Get Mystery Box with random crypto!

የእውቀት ቦታ

የቴሌግራም ቻናል አርማ artislife123 — የእውቀት ቦታ
የቴሌግራም ቻናል አርማ artislife123 — የእውቀት ቦታ
የሰርጥ አድራሻ: @artislife123
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 458

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-16 22:44:12 ደግሞ የነገን ማን ያውቃል!
(ታደሰ ደምሴ)

አንዳንዴም...
ጀምበሯ ቀዝቀዝ ስትል
ሰማዩ ደመንመን ሲል
አየሩ ሲቀዘቅዘኝ
ከላይ በረከት ሊወርድ፣
ሊዘንብ እየመሰለኝ

አንገቴን አንጋጥጥና፣ሸቅቤ አማትራለሁ
ግና ደመና ነው ያልሁት፣ጉም ሆኖ ሲተን አያለሁ
ይሔው ...
ካምና እስከ ዛሬ ፣በውሃ ጥም እንደተቃጠልሁ
የምሻው ቀኔ ተባርኮ፣የነፍሴን ቀለብ አልተቸርሁ
የጸጋ ሲሳይ ዘንቦልኝ፣ጠጥቼ ጥሜን አልቆረጥሁ
እንዲሁ ...
"ማን ያውቃል የነገን" ብየ፣እንዳማኝ እየተጽናናሁ
ብሶቴን በተስፋ አርክሼ፣ሁሉንም እታገሳለሁ!
ቻል!!!


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
36 viewsAchilles, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 22:44:08 ዝም ብለሽ ጠብቂኝ

እርግጥ በዚች ሀገር
የተካበው ሁሉ : በፈራረሰባት
ህልም ያለችው ሁሉ : ቅዠት በሆነባት
ሳመኝ ተው ስትለው : ጥርስ በነከሰባት
ፍቅር ስጠኝ ስትል : መርዝ በተላከባት
ያቀፈችው ሁሉ : ዞሮ በነደፋት
አለኝ ያለች ሁሉ : ባዶ በቀረባት
እርግጥ በዚች ሀገር
እርግጥ በዚች ሀገር
ወተት ስንለምናት : ደም ባዘነበችው
ገዳይ እና አራጇን : በሸላለመችው
ወዳጅ አፍቃሪዋን : ወደዳር ባለችው
እንውደድሽ ሲሏት : በማይገባት ፍቅር
ለሷ በሞቱላት : በሚላት ቅር ቅር
የአፍቃሪን ልብ እምነት : በሰባበረችው
ወዶ የቀረባትን : አንገት ባስደፋችው
እርግጥ በዚች ሀገር
መጠበቅ : ሰው መቅጠር
መጠራት : መቀጠር
ሰአት ሞልቶ : መገናኘት
የናፈቀን : ፍቅር ማግኘት
ቢከብድ እንኳን : ቢያስቸግርም
አንቺን ላገኝ
ሰአት ጠቦ : አያጥረኝም
(ብቻ አትቅሪ : አትቆይ እንጂ
በዚች ሀገር
ግድ የለውም : ብታረፍጂ...)

ግን በተራሽ : ከጠየቅሽኝ
እኔን ናፍቀሽ : ከጠበቅሽኝ
መቼ ትመጣለህ? ብለሽ ካልሽኝ

ጠብቂኝ ግራር ስር : ቁሚልኝ ከዋርካው
አልጣሽ ከዛፉ : ልይሽ ከጎዳናው
ላግኝሽ ከካፌ : በድልድዩ እለፊ
ኑሪ ሁሉም ቦታ : ከሀገሩ አትጥፊ
ዝም ብለሽ ጠብቂኝ : ድንገት እመጣለሁ
መቼስ በዚች ሀገር
እንደምን አምኜ : ነገን አቅዳለሁ?
ልክ ነበርሽ አንቺ
ዝም ብየ ምወዳት : ባልገባችኝ ነገር
እናት ሲሏት ባዳ : ባዳ ሲሏት ሀገር
በሆነች ምድር ላይ
የፊቱን ለማቀድ : ሆኖብኛል ፍርጃ
እንኳንስ ነገየን : ዛሬየን እኔእንጃ
ዝም ብለሽ ጠብቂኝ : ዝም ብየ እመጣለሁ
ምናልባትም ትናንት...
ምናልባትም ዛሬ...
ምናልባትም ነገ...
...እንጃ ምን አውቃለሁ

ብቻ ግን ጠብቂኝ...ጠብቂኝ...ጠብቂኝ


እስከመቼ???

በአቤኒ የተፃፈ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
19 viewsAchilles, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 22:37:23 .

