Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 18/08/2014 ዓ.ም ወደ ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2014 ዓ.ም አዲስ | Assosa online

ቀን 18/08/2014 ዓ.ም
ወደ ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2014 ዓ.ም አዲስ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ-ምረቃ መርሃ ግብር በ2014 ዓ.ም የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያው ቀን በሚከተለው መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
 ምዝገባው የሚከናወንበት ቀን ሚያዚያ 28 ና 29/2014 ዓ.ም ሲሆን
 ገለፃ የሚሰጥበት ቀን ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ
 እንዲሁም ትምህርት የሚጀመርበት ቀን እና በቅጣት የመመዝገቢያ ቀን ግንቦት 01/2014 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን
አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ ለምዝገባ በምትመጡበት ወቅት መርሳት የሌለባችሁ፡
1) የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን
• የ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሰርተፍኬት
• ከ 9ኛ-12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪፕት
2) 4 ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶ ግራፍ
3) አንሶላ፣የትራስ ጨርቅ እና ብርድ ልብስ
4) የስፖርት ልብስና ጫማ
ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳወቅን ከላይ ከተጠቀሱት የመመዝገቢያ ቀናት ውጪ ቀድሞም ይሁን ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲዎቹ የማያስተናግዱ መሆኑን አበክረው ይገልፃሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡ የዩኒቨርሲቲ ምደባችሁን ለማወቅ የሁለቱን ዩኒቨርሲቲዎች ድህረ ገፅ (www.aastu.edu.et or www.astu.edu.et) መመልከት ትችላላችሁ፡፡
በዩኒቨርሲቲው በኩል የሚተላለፉ ሌሎች መረጃዎችን በዩኒቨርሰቲው መገናኛ ዘዴዎች የምንገልፅ በመሆኑ አባል በመሆን ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

t.me/asosaonline/666

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት