2022-06-19 07:35:42
ሙታኗ ላይ ዝሙት ፈፀምኩ
"""""""""""""""""""""""""""""""""
ማንኛውም ሙስሊም ታሪኩን ያንብበው አስገራሚና አስደናቂ እንዲሁም አስተማሪ ታሪክ ነው
ዑመር (ረ.ዐ) ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እያለቀስ ገባ፤ ይህን የተመለከቱት መልዕክተኛውም፦ ምን ያስለቀስሀል ኡመር" አሉት።
አንቱ የአላህ መልዕክተኛ…! በር ላይ አንድ ወጣት ሲያለቅስ ተመልክቼ አንጀቴን አላወስው" አላቸው።
"አንተ ልጅ ሆይ… ለምን ታለቅሳለህ ?" በማለት መልዕክተኛው ወጣቱን ጠየቁት።
የሀፍረት ስሜት እየተስማው፦"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ…ብዙ ወንጀሎች ያስለቅሱኛል የተቆጣብኝ ጌታዬንም ፈርቻለሁ አላቸው ።
ነቢዩ (ሰ.ዓ.ወ) "በአላህ ላይ ሌላን አካል አጋርተህ አምልከሀልን?" አሉት።
አይ…አላቸው።
"ነፍስን ያለ አግባብ ገለሀልን?" አሉት።
"አይ…" አላቸው።
እንግዲያውስ ወንጀልህ የሰባት ስማያት፣ የሰባት ምድርን፣ የተራራዎችን እና የኮረብታዎችን ያህል እንኳ ቢሆን አላህ ይቅር ይልሀል" አሉት።
"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ… ወንጀሌ ከስባት ስማያት፣ ከስባት ምድር፣ ከተራራዎች እና ከኮረብታዎች ይበልጣል እኮ" አላቸው።
"ወንጀልህ ይበልጣል ወይስ ኩርሲይ?" ብለው ጠየቁት።
"ወንጀሌ ይበልጣል" አላቸው።
"ወንጀልህ ይበልጣል ወይስ አርሽ?" ደግመው ጠየቁት።
"ወንጀሌ ይበልጣል" በማለት ደግሞ መለስላቸው።
"ጌታህ መሀርታው ይበልጣል ወይስ ወንጀልህ?" ብለው ጠየቁት።
"አላህ ይበልጣል፣ ይልቃልም" ብሎ መለስላቸው።
"ታዲያ ትልቁንም ወንጀል እኮ ትልቁ አላህ እንጂ ማንም አይምርህም" አሉት
መልዕክተኛው።
"አንተ ልጅ እስቲ ወንጀልህን ንገረኝማ…አሉት
እሱም፦"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ…!ወንጀሌም በእርሶ ፊት መናገር ያሳፍረኛል" ብሎ መለስላቸው።
"እስቲ ወንጀልህን ንገረኝ" ጥያቄውን ደገሙለት።
"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ…! እኔ ቀብር ዘራፊ ነበርኩ
ላለፉት ሰባት አመታት መቃብሮችን ስዘርፍ አሳልፊያለሁ።
ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት የመዲና እንስት ሞታ ቀብሯን በቀን ልዘርፍ ቆፍሬ ከፈኑን ከላይዋለይ ገለብኩት፤ ከፈኗን ይዤ ትቻት መሄድ ጀመርኩ ነገር ግን ብዙም ሳልርቅ ሽይጧን ወደ ቀብሩ እንድመለስ ጎተጎተኝ…! ተመለስኩኝ እና ዘሞትኳት
ከዚያም ተነስቼ መሄድ ጀመርኩ፤ ብዙም ሳርቅ ሙታኗ ብድግ ብላ፦"ዋ ጥፋትህ… አንተ ወጣት…!! ያ ዙፋኑን ለፍርድ አስቀምጦ ከበደለኞች ሀቃቸውን ይዞ ለተበዳዮች የሚያደርስውን ጌታ አታፍርምን
በሙታን አውድማ ብቻዬን ትተህኝ ትሄዳለህን…?
አላህ ፊትም ለሂሳብ ስቆም ከነጀናባዬ አቆምከኝ…! ትርክቱን ሳይጨርስ……
መልዕክተኛው አፋቸውን ይዘው፦"አንተ ፋሲቅ ዞር በልልኝ፤ አንተ ለእሳትም ምንኛ ተገቢ ነህ…!
ወጣቱ ተስፋ ቆርጦ ከመልዕክተኛው ዘንድ ወጣ። ለአርባ ቀናት ያህልም አላህን ሲማፀን ከረመ።
አርባኛ ቀኑ ሲሞላ እጁን ወደ ላይ አንስቶ፦"አንተ የሙሀመድ፣ አንተ የአደም፣ እና፣ የሀዋ ጌታ ሆይ… ፀፀቴን ተቀብለህ ምረህኝ እንደሆን ለሙሀመድና ለባልደረቦቹ አሳውቅልኝ።
ያ-ሳይሆን ቀርቶ ፀፀቴን ያልተቀበልከኝም እንደሆነ፤ ከስማይ እሳት አውርደህ አሁኑ አቃጥለኝ'ና ከጀሀነሚቱ እሳት ገላግለኝ" በማለት አላህን ተማፀነ።
ፈጣኑ መልዕክተኛ , የረሱል (ሰ.ዓ.ወ) ባልደረባ ጅብሪል (ዐ.ስ) ሰማያትን አቋርጦ ወደ ነብዩ ( ሰ.ዓ.ወ) ዘንድ የጌታውን ትዕዛዝ ይዞ ብቅ
አለና፦
ሙሀመድ ሆይ…! ጌታህ ስላም ይልሀል" አላቸው።
ነቢዩም (ሰ.ዓ.ወ ) ፦"እሱ ስላም ነው፤ ስላምም ከሱ ነው፤ ወደሱም ተመላሽ ነው" ብለው በንግግር ተጠበቡ።
"አላህም ብሎሀል (ፍጥረትን አንተ ነህ እንዴ የፈጠርከው)" አላቸው ጅብሪል።
"እንዴታ…! እኔን እና ፍጥረታትን በሙሉ የፈጠረው ጌታ ነው የፈጠራቸው)" በማለት መለሱ።
"ጌታህም ይልሀል (አንተ ነህ እንዴ መሀርታን የምትለግስው)" ዳግም ጅብሪል ጥያቄያዊ መልዕክቱን አስተላለፈላቸው።
"እንዴታ…! አላህ እኮ ነው እኔንም ፍጥረታትንም ይቅር የሚለው መሀርታ የሚለግስው" በማለት መለሱ።
አላህም ይልሀል (ባርያዬን ይቅር በለው፤ እኔም ይቅር ብየዋለሁ)" በማለት ጅብሪል የጌታውን መልዕክት አስተላለፈ።
ይሄን ጊዜ መልዕክተኛው ያን ወጣት በማስጠራት አላህ ይቅር እንዳለው አበስሩት።
በማያልቀው የአላህ አጅር ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ላይክ ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
@ArkemMy
@ArkemMy
@ArkemMy
@ArkemMy
98 viewsHope ➊ ye aryifochu , 04:35