የመገፋት ህመም : የማጣትን ፍቺ
ልንገርሽ እንጂ እኔ : የት አውቀሽው አንቺ

ብዙ ነገ እየሳልኩ : አብሬ ካንቺ'ጋ
ሳስብሽ አመሸሁ : እያለምኩሽ ነጋ
ሀሳቤን ሰርቀሽው : ቀኔ አላማረበት
ቀልቤን ሰውረሽው : አዋዋል ጠፋበት
ከእኔ'ጋ ነሽ እያልኩ : አብረሽኝ ከጎኔ
አንቺ ሩቅ ሄደሻል : እዛው ስቀር እኔ

የቀረበሽ ልቤ : አንቺን በወደደ
የማያውቀው ነፍሴ : በእሳትሽ ነደደ
መላ አካሌ አፍቅሮሽ : እኔን ጥሎ አበደ

እፋረድሻለሁ : በይ ካሽኝ እያልኩኝ
ለብቻየ ስቀር : ብዙ እንዳልነበርኩኝ

ለማን ዳኛ ልክሰስ : ማንስ ይሰማኛል
ጉዳቴን ያሰበስ : ምንድን ይክሰኛል
ጉዳዬን የሰማ : ያ ሁሉ ዳኛ ሰው
ክሴን አቃለለ : ብሶቴን መለሰው
እንግዲህ ምን ላድርግ...
ፍትህ ንብረት አይደል : አልገዛ አልዋሰው

የሰማኝ በሙሉ : የነገርኩት ዳኛ
አንችን ነፃ አረገሽ : እኔን ጥፋተኛ
ከእንግዲህ ለማንም : አልከስም በቅቶኛል
እስካሁን የሰማኝ : እስኪ ምን ጠቅሞኛል
አንቺ ጉልበተኛ : አንቺ ባለጊዜ
እኔ ሟች ደካማ : የዋጠኝ ትካዜ
አንቺን ማን ተሟግቶ : ችሎ ያሸንፍሻል
የቀረበሽ ሁሉ : ላንቺ ያዳላልሻል
ቁመናሽ እሳት ነው : አይን ጥርስሽ ገመድ
ውበትሽ አሳሳች : አሳሳቅሽ ወጥመድ
ማለፍ ቢሳናቸው : ይሄንን ፈተና
እኔን 'በዳይ' ማለት : ቀለላቸውና
እሷን ተበዳይ ሰው : እኔን ወንጀለኛ
ብለው ፈረዱብኝ : ከአንድም ሶስት ዳኛ

አምርሮ ቢያነባ : እንባዬ ቢፈስም
በያገኘው ችሎት : እልፍ ጊዜ ቢከስም
የፍርድን ጥም ሽቶ : ከጫፍ ጫፍ ቢያስስም
ገሳጭ ሰው ነው እንጂ : አይዞህ ባይ አይደርስም

በቃኝ አልካሰስ : ይቅርብኝ ልጎዳ...
ልተወው ግዴለም
ብቻ አውቄዋለሁ : በሰዎች ደጅ እንጂ...
ፍትህ በአገር የለም
አትፍሰስ ይበቃል : ከእንግዲህ እንባዬ
ጩኸቴ አላዋጣም : ይርታት ዝምታዬ

እንግዲህ ገብቶኛል...
ላገኘሁት ሰሚ : አልከስ አልዘልፍሽም
በየአደባባዩ : ስምሽን አልጠራሽም
በየችሎቱ በር : ነይ ግቢ አልልሽም...

ስምሽን ባጠፋ : ብፎክርም እንኳን : አትደናገሪ
ጩኸቴ ምንም ነው : ዝም ስል ግን ፍሪ:


በአቤኒ የተፃፈ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
22 viewsAchilles, 19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 09:17:01 (ምን ያረጋል?)


wow ድንቅ ተፈጥሮ - አወይ መስእቧ
ታድያ ምን ያረጋል - ባዶ ነው መሶቧ

ያልተነካ ጉልበት - 70 percent ወጣት
ታድያ ምን ያረገል - ፓለቲካው ዋጣት

የሚበላ አፈር - የሚቆረስ መሬት
ታድያ ምን ያረጋል - ችግርና ምሬት

ብዙ ብዙ ውበት - ብዙ ብዙ ፀጋ
ታድያ ምን ያረጋል - አልፈጠርክም ዜጋ


Trident
ህዳር 24, 2014

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
39 viewsAchilles, 06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 00:33:29 ናፍቀሽኝ
------------

ረገፍኩ እንደ ጠል - በነንኩ እንደ'ንፋሎት!
አቅፈሽኝ....
ሰፋሁ እንደ ጠፈር - ገዘፍኩ እንደ ምኞት!
ለዚህ በከንካና መንታላ ሰውነት!
አንቺን ማጣት ሞት ነው - አንቺን ማግኘት ሒወት!

