Get Mystery Box with random crypto!

እውነት እውነት በሰው ብዛት አትዳኝም። እውነት ሁልጊዜም እውነት ናት። ሰው በእውነት መኖር ሲያቅተ | አርጋኖን ስነ-ግጥም ና ጭውውት ..On.Tg

እውነት
እውነት በሰው ብዛት አትዳኝም። እውነት ሁልጊዜም እውነት ናት። ሰው በእውነት መኖር ሲያቅተው ለውሸቱ ደጋፊ ይፈልጋል። ለውሸቱ የማይገናኝ ጥቅስ ይጠቅሳል ። ውሸትን ግን በሚዲያ ብታስነግራት፣ በመጽሐፍ ብትጽፋት፣ በብዙ ሰው ብታስነግራት ያው ውሸት ናት።ሰው በመንጋ ከማሰብ ወጥቶ በተ ሰጠው አእምሮ ክፉና መልካሙን አመዛዝኖ የሚወስን መሆን ይገባዋል። በውሸት ሚልየን ሕዝብ ከሚያጨበጭብልህ እውነትን ተናግረህ ሚልየን ሰው ቢጠላህ ይሻላል።ሰው ቢጠላህ የእውነት ባለቤት እግዚአብሔር ግን ከአንተ ጋር ይሆናል። ቅዱሳን መላእክቱ ይወዱሃል።

እውነት አንድ ነው።እርሱም እግዚአብሔር ነው ። የእግዚአብሔር ትእዛዙ ሥርዓቱ የእውነት መገለጫ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥም በሌላው ሀገርም ሰላም ፍቅር የሌለበት ምክንያት ሰላም እና ፍቅር እንዲያሸንፉ ሰው ስለማይፈልግ ነው።ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነት የበዛው እውነት እንድታሸንፍ ስለማይፈለግ ነው። እየተጣላንበት ያለው እውነታው አንድ ነው።ነገር ግን እውነታውን ከመቀበል ይልቅ ራስ ወዳድነት እና ግለኝነት ስለተስፋፋ ሁሉም ከፍቅር እና ከአንድነት እሳቤ ወጥቶ ለጦርነት ተሰለፈ።

ፍትሕ፣ፍቅር (ሌላውን እንደራስ መውደድ)፣ አንድነት የእውነት መገለጫዎች ናቸው። ነገር ግን እውነትን የጠሉ ሰዎች ስግብግብነትን፣ ዘረኝነትን እና ማዳላትን ገንዘብ አድርገው ሰውን ያበጣብጣሉ።ዘላቂ ሰላም የሚመጣ በጦርነት አይደለም። በይቅርታና በፍትሕ እንዲሁም በፍቅር እንጂ። እውነትን የሚፈራት ውሸታም ሰው ነው።

በእውነት እንኑር
ለእውነት እንኑር
ለእውነት እንሙት