2023-01-12 20:55:09
የሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት ክፍል በሰንበት ት/ቤቱ አባላትም (ተማሪዎችም) ከምእመናን የሚነሱ ማንኛውም ዓይነት መንፈሳዊ ጥያቄዎችንን ለመመለስ የሚያስችል
ምን እንጠይቅልዎ? የተሰኘ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም የሰንበት ት/ቤታችን አባላት እና ተማሪዎች እንዲሁም ምእመናን ለሚፈጠርባችሁ ማንኛውም ጥያቄ ለሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት ክፍል ጥያቄያችሁን በማቅረብ አስፈላጊውን መልስ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
እንዲሁም በቅርቡ ተሰጥቶ በተጠናቀቀው ነገረ ሰብእ ትምህርት ላይ መጠየቅ የምትፈልጉትንም ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል፡፡
ጥያቄዎትን ከዚህ በታች ባሉት አማራጭ ተጠቅመው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
1.@minenteyklwobot ወይንም
ምን እንጠይቅልዎ? በማለት Telegram ላይ በመፈለግ(Search) በማድረግ ቡቱን በመጠቀም ጥያቄዎትን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
2. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ቤተ-መጻሕፍት በሚገኘው ሳጥን በመጠቀም ጥያቄዎትን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ (ጥያቄዎትን ሲጠይቁ የሚገኙበትንም አድራሻ (ስልክ ቁጥርም) አያይዘው ይግለጹ)
3. የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችን በአካል በማግኘት ጥያቄዎትን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ (ጥያቄዎትን ሲያቀርቡ በጽሑፍ ብቻ ይሁን፡፡) (ጥያቄዎትን ሲጠይቁ የሚገኙበትንም አድራሻ (ስልክ ቁጥርም) አያይዘው ይግለጹ)
162 views̶L ̶o ̶g ̶ ̶I ̶n, edited 17:55