Get Mystery Box with random crypto!

★★ናቲ ና ሜሪ★★ ክፍል-32 | ኤሽ ጣፋጭ ታሪኮች

★★ናቲ ና ሜሪ★★

ክፍል-32




፠ ሄሎ ናቲ

፠ እንዴት ነሽ ጄሪዬ

፠ አለው እ/ር ይመስገን ምን እሆናለሁ

፠ ምንም አትሁኝብኝ። እኔ ግን life በጣም አይሆኑ ነገር እየሆነብኝ ነው። በጣም ከምታስቢው በላይ እየተረበሽኩ ነው። አንቺን ማስከፋቴ ምዬ መካዴ ሁሉ ተደርቦብኝ በጣም ተረብሻለሁ!!
እባክሽን ስለ ሁሉም ነገር ይቅርታ አድርጊልኝ

፠ ናቲ እኔ ይቅርታ አርጌልሀለሁ ብዬ ልዋሽህ እችላለሁ ግን እመነኝ ከልቤ በፍፁም ይቅር ልልህ አልችልም!! 3 አመት አብሮኝ ከኖረው ባሌ አንተ በ5 ወር ወስጥ ያደረከኝ ይብሳል። ናቲ አንተን በፍፁም ይቀር ልልህ አልችልም!!

፠ ሰው የ እናቱን ገዳይ እንኳ ይቅር ይል የለ እንዴ?

፠ ናቲ ዛሬ ይምታል የቅር ካላልሽው ብባል እንኳን አላደርገውም!!

፠ ቢያንስ በደንብ አስቢበት

፠ ምንም የማስበው ነገር የለም በፍፁም ይቅር ልልህ አልችልም አትደውል ከቻልክ?

ናቲ የጄሪ መልስ ካደረጋት ነገር አንፃር ቢያንስበት እንጂ አይበዛባትም እንደውም ያንን ሁሉ አድርጓት አንድም ክፉ ነገር አለመናገሯን እጅግ በጣም እንዲያከብራት አድርጎታል። ይቅርታዋን ባለማግኘቱ ግን መከፋቱ አልቀረም።

ሆሆ ሰው የዘራውን ያጭዳል ሲባል ሽንት እንዳሸተተ በግ እኝ ብዬ እንዳልሳቅኩ ዛሬ ... የናቅኩት ክፋቴ እንደ ዳዊት ግንባሬን ብሎ ሊጥለኝ መሆኑን ሳስበው እውነትም የዘሩትን..... አሰኝቶኛል።

★ሜሪ★

ከሜሪ ጋር ያለን ነገር እንደተለመደው አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል። የምትፈልገውን ሁሉ በኩርፊያ ለማግኘት መምከሯ የእለት እለት ተግባሯ መሆን ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል።

፠ ናቲ ካፌ እንቀመጥ

፠ እረ እኔ እኮ በጣም ነው ሚደብረኝ

፠ ለነገሩ አንተ እኮ ከኔ ጋር ......

ሳትጨርሰው "እሺ እንቀመጥ" ይላታል አለበለዚያ የሚጀመረው ጦርነት እንኳን በናቲ አቅም በመከላከያ ጣልቃ ገብነት እንኳ መብረድ የሚቻለው እንዳልሆነ ልቡ ያውቀዋል። ምን አለፋቹ ናቲሻ ድሮ ደረቱን ነፍቶ ከጠዋት እስከማታ የራሱን ፍላጎት ብቻ ሲከተል እንዳልኖረ ዛሬ ባጠፋው ከባድ ጥፋት የተነሳ የተባለውን ሁሉ ለማድረግ " ለነገሩ ...." ማለት ብቻ በቂ ነው። ይኸው ካፌ መቀመጥ የማይወደው ልጅ በአለቃው ምክንያት መዋያቸው ከሆነ ቆይቷል። በፍፁም እንዲከፋት ስለማይፈልግ እንደወሰለተባት እንዳታስብ የሚኖርለትን ክብሩን ጭምር ጣል አድርጎ የምትፈልገውን ሁሉ በማድረግ ተጠምዷል።

ይህን ያህልም ተቀይሬላት እንደምወዳት ለማሳመን በቂ አልነበረም። አሁንም ጄሪ ጋር የሄድኩት መወስለት አምሮኝ እንደሆነ በማሰብ የጥያቄ ናዳ ታወርድብኛለች።

፠ የምትወደኝ ቢሆን 10 አመት ቢፈጅም ትጠብቀኝ ነበር

፠ ሜሪዬ ለስራ አሜሪካ ልሄድ ነው እኮ አይደለም ያልሽኝ? ላገባ ነው ተወኝ ብለሺኝ ምን ተስፋ አርጌ ነው ልጠብቅሽ የምችለው?

፠ ቢሆንም ..........

በሂወቴ እንደ ጭቅጭቅ እና ልምምጥ የምጠላው ነገር በፍፁም ኖሮ አያውቅም። ሜሪን እንዳፈቀርኳት በጣም የሚገባኝም ጭቅጭቋን ከመቻሌ ባሻገር ስታኮርፍ እስከ ጥግ ድረስ የምለማመጣት ነገር ኦኦኦ.... እውነትም ላፈቀሩት ሰው እያስባለኝ መጥቷል።

በዚህ ሳመልጥ በዚያ በዚህ ስሮጥ በወዲያ እየመለሰችኝ እሷም ማኩረፏ ላይ እኔም አዲሱ በሀሪዬ መለማመጤ ላይ ተጣብቄ እዚህ ደርሰናል። በጣም እንደምትወደኝ የእውነት ሁሉም ነገሯ ምስክር ነው ቅንጣት እንኳ በፍቅሯ ጥርጣሬ የለኝም ግን ምን ዋጋ አለው የዋህነቷ የመከራትን ሁላ መስማቷ እኔን ለመከራ ሰጥቶኝ እሷንም በጥርጣሬ እንድትቃጠል አድርጓታል።

ነገ በአካል ለመገናኘት ተቀጣጥረን ሁለታችንም ለመገናኘት ልባችን ቆሟል።

ሜሪ.....

፠ ሄሎ ሜሪዬ

፠ ወዬ ናቲዬ

፠ ነገ ስንት ሰአት ነው የምትመጣው?

፠ በጠዋት ነዋ

፠ እሺ የኔ ፍቅር ፀጉር ቤት ልሂድ በቃ ቻው ቻው...

እጅግ በጣም ደስ ብሏታል ለነገሩ በስልክ ከምናወራው ይልቅ በአካል ለማስረዳቱም ለምኑም ይሻላል።

★ጠዋት★

ናቲ ከመድረሱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ደውሎ አሳውቋት ስለነበር ብዙም ሳትዘገይ ያለበት ቦታ ደረሰች። የሌለ እምር ብሎባታል ልክ ናቲን ስታየው የምትሆነው የሆነ ነገር አለ እሱ ብቻ የሚረዳው። መርበትበት አይሉት መደናገር መበርገግ አይሉት..... ብቻ ናቲ ይሄን ስሜቷን ይወደዋል ሳይሆን ያመልከዋል ቢባል ይቀላል። አይን አይኗን እያያት እንቅ አርጎ ከንፈሯን ግምጥ አደርጓ ሳማት እየተላፉ የባጥ የቆጡን እያወሩ ወደሚይዙት ክፍል አመሩ።

ከመንገድ እንደመምጣቱ ሻውር ለመውሰድ እየተጣደፈ ገባ። ተጣጥቦ ሲመለስ ሜሪ አልጋ ላይ ተቀምጣ ሲያያት ትግስቱን አጣ ዘሎ እንደመዥገር እላይዋ ላይ ተጣበቀባት። እንደተለመደው ሁሉንም ነገር ካደረጉ በሃላ ተያይዘው ከክፍሉ ወጡ።

ጠዋት የወጡ በሚገርም ፍቅር በተሞላበት ሁኔታ ውለው ማታ እያሽካኩ ወደያዝዋት ክፍል ተመለሱ።