Get Mystery Box with random crypto!

በዚህኛው እና ይሔን በመሠሉት አይደለም የክህደት እና ተቃርኖ መገለጫችን ይፋ የወጣው ፤ ➙ በድሕ | አንሙት አብርሃም

በዚህኛው እና ይሔን በመሠሉት አይደለም የክህደት እና ተቃርኖ መገለጫችን ይፋ የወጣው ፤

➙ በድሕረ-ደርግ የጀመረው የአማራ ቅራኔ፡ ከ2008 ጀምሮ በአዲስ ⁽⁽ማሕበራዊ ንቅናቄ⁾⁾ ሲመራ እና "የበለሳውን የአመራር ቡድን" ተጠያቂ ሲያደርግ፣ የበለሳዎቹ ስሪትና አስፈፃሚ የነበሩትን አድኃሪያን በለውጥ አመራርነት ሲቀበል ነው ተቃርኖው የጀመረው፤

➙ የአማራውን ⁽⁽ማሕበራዊ ንቅናቄ⁾⁾ በማጥቃት እና በማስጣል ሲሠሩ የነበሩ አመራሮች ፣ ድንገት የትግሉን ሚዛን ተከትለው ሲቀየሱ ፣ ያልፈጠረባቸውን እና የማያምኑበትን የአማራ ብሔርተኝነት ንቅናቄ ኮርጀው "ፊት መሪ" ሲመስሉና ሲደረጉ ነው ተቃርኖው የከፋው፤

➙ የአማራ ⁽⁽ማሕበራዊ ንቅናቄ⁾⁾ የጠበቀውን ውጤት እና ጥያቄዎቹን ለሌላ ጌታ አሳልፈው ሸጠው፣ ከሕዝቡ ጋር አብረው አልቃሽና ቆዛሚ ሆነው ሲሰለፉ ነው የሀሳብና አላማ ድርቅ ተቃርኖ፡ ፀሐይ የመታው፤

➙ ለ20 አመት እና ሰላሳ አመት ከአማራ መከራዎች ጎን ተሰልፈው የነበሩ ሰዎች፣ ይቅርታ ስለጠየቁ፡ የአማራ ጥያቄዎች እና ችግሮች መፍትሔ ይሆናሉ ተብሎ ሲገመት ነው የአማራ ውድቀትና ጥቃት ቀጣይነት የታወጀው፤

➙ በወታደራዊው መስክ፡ ለሩብ ክፍዘ የአማራ ወታደራዊ አባላትና አመራሮች ቅሬታ ሲያቀርቡ ፣ ሲባረሩ ፣ ሲነቀሉ እና ሲገፉ ያለእንቅፋት እስከ ሌተናንት ጀነራልነት የደረሰው አበባው ታደሰ ፣
የቅድመ-2010 ፖሊስ፡ የአማራ ልጆችን ሲያሳድድ፡ የተቋሙ ኃላፊ የነበረው ተመስገን ጥሩነህ ፣ ... ግለሰቦቹ ከመደበኛ ትምህርት ሪኮርድ ውስንነት በላይ፣
ያላቸውን "ውጫዊ ታማኝነት" እና "ፖለቲካ-አልቦነት" የዘነጋ ተስፋ ሲጣልባቸው ነው የአማራ ልጆች እሥራትና እንግልት ተቆርቋሪ አልባ መሆኑ ገሃድ የወጣው፤

➙ የአማራን ጥያቄ መመለስ አቅቷቸው ፣ ቆስለው አቁስለውን ፣ በመንደር ተሰልፈው እና በመንደር ተቧድነው፣ የግልና የመንደር አጀንዳ የፖለቲካ አላማ አድርገው ሕዝቡንም ለማባላት ሲሰለፉ ነው የአማራ ትግል መቀልበሱ ሌላ መልክ የያዘው ፤

➙ ወይ ለሰላም ወይ ለጦርነት ሳይዘጋጁ ፣ የአማራን ሕዝብ እጅግ አዋራጅ ለሆነ ጦርነት ዳርገውት ሲያበቁ፣ ለማያቋርጥ የጭፍጨፋ እና መፈናቀል ውርደት ዳርገውት ሲያበቁ፡ በስልጣን እና ገባሪነት እንዲቀጥሉ ሲፈቀድ ነው፡ የአማራ ፖለቲካዊ ውድቀቶች የተለየ ምዕራፍ የገቡት፤

➙ ስለሆነም፡ Sisay Awgichew Wondemtegegn (እና ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች) የሚንገላቱት፦

የኢሕአዴግ ሰልቫጆች በፖለቲካ ውድቀት ከፈጠሩት ጦርነት እና ውድቀት ይልቅ የተፈፀመን ግፍ በመፅሐፍ የመዘገበው ሲሳይ የሚወነጀለው ፣
እነሱ ማፈናቀሉን እና መጨፍጨፉን ማስቆም ይቅርና በተሰበሰቡበት ካምፕ ሊመለከቷቸው የሚጠየፏቸውን ተፈናቃዮች አለሁ በማለቱ የሚከሰሰው ሲሳይ፤
ዘጠኝ ዙር ያጠቁትን እና ያስጠቁትን አጣዬ መልሶ ለመገንባት በመሥራቱ የተወነጀለው ሲሳይ.... መነሻው ክህደትና ተቃርኖ ያጎበጠውን ፣ ግርድና የተለማመደውን፣ ብሔራዊ ስሜት የነጠፈበትን የብዐዴን ውራጅ በመሸከማችን ነው !!

መፍትሔውም ይሔንን አለቅት ከአማራ ትከሻ ፈጥፍጦ የሕግ ተጠያቂ ማድረግ ነው !!