Get Mystery Box with random crypto!

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

የሰርጥ አድራሻ: @bahruteka
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.65K
የሰርጥ መግለጫ

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية
በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-17 22:30:44 የኢኽዋን መሪዮች የስልጣን ጥማት

የሀገራችን የኢኽዋን መሪዮች የስልጣን ጥማት በቀን ቁጭ ባሉበት እንዲቃዡ አድርጓቸዋል ። ቅዠቱ በርግጥ በውስጣቸው ሲያልሙት የነበረ መሆኑን ያመላክታል ። የእነዚህ አካላት የቀን ቅዠት ልክ እንደ አንድ በረንዳ አዳሪ ነው ። በቀን ጎዳና ላይ ቁጭ ብሎ እርጥብ እሳት እየበላ የምርቃና ሙቀት በሁለመናው ሲሰራጭ በምናቡ የመዋኛ ቦታ ፣ ሜዳ ቴኒስ ፣ የልጆች መጫወቻ ባለው በተንጣለለ ጊቢ ላይ በተሰራ ቪላ ውስጥ ራሱን አስቀምጦ በሐሴት ማእበል ሲናወጥ ምርቃናው እንደጠፋበት አምሳያ ነው ።
እነዚህ የሀገራችን የኢኽዋን መሪዮች ለስንት አመት ሲመኙት የነበረውን የመጅሊስ ስልጣን ላይ ሲወጡ የተሰማቸው ሙቀት የሰራ አካላታቸውን ሲቆጣጠረው ቁጭ ብለው የሀገር መሪ ሲሆኑ በቀን በተቀመጡበት በምናብ ዐለም ማየት ጀምረዋል ። የሚገርመው ይህ ሀዋእ ላይ የሚያንሳፍፋቸው ቅዠት ወደ መሬት ለማውረድ ቆርጠው ተነስተው ማስፈራራት ጀምረዋል ።
ሶሞኑን ሐረር ላይ በነበራቸው ጉባኤ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በሱ የስልጣን ግዛት ላይ እሱን የማይታዘዝ መኖር እንደማይችል ሲዝት ቅዠቱ እውነት መሆኑን አስረግጦ ተናግሯል ።
ሰለፍይ የሚባል ነገር መስማት እንደማይፈልግ በመግለፅ ሰለፍዮች ወደዱም ጠሉም በአሁኑ ሳአት እዚህ ሀገር ላይ ( ኢትዮዽያ ላይ ) የሙስሊሞች መንግስት እሱ መሆኑን አውጇል ።
ገርሞ ገርሞ ይገርማል ። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንደሚሉት ወይም ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ነው ነገሩ ። ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከዶ/ር አብይ አሕመድ ጋር የሙስሊሞች መሪ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የክርስቲያኖች መሪ ደግሞ ዶ/ር አብይ አሕመድ እንዲሆኑና ኢትዮዽያ በሁለት መንግስት እንድትመራ የተስማሙ ይመስል ራሱን በዚቹ ሀገር ላይ የሙስሊሞች መንግስት ነኝ ብሎ አረፈው ። ይህን የሐጂ የቀን ቅዠት በተለይ ኦሮምኛ የምትሰሙ በሚከተለው ሊንክ ገብታችሁ አድምጡ :–
https://drive.google.com/file/d/1VZSVRvGK0tOrUTiP4z7vJXz_Mx28Qqi4/view?usp=drivesdk

