Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ሶላትን አስመልክቶ ሙስሊም ተማሪዎች ወጥተው እንዲሰግዱ ከስምምነት ተደረሰ። Mujib | አራይቫል የልማት እና መረዳጃ ማህበር

ሰበር ዜና

ሶላትን አስመልክቶ ሙስሊም ተማሪዎች ወጥተው እንዲሰግዱ ከስምምነት ተደረሰ።

Mujib Amino
▬▬▬▬▬▬▬▬▬●●▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ሚያዚያ 03/2014 ሰኞ

በተለይም ካለፈው ሳምንት ወዲህ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሴኩላሪዝም ጽንሰ ሐሣብ abuse በማድረግ ሙስሊም ተማሪዎች በእምነታችው በግዴታነት የተደነገገውን ሶላት ወደውጪም ቢሆን ወጥታችሁ አትስገዱም በማለት ሕገ መንግስታዊ የኃይማኖት ነጻነታቸውን ሲገፍ ቆይቷል።

በዛሬው እለትም ቢሆን የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላይ ሶላትን አስመልክቶ ከተማሪዎች ጋር አላስፈላጊ ግብግብ ሲፈጸም ነበር።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝደንትን የሆኑት መሪያችን ፣ አባታችን ፣ የሕዝባችን ጠበቃ የሆኑት ሸይኽ ሱልጣን አማን በየእለቱ የመንግስት ቢሮዎችንና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ካለእረፍት ሲወተውቱ ቆይተዋል።

በዛሬው እለትም ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ጋር በነበረው ውይይት የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሱልጣን አማንና ባልደረቦቻቸው ባደረጉት ትግል ተማሪዎች ወደውጪ ወጥተው እንዲሰግዱ አቅጣጫ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ሰዓትም በስምምነት ላይ የተደረሰውን የተማሪዎችን የሶላት ጉዳይ በፁሁፍ እንዲደርስና ለሁሉም ክ/ከተሞች በግልባጭ እንዲደርስ በመነጋገር ላይ ይገኛሉ።

ትግላችን ይቀጥላል!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የቴሌግራም ቻናል-https://t.me/MujibbinISLAM
@Abuki_Tube | @Abuki_Tube