Get Mystery Box with random crypto!

'የሩሲያ የሚሳኤል ዶፍ' ከተጀመረ 104 ቀናት የሆነው ጦርነት የስላም ምድራቸውን ወደ ጦር አውድ | @ArtsTvWorld - Arts TV - አርትስ ቲቪ

"የሩሲያ የሚሳኤል ዶፍ"

ከተጀመረ 104 ቀናት የሆነው ጦርነት የስላም ምድራቸውን ወደ ጦር አውድማነት ለቀየሩት አገሮች ወደ ለየለት የከባድ መሳሪያ እና ሚስኤል ቡጢ ውስጥ ገብተዋል።

የአሜሪካን የአውሮፖን አይዞሽ ባይነት ተከናንባ ወደ ጦርነቱ የገባችው የዘለንስኪዋ ዩክሬን ሁኔታው ሁሉ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኖባታል።ዛሬም ድረስ የመከላከል ብቃት እና ኃይላቸው ከተማዎቻቸውን ከፍርስራሽ፣ዜጎቻቸውን ከስደት፣ወታደሮቻቸውን ከሞት ሊታደግላቸው አልቻለም።

ቢቢሲ እንዳስነበበው በጦርነት ምክንያት ከ6 ሚሊየን በላይ ዩክሬናዊያን ከመኖሪያ ቀያቸው ርቀዋል። 20 በመቶ የዩክሬን ክፍልም በቭላድሜር ፑቲኗ ሀገር በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር ወድቋል።

ወዲህ ደግሞ
ሩሲያ ጦርነቱን ከጀመርች እንስቶ ከሁለት ሺህ አንድ መቶ በላይ ሚሳኤሎችን ወደ በዩክሬን ምድር እንዳርከፈከፈች ተረጋግጧል።

በፈረንጆቹ ዘመን ስሌት በ1991 በሀንጋሪ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ፖላንድ እና ስሎቫኪያ አቅፎ የተመሰርተው ቪስጋርድ (V4) የተባለው ተቋም አረጋገጥኩ እንዳለው የዩክሬን ምድር ካደባዩት ሁለት ሺህ አንድ መቶ በላይ ሚሳኤሎች መካከል ስድስት መቶዎቹ መነሻቸው ከቤላሩስ እንደሆነ ነው ያስቀመጠው።
የተመድን የረሀብ ስጋት ውትወታ ወዲያ ያለው ጦርነት
አሁን ለአለም የምግብ አቅርቦት ችግርን እንዳነገበ፣የፋይንሱን ስርዓት እያደፈረስ መጓዙን አላቋረጠም።
ከዚህም ጋር ተያይዞ ከሁለት ሺህ አንደ መቶ ሚሳኤሉ ባለፈ ሩሲያ “ዚርኮን” የተባለ አዲስ ሃይፐርሶኒክ ክሩዝ ሚሳዔል ለሙከራ ማብቃቷ ይበልጥ በቀጠናው
ውጥረትን መፍጠሩ የሚታወስ ነው።
ምንጭ ቢቢሲ