በዚህ ቅዠቱ ላይ በሚገርም መልኩ ሰለፍዮችን ያስፈራራል ውሀ ዝም ብሎ ሲሄድ የተኛ ይመስላል እንደሚበላ ሰው አያውቅም የሚል ምሳሌ አምጥቶ ዝም ስላልኩ የማላውቅ አይምሰላችሁ አጠፋችሇለሁ ይላል ።
እኛ የምንለው መጀመሪያ ዙፋኑን አረጋግጥና ከዛ በኋላ ዛቻውን አምጣ ነው ። አሁንም የምንለው አንተ የአንድ ተቋም መሪ እንጂ የሀገር መሪ አይደለህም ነው ። እንደሙስሊም በቁርኣንና በሐዲስ በሶሓቦች አረዳድ እንደ ሀገር ደግሞ በህገ መንግስቱ ነው የምንመራው ። አንተም እኛም በህገመንግስቱ እኩል ነን የኛ የመኖር ህልውና ባንተ መልካም ፈቃደኝነት ላይ የወደቀ አይደለም በዓለማቱ አስተዳዳሪ አላህ ፈቃድ ላይ ነው እንልሀለን ።
ከኢስላም ሊቃውንቶች ጥበበኛ ንግግር አንዱ " ልኩን ያወቀን አላህ ይዘንለት " የሚል ነው ።
ይህ የቀን ቅዠት በሱ ላይ ብቻ አላበቃም ዶ/ር ጀይላንም የአሕባሽ ሱፍይና ኢኽዋን ጥምር የሆነው የዑለማእ ፈታዋ ያልተቀበለ ኻሪጅይ ነው ( በመንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ የወጣ ) ነው ብሎ የጓደኛውን የማይጨበጥ ምናብ አጠናክሯል ።
የሐረሩ የኢኽዋኖች ጉባኤ በዚህ መልኩ በቀረርቶና ፉከራ እንዲሁም ሽለላ የዋለ ሲሆን በጊዜው ሁለት ግለሰቦች ሸይኽ ኢልያስ አባስና ሸይኽ አህመዴ ጨለንቆ የሚባሉ ምክንያታቸው እነርሱ የሚያውቁት ሲሆን በዚሁ ጉባኤ ላይ እኛ ከናንተ ጋር ነን ድሮም ከናንተ ጋር ነበርን ( የኦሮምኛ ግርድፍ ትርጉም ) ዑለሞችን ከሚሳደቡ አልነበርንም ይላሉ ። እነዚህ ሁለቱ ሸይኾች ከዚህ በፊት ሸይኽ ጣሃ ኸድር የሰለፍይ መሻኢኾች መሆናቸውን በመግለፅ አወድሷቸው ነበር ። በአሁኑ ጉባኤ ላይ ግን ከላይ እንደገለፅኩት ከሰለፍዮች እንዳልሆኑና ከኢኽዋኖቹ ጋር መሆናቸውን ድሮም ከሰለፍዮች እንዳልነበሩ ገልፀዋል ።
እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት እኛ ሰለፍዮች ሁለት አይነት መስፈሪያ የሌለን መሆኑን ነው ። መስፈሪያችን አንድ ነው እሱም የሰለፎች መዝሀብ ነው ። በወዳጅም በጠላትም ያው ነው ። ይህም ማለት ሰዎችን በዛሂራቸው ነው የምንኗራቸው ። የውስጣቸውን አላህ ነው የሚያውቀው ። እነዚህ ሁለቱ ሰዎች ከሰለፍዮች እንዳልሆኑና ከኢኽዋኖች እንደሆኑ ያውም ድሮም ጭምር ከኢኽዋኖች እንደነበሩ ገልፀዋል ። ይህንን ነው እኛ የምንቀበለው ። ከዚህ በፊት ዶ/ር ጀይላን የሱፍይ ልጅ ሱፍይ ነኝ ሲል እኛ ሱፍይ ነው አልን ከራሱ የሰማነውን መረጃ አድርገን ኢልያስ አሕመድ አይ ሱፍይ ነኝ ያለው አውቆ ነው ሰለፍይ ነው አለ አልተቀበልነውም ። ግለሰቡም አውቄ ነው እንደዛ ያልኩት ሰለፍይ ነኝ አላለም ። አሁንም እነዚህ ሁለት ሰዎች ድሮም ከኢኽዋን ጋር ነበሩ አሁንም ከኢኽዋኖች ጋር ናቸው እንላለን ።
አይ እኛ ዑዝር አለን ብለው የሚያቀርቡት ነገር ካለ ያኔ እናየዋለን ለአሁኑ ግን መስፈሪያችን አንድ ነው ። ሁለት መስፈሪያ የለንም በቡድንም በፈለጉት ላይ የሚፀድቅ መርህ የለንም ። ሸይኽ ጣሀም በጊዜው ባየው ነገር የሰጠው ምስክርነት አሁን ባየው ያስተካክለዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ።
በዚህ አጋጣሚ የሙነወር ልጅ የፃፈውን አንድ ወንድሜ አንብቦልኝ በጣም የገረመኝ የኢኽዋን መሪዮችን መንግስትነትና እነርሱን የተቃወመን ኻሪጅይነት አምኖበት ነው ይህን ትልቅ አጀንዳ ወደ ጎን ብሎ በሁለቱ ሰዎች ምክንያት ሸይኽ ጣሃን ለመወረፍ ይህን ያክል ትንፋሽ ያባከነው ።
የማይኖረውን የሚጮኸው የምነወር ልጅ ስንትና ስንት በመረጃ የቀረቡለትን እውነታዎች ለማድበስበስ የማይሆነው የማይሰራው የለም ። አቋሙን ከቀየረ በኋላ አንድም ቀን ሐቅን ተቀብሎ አይተነው ሰምተነው አናውቅም ። ይልቁንም ሐቅን በባጢል ስሌት ለማጣፋት ሲታትር እንጂ ። እኛ ግን በአላህ ፈቃድ ሐቅ በማንም ይነገር እንቀበላለን የሰለፍዮች መለያ ስለሆነ ከተሳሳትንም ተሳስተናል እንላለን ይህ ለኛ ክብር ነው ። በባጢል ለባጢል መወገን የስሜት ባልተቤቶች መለያ ነው ።
አላህ ሐቅን አውቀን የምንከተለውና ባጢልን አውቀን የምንርቀው ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka
6.3K views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-17 10:12:44 بقلم الشيخ محمد حياة – حفظه الله ورعاه –
ስለ ኢኽዋኖች ባህርይ ቀንጨብ የተደረገ በሸይኽ ሙሐመድ ሐያት ( አላህ ይጠብቃቸው )

https://t.me/bahruteka
5.3K viewsedited  07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-16 15:02:09 https://t.me/bahruteka mesael al jahiliya online ders

