Get Mystery Box with random crypto!

✞✞✞ ታኦሎጎስ✞✞✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ astemro — ✞✞✞ ታኦሎጎስ✞✞✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ astemro — ✞✞✞ ታኦሎጎስ✞✞✞
የሰርጥ አድራሻ: @astemro
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 918
የሰርጥ መግለጫ

ውድ የክርስቶስ የእናቱ የእመ አምላክ ቤተሰቦች እንኳን ደህና መጡ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን አስተምህሮ ከአባቶቻችን አበው የተሰጡትን አስተምህሮት ይከታተላሉ ዘንድ ጋብዤዎታለሁ። ለወዳጆቹ በማስተላለፍ የተዋህዶን አስተምህሮ ለአለም ያድርሱ ስል በፈጣሪ ስም መንፈሳዊ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
ሃሳብ አስተያየት ለመስጠት ጥያቄ ካሎት ለማድረስ እንዲነሳ ምትፈልጉትን ሃሳብ ለመስጠት
@betetewahido

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-04 20:14:28
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አርፈዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የቅዱስነታቸውን ሽኝት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ተሰብስቦ በሚያስተላልፈው ውሳኔና በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበሩ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
477 views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 20:47:03
550 views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 06:46:15 በመቀጠልም ከ1245-1268 ዓ.ም ለ23 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በዐጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሳሳቢነት ታቦታቱ በባሕረ ጥምቀት ሲውሉ ምእመናን በታላቅ ድምቀት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እንዲውሉ መንፈሳዊ ዐዋጅ አሳወጁ በማለት ገልጸዋል፡፡

በመቀጠል ከ1426-1460 ዓ.ም ለ34 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በታላቁ ንጉሥ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥትም ንጉሡ ከሊቃውንት ጋር በመወያየት የበዐሉን ታሪክ ተከትሎ ታቦታቱ ጥር 10 ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት እንዲወርዱና ጥር 11 እንዲመለሱ መወሰኑን ሊቀ ትጉኃን ኀይለ ጊዮርጊስ ይተነትናሉ።

እንደሚታወቀው ታቦተ ጽዮን በሄደችበት ሁሉ በረከትን ትሰጥ እንደነበር የአቢዳራን ቤት በበረከት እንደሞላች፤ የዮርዳኖስን ባህር እንደከፈለች፣ የኢያሪኮን ቅጽር እንዳፈረሰች፣ የፍልስጤማውያን ጣዖት ዳጎንን ቀጥቅጣ እንዳጠፋች ሀገሪቱ ትባረክ ዘንድ ርኲሳን መናፍስት ይርቁ ዘንድ ምድሪቱ በቃል ኪዳኑ ታቦታት ትቀደስ ዘንድ ታቦታቱ በመጡበት መንገድ እንዳይመለሱ ታላቅ ዐዋጅ አሳውጀው በዐዋጁ መሠረት ዛሬ ድረስ በደመቀ መልኩ በዓሉ እየተከበረ ይገኛል ብለው ታሪካዊ ዳራውን ጽፈዋል፡፡

ከባሕር ማዶ ጸሐፍያን ውስጥ ቼሩሊ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ቁመቱ 14 ወርዱ 8 ክንድ የኾነ ባሕረ ጥምቀት እንደተዘጋጀ ሲጽፍ፤ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐጼ ልብነ ድንግል በተገኙበት እጅግ ታላቅ ድንኳን በባሕረ ጥምቀቱ ዙሪያ እንዴት ተተክሎ እንደተከበረ ፍራንቺስኮ አልቫሬዝ ገልጿል፤ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረውን የበዓለ ጥምቀት አከባበር ደግሞ ፔድሮ ፔየዝ ዘግቦት ነበር።

