ya9Z6ragluA

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-26 18:11:39
መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ጁንታው ጥቃቱን ቀጥሎበታል።

በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለጁንታው ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ ይወስዳል።

ስለሆነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የጁንታው ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል።

የመንግሥት ኮምንኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር።
@bbc_amharic1
634 views , 15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 11:01:07
"ዩኤስኤይድ በህወሓት የተፈጸመውን የነዳጅ ዘረፋ በጽኑ ያወግዛል"፦ ሳማንታ ፓወር

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) በህወሃት የተፈጸመውን የነዳጅ ዘረፋ በጽኑ እንደሚያወግዝ የድርጅቱ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ገለጹ።

ሳማንታ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአለም ምግብ ፕሮግራም 570 ሺህ ሊትር (ከ150 ሺህ ጋሎን በላይ) ነዳጅ በህወሓት መዘረፉና የእርዳታ ሰራተኞች ላይ እንግልት መድረሱን በጽኑ አውግዘዋል።

"ኢትዮጵያውያን ሲቪሎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው " ያሉት ሃላፊዋ ህወሓት የዘረፈውን ነዳጅ እንዲመልስ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችን እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

ከነዳጅ ዝርፊያ ጋር በተያያዘ ህወሓት ትናንት ማምሻውን በሰጠው ምላሽ " ከወራት በፊት ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ያበደርኩትን ነዳጅ መልሼ ወስድኩ እንጂ ዘረፋ አልፈጸምኩም " ብሏል።

ነዳጁን ለድርጅቱ ያበደርኩት ከጥቂት ወራት በፊት በነዳጅ እጥረት ምክንያት የምግብ እርዳታ ማከፋፈል ባለመቻሉ ነው ያለው ህወሓት፤ ድርጅቱ ነዳጅ መበደሩንና እንደሚመልስ ግንዛቤ ነበር።" ሲል ገልጿል። "ሥምምነታችን በጽሁፍ ተሰንዶ ተቀምጧል" ሲልም ህወሓት ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት እየቀረበበት ላለው ክስ ምላሽ ሰጥቷል። "ነዳጁ በመላው ትግራይ ለሚገኙና ጉዳት ለደረሰባቸው ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮች እና ሌሎች የጤና ተቋማት መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማስኬጃ ይውላል" ሲልም ገልጿል።

@bbc_amharic1
735 views , 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