የመሳኢሉል ጃሂሊያ ኪታብ ደርስ ቀጥታ ስርጭት
ቦታ ፣ አል ኢስላሕ መድረሳ
ሳአት ፣ እሮብና ሐሙስ ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ

https://t.me/bahruteka
5.5K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-16 08:54:09 አይሁዳዊ ስልትና ተመዩዕ

የእነ ኢብኑ ሙነወር የጥብቅና ስልት

﴿أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِینَ أُوتُوا۟ نَصِیبࣰا مِّنَ ٱلۡكِتَـٰبِ یُؤۡمِنُونَ بِٱلۡجِبۡتِ وَٱلطَّـٰغُوتِ وَیَقُولُونَ لِلَّذِینَ كَفَرُوا۟ هَـٰۤؤُلَاۤءِ أَهۡدَىٰ مِنَ ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ سَبِیلًا * أُو۟لَـٰۤىِٕكَ ٱلَّذِینَ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُۖ وَمَن یَلۡعَنِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ نَصِیرًا﴾ [النساء ٥١-٥٢ ]

عَنْ قُتَيْلَةَ: " أَنَّ يَهُودِيًّا أَتَى النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: إِنَّكُمْ تُنَدِّدُونَ، وَإِنَّكُمْ تُشْرِكُونَ تَقُولُونَ: مَا شَاءَ اللَّهُ وَشِئْتَ، وَتَقُولُونَ: وَالْكَعْبَةِ.
فَأَمَرَهُمُ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا أَرَادُوا أَنْ يَحْلِفُوا أَنْ يَقُولُوا: وَرَبِّ الْكَعْبَةِ، وَيَقُولُونَ: مَا شَاءَ اللَّهُ، ثُمَّ شِئْتَ".
رواه النسائي (3773)، وصححه ابن حجر في "الإصابة" (14 /130–131)، والشيخ الألباني في "السلسلة الصحيحة" (1/263).

እውነትን ለፈለጋት ግልፅ ሆናለች።


ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

https://t.me/Abuhemewiya
5.3K views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-15 16:34:41 https://t.me/bahruteka mesael al jahiliya online ders

የመሳኢሉል ጃሂሊያ ኪታብ ደርስ ቀጥታ ስርጭት
ቦታ ፣ አል ኢስላሕ መድረሳ
ሳአት ፣ እሮብና ሐሙስ ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ

https://t.me/bahruteka
5.6K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-12 09:35:55 https://t.me/bahruteka al ajwibetul mufidah online ders
የአል አጅዊባ ኪታብ ደርስ ቀጥታ ስርጭት በየሳምንቱ እሁድ
ቦታ ፣ አል ኢስላሕ መድረሳ
ሳአት ፣ ከጠዋቱ 5 : 00 – 6 : 00
5.2K views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-10 21:37:27 የኢብኑ ሙነወሩ አቅለ-ደካማ ለሞጫጨረው የግፍ ፅሁፍ የተሰጠ አጠር ያለ ምላሽ!!! ▬▱▬▱➝ ➧ በመጀመሪያ ኢብኑ ሙነወርን ለመሻይኾች ያለው ጥላቻ ወይም ለምን ተነካሁ የሚለው እልህ ወይም የተመዩዕ ቫይረስ፦ ➧ የማስተዋል አቅሙን፤   ➧ የፍትህ መስመሩን እና     ➧ የረድ (የማስተካከያ አሰጣጡን) ዘግቶበታል ማለት ይቻላል! ➲ የሱና መሻይኾችን ለማጠልሸት የሚጥሩ አቅለ-ህሙማንን ሁሉ የመረጃ ምንጩ…
9.0K viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-09 14:09:29 https://t.me/bahruteka mesael al jahiliya online ders

የመሳኢሉል ጃሂሊያ ኪታብ ደርስ ቀጥታ ስርጭት
ቦታ ፣ አል ኢስላሕ መድረሳ
ሳአት ፣ እሮብና ሐሙስ ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ

https://t.me/bahruteka
6.6K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-09 07:16:19 ቡታጅራ ዶ/ር ሙሀመድ የሚባሉ (ክሊኒክ ያላቸዉ) ስለልጃቸዉ ሀኒፋ ሙሀመድ በአስቾካይ መስማት ያለባቸዉ ጉዳይ ስላለ ተባበሩን!

@DrKhedirMA
6.7K views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