አሁን ባለንበት ጊዜም ዳዊት በመዝ 44፡16 ላይ “በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ” በማለት እንደተናገረ ከመቼውም በበለጠ እግዚአብሔር የወጣቱን ልብ በረድኤት ጎብኝቶት "አልፋ ወዖ ቤጣ የውጣ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወወልደ ማርያም ሥግው" ተብሎ ሕይወት የሆነው የአምላካችን የኢየሱስ ስም ለተጻፈበት ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ለሚሠዋበት ለቃል ኪዳኑ ታቦታት ክብር አካባቢውን እያስዋበ፣ ታቦታቱ የሚሄዱበትን መንገድ እየጠረገ፤ ታላላቅ ምንጣፎችን ታቦታቱ በሚሄዱበት መንገድ እያነጠፈ ለቃል ኪዳኑ ታቦት እንደ ነቢዩ ዳዊት ከፍተኛ ክብር በመስጠት እግዚአብሔርን እያገለገለ ይገኛል (1ኛ ነገሥት 6፡1-23)፡፡

“የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት” (ኢያ 3፡3)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ]
የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Rodas9
የYoutube Channel:- https://youtube.com/channel/UCFKnpmDyWe3LQ_9Gx3TMnAg
683 views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 06:46:14 [እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ጥምቀት ማለት ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውሃ ውስጥ ገብቶ መውጣት” ማለት ነው፡፡

ምስጢረ ጥምቀትን የመሰረተልን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ሲመሠርትም በማዘዝ ብቻ ሳይሆን በሥራ በማሳየት ጭምር ነው (ማቴ 3፡17፤ ማር 1፡9፤ ሉቃ 3፡21፤ ዮሐ 1፡31)፡፡

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እከብር አይል ክቡር የባሕርይ አምላክ ሆኖ ሳለ በዮርዳኖስ ወንዝ በአገልጋዩ (በፍጡሩ) በዮሐንስ የተጠመቀበት ምክንያት፦
1) አንድነቱን ሦስትነቱን ለመግለጽ
2) የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ (ቆላ 2:14)
3) በእርሱ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት ለመቀደስ
4)ለጥምቀታችን ኀይልን ለመስጠት
5) ለአብነት ርሱ ተጠምቆ እናንተም ተጠመቁ ብሎ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በ30 ዘመኑ ጥር 11 ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት፤ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ እንደሚጠመቅና የዮርዳኖስ ወንዝ ጌታን ስታይ እንደምትሸሽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 113፡3-5፦ “ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ፤ ተራሮች እንደ ኮርማዎች፥ ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ፤ አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ ምን ሆናችኋል?” በማለት ከ1000 ዓመት አስቀድሞ ትንቢት የተናገረ ሲሆን፤ ብዙ ምሳሌም አለውና ከትርጓሜ ወንጌል ይመልከቱ፨

ዮሐንስ ወደ ጌታችን መምጣት ሲገባው ጌታችን ወደ ዮሐንስ የሄደበት ምክንያት የመጀመሪያው ትሕትናን ለማስተማር ነው።
ሁለተኛው ለአብነት ለምሳሌ ነው፤ ይኸውም ዮሐንስ ሄዶ አጥምቆት ቢሆን ዛሬ ባለሥልጣናቱ ካህናትን ቤታችን ድረስ መጥታችሁ አጥምቁን ይሏቸው ነበርና ሰማያዊ ንጉሥ እኔ ከሄድኩ እናንተም ሄዳችሁ ቤተ ክርስቲያን ተጠመቁ ለማለት ሄዷል።

ዮሐንስ ግን ወደርሱ በትሕትና የመጣው አምላኩ ክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ሲል ጌታችንም “ጽድቅን ልንፈጽም” ይገባናል ብሎ ትንቢተ ነቢያትን ሊፈጽም እንደመጣ ሲነግረው ዮሐንስ እሺ አለ።

ከዚያም ተያይዘው ወደ ዮርዳኖስ ሲወርዱ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት የዮርዳኖስ ወንዝ ወደ ኋላዋ ሸሽታለች በዚህም ዳዊት በመዝ 77፡16 ላይ፦
“አቤቱ፥ ውሆች አዩህ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውሆችም ጮኹ” ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ።

ጌታችንም ተጠምቆ ከውሃው ከወጣ በኋላ ሰማይ ተከፈተ ይላል። መተርጉሙ ሲያመሰጥረው፦
1) "ከመ ተጠምቀ ሰማያዊ ናሁ ወረደ እምሰማይ ወሀለዎ ከመ ይዕርግ ውስተ ሰማይ" (ሰማያዊው እንደተጠመቀ ከሰማይ እንደወረደ ወደሰማይ እንደሚያርግ ለማስረዳት)

2) "ወዳግም እስመ አናቅጸ ሰማያት ተዐጽዉ በምክንያተ ዕልወተ አዳም ..." (በአዳምና በሰዎች በደል ምክንያት የሰማያት ደጆች ተዘግተው ነበር። ገነትም ተዘግታ በእሳት ጦር ትጠበቅ ነበር። ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ በጥምቀቱ ምክንያት የሰማይ ደጃፎች ተከፈቱ)።

3) "ሣልስ ያጠይቀነ ከመ እለ ይጠመቁ ይትረኃው ሎሙ አናቅጸ ሰማያት ..." (ለሚጠመቁ ሰዎች የሰማያት ደጃፎች እንደሚከፈቱላቸውና ከሞት ከተነሡ በኋላ ወደ ሰማይ እንደሚወጡ ያስረዳል)።

4) ሰማያት ተከፈቱ መባሉ ደጃፍ በተከፈተ ጊዜ በውስጥ ያለው ዐዲስ ነገር እንዲገለጥ በጥምቀትም ዐዲስ ምስጢር ይገለጣልና ነው።

አብ በሰማይ ኹኖ “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ዘቦቱ ሠመርኩ” (በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው) ብሎ ሲመሰክር፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስም በጽንፈ ዮርዳኖስ ቁሞ ታየ፡፡

መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ለምን ወረደ? ቢባል
ርግብ ኀዳጊተ በቀል (በቀልን የምትተው) ናት፤ መንፈስ ቅዱስም ኀዳጌ በቀል፤ ቸር ነኝ ሲል፡፡
ርግብ ልጆቿን ተከባክባ እንድታሳድግ፤ መንፈስ ቅዱስም ለምእመናን ልሕቀት መንፈሳዊ እሰጣለኊ ሲል፡፡
የርግብ ዐይኑ ነጩም ጥቁሩም ያያል አይከፈልበትም፤ መንፈስ ቅዱስም ዕውቀት ሥልጣን አይከፈልብኝም ሲል፡፡
ርግብ በኖኅ ጊዜ የጥፋት ውሃ መጒደሉን የወይራ ቅርንጫፍ ይዛ ብሥራተ ፍሥሐ የምሥራችን እንደገለጸች፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በመውረድ ከርሱ ጋር የሥልጣን አንድነት ባለው በወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በመውረድ የፍዳ ዘመን ማክተሙን ተስፋ መስቀልን አብሥሯል፡፡
ርግብ ክንፏን ቢመቷት፤ ዕንቊላሏን ቢሠብሩባትም ቤቷን ካላፈረሱባት በቀር አትኼድም፤ መንፈስ ቅዱስም ምንም ኀጢአትን ቢሠራም፤ ጨርሰው ካልካዱት በስተቀር አይለይምና፡፡

ይኸውም በምስጢረ ሥላሴ ትምህርት እንደምንረዳው ከሰማይ ኾኖ የመሰከረው ክርስቶስ በቃልነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ያሉበት (ሕልው የኾኑበት) አብ ነው።
ወርዶ በወልድ ራስ የተቀመጠው አብ በልቡናነት ክርስቶስ በቃልነት ሕልው የኾኑበት መንፈስ ቅዱስ ነው። በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ የታየው አብ በልቡናነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ሕልው የኾኑበት አካላዊ ቃል ክርስቶስ ነው፤ እንዲኽ አድርገው የአካል ሦስትነታቸውን የፈቃድ አንድነታቸውን ለማስረዳት አብ በደመና ኾኖ መሰከረ፤ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ታየ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ ታየ።

