Get Mystery Box with random crypto!

.....የኛን ልብስ ለማልበስ እሱ እንደወይንጠማቂ ልብሱን በደም ነከረ .....እኛን የልጅነት አ | Top 6👭👭👭

.....የኛን ልብስ ለማልበስ እሱ እንደወይንጠማቂ ልብሱን በደም ነከረ
.....እኛን የልጅነት አክሊል ሊያጎናጽፈን እሱ የእሾህ አክሊል ደፋ
.....እኛ የታመምነውን ህመም ለመሻር ሲል የኛን ስጋ ለብሶ ታመመ ቃተተ ተሰቃየ
.....እኛዲያቢሎስ ከሰቀለን የሀጥያት መስቀል ላይ ለማውረድ መስቀል ላይ ተሰቀለ
......እኛን የልጅነት ክብር ለማልበስ ሲል እሱ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ በፈጠረው ፍጡር ተዋረደ
.....እሱ ለኛ ሲል ክብሩን ትቶ እኛ ግን ለልብሳችን እንሳሳለን
.....እሱ ለኛ ሲል መሬት ለመሬት ሲቃትት ሲገፋ እና ሲወድቅ እኛ ግን ለክብሩ የሚሆን ስግደት ለመስገድ ለጉልበታችን ሳሳን
.....እሱ አፈር ለብሶ እኛን አክብሮን እኛ ግን ለእግራችን አፈር ለሚበሰብስ ስጋችን ስግደትን ነፈግነው
.....እኛ የእግዚአብሔር ጠላት ሆነን ሳለ፡ በባህሪ ልጁ ሞት ታረቀን
.....የሆሳዕና ዕለት 'ሆሳዕና በአርያም' እያልን ዘምረን አመስግነን በዛች በስቃይ ቀን በስቅለት ቀን ግን ሁላችንንም እንደመጻጉዕ ካድነው

ግን እሱ.......ግን እሱ መሀሪ ነውና በሞቱ ሞታችንን ሻረልን


#እኛ_እና_እሱ