Get Mystery Box with random crypto!

ለጊዜው ተቆርቋሪ፣ ተከራካሪ፣ ተሟጋች፣ ለ ሌለው በተገኘበት እንደ ዶሮ አንገቱን ለሚቆረጥ , ህ | Anti illuminati

ለጊዜው ተቆርቋሪ፣ ተከራካሪ፣ ተሟጋች፣ ለ ሌለው በተገኘበት እንደ ዶሮ አንገቱን ለሚቆረጥ , ህዝብ ማን ድምጽ ይሁነው..? የ በፊቱ አንባገነን አገዛዝ አልፎ ተደስተን ሳናበቃ መንበረ ሥልጣኑን ከተረከቡ ዕለት አንስቶ ባለፉት 4 ዓመታት በኢትዮጵያ ስንት አልፍ ቁጥር ያለው ሰው ታረደ፣ ተጨፈጨፈ ፣ ተሰደደ ተዘረፈ ፣ መሄጃ መደረሻ አጣ ፣ መንግስት ባለበት ምድር ፣ ሰው እንደ ዶሮ ባደባባይ ታረድ ! ይሄሁኑ ጉድ ፣ ጭካኔ ፣ ሲፈጸም ፣ ምንግስት ችግኝ እየተከለ ነው፣ አንድም የሃገር ሚዲያ አካል አላወገዘውም.. ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ጭ ጭ ብለው ስለ ዩክሬን ራሺያ ጦርነት ይዘግባሉ.. ሃገራቹ ላይ ይህን ያህል የዘር ጭፍጨፋ እየተካሄደ .. ዜናው ስለ አብይ አህመድ ሰላጣ ተከላ ያወራል.. ታዲያ ይሄ ሃገር ነው ...? ምንም እንኳን መንግሥት ነኝ (ባዩ ገዳይና አስገዳይ) ምንም አይነት የሀዘን መግለጫ ባይሰጥም ፣ከ ቀናት በፊት ቴዲ አፍሮ ህመማቸንን ፣ ብሶታችንን፣ በሙዚቃ ገልጾልናል ለዚ ነው ቴዲ አፍሮን የምንወደው ... ልክ ያለሆነ ነገር እያየ እንደሌሎቹ ሆዳም አርቲስቶች ዝም አይለም... #TEDDY AFRO - ናዕት ሰብዓዊነት የት ገባ .. ይህን ያህል ህዝብ እየተጨፈጨፈ ,.. ሚዲያው ስለ እገሌ ኮንሰርት ያወራል.. የ እውነት ያሳፍራል! እኔ እዚጋ ሰለ አዲሱ የ አለም መንግስት NWO ፣ ስለ ኢሉሚናቲ ስለ ፣ fake pandemic , ባወራ ምን ትርጉም አለው .. ህዝን እየተገደለ ..ወገን ወዴት እየሄድን ነው..? ሃገራችን ውስጥ ስንት ተሰሚነት ያለው መልዕክት ማስተላለፍ ሚችል .. ሰው አለ ... ዪሄ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም ግን አንዳቸውም ምንም እንዳላዩ ዝም ጭጭ ብለዋል ለምን? እስከመቼ ዝም ብለነ እንኖራለን? ገዳይን ገዳይ ማለት ምን ያስፈራናል? የግድ የገዛ ቤተሰቦቻችን ላይ እስኪመጣ መጠብቅ አለብን.. እንዴት ሰው በገዛ ሃገሩ በ ሺ ሚቆጠር ሰው እየተገደለ ዝም ይላል? እንዴት ንፁሐን ምንም በማያቁት በማንነታቸው ሲታረዱ ዝም ይባላል? እኔ ግን ዝም አልልም ተሟጋች አልባ ተከራካሪም ለሌላቸው የ ሃገር ልጆች የወንድም እህቶቼን፣ የአባት የእናቶቼን ህጻናት የአዛውንቶቹን ሞት እያየው ዝም አልልም። ያማል, ፍትህ የጠፋበት ግዜ ያሳዝናል አምላክ ደማቸውን ይቀበል ፍርዱንም ሳይዘገይ ያሳየን አምረራቹ ከጸለያቹ .. ይሄን ሰይጣን መንግስት ይነቅልልናል። ፀልዩ

@thetruthmayscareyou

የሃዘን ቀን

የሞቱትን ነብስ ይማርልን !