በዚኽም የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሚገባ ሲታወቅ በተጨማሪም “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ እግዚአብሔር አብ በመመስከሩ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው በኋለኛው ዘመን ከእመቤታችን ያለ አባት በኅቱም ድንግልና የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ብቻ መኾኑ በሚገባ ተረጋግጧል፤ ዕለቱም በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋንያ ሲባል በግእዝ አስተርእዮ በዐማርኛም የመታየት የመገለጥ ጊዜ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን ስለ ነገረ ጥምቀት የሰማችው ከሌላው ዓለም አስቀድማ ጌታችን ባረገ በጥቂት ወራት (በ34 ዓ.ም) በኢትዮጵያው ጀንደረባ አማካይነት ነው (የሐዋ 8፥26-39)፤ ይህም በዐል ከዘጠኙ ዐበይት በዐላት አንደኛው ሲሆን ጌታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ስላመራ ይህንን ለማሰብ ታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ያመራሉ።

በዚህ መልኩ መከበር እንዴት ተጀመረ? የሚለውን ሊቀ ትጉኃን ኃይለ ጊዮርጊስ በጻፉት የነገረ ሃይማኖት መጽሐፍ ላይ የጻፉትን ለአንባብያን ለማካፈል ወደድኩ። ይኸውም ከ515-529 ዓ.ም ለ14 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በአጼ ገብረ መስቀል ዘመን ሲሆን በጊዜው ቅዱስ ያሬድ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ ከዝማሬው በመነሣት ታቦታቱ ጥር 11 ጠዋት ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ አምርተው አመሻሹ ላይ ይመለሱ ነበር ብለዋል፡፡

ከዚያም ከ1157-1197 ዓ.ም ድረስ ለ40 ዓመት ኢትዮጵያን በመራው በታላቱ ጻድቅ ንጉሥ በላሊበላ ዘመን በአንድ አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስትያናት ታቦታቱ ባንድ ላይ እንዲያከብሩ ንጉሥ ላሊበላ ታላቅ መንፈሳዊ ዐዋጅን አሳውጆ በአንድ አካባቢ፣ ወረዳ፣ ያሉ በአንድ ላይ ማክበር ጀመሩ፤ በርሱ ዘመን የነበሩት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በጎንደር፣ በሸዋ፣ በአንኮበር፣ በመርጡለ ማርያም እየሄዱ ባሕረ ጥምቀቱን እንደባረኩ ይጽፋሉ፡፡
454 views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 06:45:19 ታኦሎጎስ(ነባቤ መለኮት) ዮሐንስ የጀመረው የነገረ መለኮት ጥናት ይህንን ባህር ከመጭለፍ ጋር የተመሳሰለው ለሰው አረዳድ እንጂ ምሳሌው ሙሉ ሆኖ አይደለም።
https://t.me/+V8zdhrOXFxQlWeX8
516 views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 06:42:45 Channel photo updated
03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 06:02:02 https://t.me/+jrytdA4vD8pjM2E0
384 views03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 20:01:38 Channel photo updated
17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 19:57:49
399 views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-06 06:29:21 "ወዳጄ ሆይ ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው በጌታችን እራስ ላይ እሾህ እዳቀዳጁት ባሰብህ ጊዜ እጅግ ማዘንህ አይቀርም ። ሆኖም አንተም እሾህ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሰራህ ቁጥር በጌታችን ላይ የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ ።በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን ወታደሮች ከጎነጎኑት እሾኽ በላይ የጌታችንን እራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው ደሙን አፍስሶ ያዳነን እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን የምንጎነጉነው የእሾኽ አክሊል ነው ።{ስለመተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል ።!}

{በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ከሚለው ርዕስ የተወሰደ )

[ ሕማማት]
{በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ}
:
መድኃኔዓለም ሆይ አባት ሆይ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ፥ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህን በጦር በወጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ ።
መድኃኔዓለም ሆይ ጻድቃንን ያይደለ ኃጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ስነ መልክህ ሰላም እላለሁ !
( መልክአ - መድኃኔአለም )27
https://t.me/+V8zdhrOXFxQlWeX8
650 views03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