Get Mystery Box with random crypto!

ረመዳን እዝነት ራህመቱ ሀድ የሌለው ወሰን ነብስያን መራቂያ መጣልን ረመዳን ዑማውን ሊያስ | Art on as sunnah

ረመዳን


እዝነት ራህመቱ ሀድ የሌለው ወሰን
ነብስያን መራቂያ መጣልን ረመዳን
ዑማውን ሊያስምረው ነብስያን አስጥሎ
ከወንጀል መራቂያ ኸይራት አስከትሎ
ከደህና እርዚቅ ጋራ በኢማን ታጅቦ
ዘንድሮም ዘለቀ ሸብርቆ እና አብቦ
ራህመት አስከትሎ ከገፍላ ሚያፀዳ
ከሂስድ ከሀሜት ደርሶ በማለዳ
ብርሀንን አዝሎ ጨለማን አስጥሎ
የራህመት ባንዲራን ተወዲህ ቸክሎ
አቃርቦን የለ ወይ ዑማውን ጠቅሎ
ወጣት አዛውንቱን ሁሉንም አካሎ
የመተሳሰብ ወር ሀቅን አስተማሪ
የቲም መዳበሻ ደግፎን ያባሪ
ሚስኪንን ማጉረሻ በዝነት አባሻሪ
የዝነት ወር ረመዳን ሙሀባን አብሳሪ
አልሀምዱሊላሂ ከአምናው ለዘንድሮ
ላደረሰን ጌታ በአማን አኑሮ
አላህ ካደረሰን ለራህመቱ ወር
ተጠቃሚ ያርገን ከበረካው ባህር

አሚንንንን አሚንንንንንን
አሚንንንንን


@Seadiii

@artonassunnah