Get Mystery Box with random crypto!

የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ ሚያዝያ 17/2014 ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል | Assosa online

የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

ሚያዝያ 17/2014 ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ አደረገ።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር ዐቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ለማየት በድረ ገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ ነው የተባለው።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድረ ገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢውን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርኃ ግብር የሚያሳውቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ በፊት በተገለጸው የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል።