Get Mystery Box with random crypto!

በብሔራዊ ባንክ ዕውቅና የተነፈገው ክሪፕቶከረንሲ እና የኢትዮጲያ ተጠቃሚዎች ብሄራዊ ባንክ በክሪፕ | @ArtsTvWorld - Arts TV - አርትስ ቲቪ

በብሔራዊ ባንክ ዕውቅና የተነፈገው ክሪፕቶከረንሲ እና የኢትዮጲያ ተጠቃሚዎች
ብሄራዊ ባንክ በክሪፕቶከረንሲ ወይም ምናባዊ ገንዘብን ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በብሄራዊ ባንክ እውቅና ያልተሰጠው ህገወጥ ድርጊት መሆኑን ትናንት በመግለጫው አስታወቀ
ብሄራዊ ባንክ የክሪፕቶከረንሲ፣ ቢትኮይን እና የመሳሰሉት የምናባዊ ገንዘብ ወይም ቨርችዋል አሴት አገልግሎት በሃገራችን እየተስፋፋ መምጣቱንም በመግለጫው አስፍሯል።
ይህንን ተከትሎም ከብሄራዊ ባንክ እውቅና ውጭ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት እና በተለይም በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት መቻሉን ብሄራዊ ባንክ ገልጿል።
አርትስ ቲቪ ያነጋገራቸው ግለሰቦች ከዚህ በፊት እንደ ቢትኮይን ያሉ የማይዳሰሱ ዲጂታል ገንዘብን በተለያዩ ባንኮች ከሃገር ውጭ በሚገኙ ሰዎች በዌስተርን ዩኒየን አማካኝነት የገንዘብ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ገልጸውልናል።
የብሄራዊ ባንኩ በደነገጋቸው የብሄራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 እንዲሁም በ በክፍያ አዋጅ ቁጥር 718/2003 በብሄራዊ ባንክ በሌላ አኳኋን ካልተፈቀደ በስተቀር ማንኛውም የገንዘብ ኝኙነቶች በብር እንደሚሆን እና ያለ ብሄራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት እንደማይቻል አስቀምጧል።
ብሄራዊ ባንኩ ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጾ ህብረተሰቡ ከመሰል ተግባሮች እንዲቆጠቡ በመግለጫው አስፍረዋል።
ክሪፕቶከረንሲ በኦንላይን ብቻ የሚገኝ የማይዳሰስ ገንዘብ ሲሆን በአለማችን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የክሪፕቶከረንሲ አይነቶች ይገኛሉ። ቢትኮይን፣ ኤቴሪየም፣ ቴዘር እና ካርዳኖ የተሰኙ ክሪፕቶከረንሲዎች ግንባር ቀደም የሚጠቀሱ ናቸው። በአፍሪካ ደግሞ ቢትኮይን ከፍተኛ ተጠቃሚ ያለው የክሪፕቶከረንሲ አይነት ነ