በጋሻው የኋላሸት (ዘቢደር)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
10 viewsAchilles, 21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 05:15:37 #አበስ_ገበርኩ
:
:
እንደተለያየን ...
ንቃቃቷ ሞላ ጣለች ገፋ ከሏን፤
ነዶ ሰበሰበች ጠል ወርሶት አካሏን።
እግሯ ባ'ለት ፀና ሻረች መወላገድ፤
ተደላደለላት ስርጓጎጡ መንገድ።


እንደተለያየን ...
ዕድል ተከተላት፤
ንዋይ ሲሳይ ምንዳ ባንድነት ነደላት።
ራስ ሆነች ቁንጮ ፈላጊዋ ጋመ፤
የማይደገመው እየደጋገመ፤
መዳፏ ላይ ታየ፤
የሚያያት ፈዘዘ የነካት በረየ።


እንደተለያየን...
ገዛት ህያው ቃሉ፤
ሰላም ሰፈነለት ሰላም ያላት ሁሉ።
የአፏም ቃል ፀና ይሁን ስትል ሆነ፤
ፈሪው ድፍረት በዛው አንጋሴው ጀገነ።
ተገለጠ ጥርሷ፤
ይስረቀረቅ ጀመር ቱማታው የልብሷ።
እንደ ጀምበር ፈካች፤
በሳቋ ካካት ሰማይ ጫፉን ነካች።


እግዚኦ ምህረት ለኔ አበሳ ለገበርኩ፤
በደል ሀጥያቷ ለካስ እኔ ነበርኩ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
30 viewsAchilles, 02:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 20:46:33 አናቱን ክፉኛ ተፈንክቶ ተኝቷል።
"ማንበብ እወድ የለ?"
"እንዴታ?"
"እና…የሆነ የጎረቤቴ ግድግዳ ላይ የተለጠፈ ነገር ለማንበብ
ስንጠራራ ነው ጉጠት ነገር የወጋኝ…"
"ውይ ውይ! እና አነበብከው?"
"አዎ በጣም!!"
"ምን ይላል…"
"ይህን ለማንበብ አይንጠራሩ!!"

@wegoch
@wegoch
@lula_al_GREEKO
29 viewsAchilles, 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 23:20:27 ሳላውቅሽ በፊት

መኖር ቋቅ ብሎኝ 
ሞትን ልወዳጅ ደጁን ብጠና፣
ላሽ ብሎኝ ቀረ
ለኑሮ ጥዶኝ በአሳር ጀበና።

"ሞት ልለምንህ"

"ኑር አርፈህ!"

"ባክህ ውሰደኝ!"

"ተው አትበጥብጠኝ"


ጥሎኝ ከነፈ!
ጽልመት ገዘፈ!



ካወቅኩሽ በኋላ

ንጋት መነጨ!
ሞትም ተቆጨ!

ዘመናት ንቆ
ገሸሽ ያለውን ጥሪ አክብሮ፣
ይኸው ከች አለ
ከሰይጣን ዘንድ ሴራ  ቋጥሮ።


"ና እንሂድ!"

"ወግድ!"

"ተው አላምልጥህ"

"ማን ሲፈልግህ"

ሞኞ
እሷን አቅፌ መደየም ልመኝ፣
ተው አታስቀኝ!

ይልቅ አትልፋ
ደጄን ቆርቁረህ ነፍሴን ለመንጠቅ፣
ላንተም ስቃይ ነው
ከ'ቅፏ እስክለይ ዘመን መጠበቅ።
አትምጣ ንገር ለላከህ ጌታ፣
መስቀል መውደዴ
ጎኔ እስካለች ሞትን ዘላለም እንደምረታ።

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
24 viewsAchilles, 20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 23:19:23 #ኖሯል_ለካ
:
:
ቀኝክ ሲሰጥ ግራክ አይይ
ሚለውን ቃል ረስቼ፤
ላደባባይ ልግስና
ጎህ ሳይቀድድ ተነስቼ፤
ተሽቀዳደምኩ ለታይታ፤
ተንበረከኩ ለሁለት ጌታ።
:
:
በልቤ ውስጥ ቁርሾ ሞልቶ፤
መንፈሴንም አከርፍቶ፤
ሥጋዬ ግን ናርዶስ ሽቶ፤
ተርከፍክፎ ተቀብቶ፤
በሙክራቡ ዘርፈፍ አልኩኝ
እየወጣው እየገባው፤
አልባስጥሮስ በሰው ራስ
ግን አንድም ቀን መቼ ቀባው።
:
:
በሰዎች ላብ ቦርጭ አወጣው፤
ጥማዶቼም ለሰው ታዩ
ገሀድ ቆሜም ፅዋ ጠጣው።
ባንዲት መርፌ ቀዳዳ ውስጥ
እንደማልፍ መች አሰብኩት፤
ያለ ድንበር ያለ ወሰን
ሥጋዬንም አደለብኩት።
:
:
አንድ ኪሴን ታበይኩበት፤
«አለው» መባል «አለኝ» ማለት፤
ግብዝ ልቤን እያኩራራው፤
ምንዱባንን ፀበል ጠራው።


ተላለፍኩኝ እውነት ምንጩን፤
ስንቱን ከዳው ስሜ ጉንጩን።
ግንድ አክሎ ያይኔ ጉድፍ
ማየት እንኳ ተቸግሬ፤
ፈርጃለው ጣት ቀስሬ።


አሳደድኩት አሳዳጄን፤
ቀኜን መታኝ አነሳሁት
ለአፀፋው እኔም እጄን፤
ባልንጀራን እየገፋው፤
እንጀራዬን ግን አሰፋው።


ነፍሴ ተዪኝ ይበቃኛል
እስከመቼስ ከራሴው ጠብ፤
ከፍ ማለት ኖሯል ለካ
ዝቅ ብሎ እግር ማጠብ።

(እኛ ልናንስ ፍቅር ግን ሊልቅ ግድ ነው)

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@cyrusofethiopia
@getem
@getem
@getem
22 viewsAchilles, 20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 23:15:40 ናፍቆት ወለድ ሆሣዕና
°°°°°°\°°°°°\°°°°°°°°

ከቤተ መቅደስ ደጅ
በረከት የነካው ይሰጣል ዘንባባ፣
ቀለበት ያማረው
እጁን ይዘረጋል ሊቀበል ከአባ።

እኔ አስባለሁ ከአጥሩ ፊት ቁሜ፣
ልቤን ያሰርሽ 'ለት
እንዴት እንደረካሁ ከአፋኝ ሀሴት ጥሜ።
ትዝ አለሽ?
የዛሬ ዓመት
የኔነቴን መቅደስ ልታጥኚ በፍቅር፣
ወንበዲያም ዝሙቴን
ቀማኛ ምኞቴን አስረሽ በውበት ክር፤
ገፍተሽ ስትጥይው!!
ከኔ ስትሰውሪው!!
ዘለዓለሜን ላንቺ ልገብር አስቤ፣
ዘንባባ ዘንጥፌ
ልብሶቼን አንጥፌ
ሆሣዕና እያልኩ ስዘምር በልቤ።
:
{አየሽው እብደቴን?
ማጣት የጎበኘው ጅል ውፍፍናዬን፣
በሌለሽ ተሰጥኦ
ሰሚ ሲያደርግሽ የልብ አፍ ወሬዬን።}
:
አልባስ የለበሱ፥
ዘንባባ የያዙ፥
በስርቅርቅ ድምፅ መዝሙር ሚዘምሩ፣
አዳጊ ህጻናት
ጌታን ሊዘክሩ አህያ ሲያዞሩ፤
ነቃሁ ከሀሳቤ፥
የት ትሆኝ ያለሽው አንቺ የነፍስ ምግቤ?
ናፈቅሽኝ!
ናፈቅሽኝ!!
ናፈቅሽኝ!!!
ከህማማት በፊት
ምናለ ላንዳፍታ መጥተሽ ባቀፍሽኝ።
እቅፍ!!
እቅፍቅፍ!!!
በቁም በድኔ ገላ
ህያው ትንፋሽሽን እፍፍፍፍፍፍፍፍ...!!!

ንቃ ባትይኝም
ተነስ ባትይኝም የ'ስትንፋስሽ ጉልበት፣
ነፍሴን ያድሳታል
ፈንቅሎ አውጥቶ ከተቀበረበት።

እንደገና እቅፍ!!
ደረትሽ ላይ ልጥፍ!!
ለዘለዓለም እርፍ!!
.
.
በባዶ አየር ላይ
በሀሳብ ስንጎማለል ገጽሽን ለጥፌ፣
ወድቄ ተገኘሁ
በደረትሽ ፈንታ መሬት ላይ አርፌ።

አትመጪም ልሙት?
ወይስ ልጠብቅሽ ተነጥፌ ከአፈር?
ቃልሽን ጠባቂ ነኝ፥
ብስራት ሰምቼ በሀሴት ለመዘመር፤
አልያም አሁኑኑ
መርዶዬን ተግቼ በፍትኃት ለመቀበር።

በይ ቃል ተንፍሽ!!

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
22 viewsAchilles, 20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