Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አዙሪት እና የአማራ ፍዘት!? (አንሙት አ.) አስተማሪዬ ሀብታሙ አለባቸው 'ታላቁ ተቃ | አንሙት አብርሃም

የኢትዮጵያ አዙሪት እና የአማራ ፍዘት!?
(አንሙት አ.)

አስተማሪዬ ሀብታሙ አለባቸው "ታላቁ ተቃርኖ" ባለው መፅሐፉ፥ አፄ ኃይለሥላሴ፡ ኤርትራን ከቅኝ ግዛት ነፃነት በኋላ ወደኢትዮጵያ ለማካተት መሥራታቸው፡ በአፄ ምኒልክ ዘመን የተጠቃለለውን የstate formation ሒደት ወደኋላ የመመለስ እርምጃ እንደነበር ያወጋል።

ደርግ ያንን state ለማስከበር "በአቢዮታዊት እና አንዲት ኢትዮጵያ" ሲምልና ሲታክት ከርሞ አሸለበ። በወያነ/ኢሕአዴግ ደግሞ የኢትዮጵያ state formation ጉዳይን እንደገና በማንሳት፤ ኤርትራ መልሳ የተሸኘችባት እና በውስጧ ደግሞ የራስ-በቅ ግዛተ-መንግስቶች አገር ለማድረግ ደከመ። "አዲስቷ ኢትዮጵያ" እያለ ሲያንቆለጳጵሳት ከርሞ ከመንበሩ ዘወር አለ።

በዚህ የኢትዮጵያ state formation ጉዳይ፡ ከዜሮ የመጀመር ልማድ ስለተጣባን፥ አሁን እድል አግኝተናል የሚሉት የኦሮሞ ልሒቃንም የፈረደበትን የኢትዮጵያን state formation መልሰው አንስተው እያመነዠጉት ነው። ወደኋላ 150 ዓመት መልሰን እንሥራው ብለው ተነስተዋል። (500 ቢያደርጉት ምን ፈርተው ይሆን!? )

የአሁኖቹ የሚለየው በstate formation ላይ የያዙት አላማ ከኢትዮጵያ ይልቅ በኦሮሚያ state formation ላይ ትኩረት ማድረጉ ነው። ሌሎችን ኢትዮጵያውያን እና የአገር-ግዛቶቻቸውን ከኦሮሞ የግዛት ፍላጎት የሚተርፉ ጥቅም አልባ የማድረግ ቡድናዊ ፍላጎት መሸከሙ ልዩ ነው።
እንደቀደሙት መንግስታት፡ ወደኢትዮጵያ በሚካተቱ እና ከኢትዮጵያ በሚቀነሱ ግዛቶች ላይ ሳይሆን ወደኦሮሚያ በሚጠቃለሉ ግዛቶች ላይ የሚሠራ ነው።

ከኢትዮጵያ አጎራባች የሆኑ አገራት ለምሳሌ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ እና ሌሎችም ከኢትዮጵያ አንፃር ሳይሆን ለኦሮሚያ በሚኖራቸው ፋይዳና ተጎራባችነት እየተሠሉ እና እየተሠላላቸው መሆኑ በክፍለዘመኑ የተለየ ገጠመኝ ነው።

ኢትዮጵያ የstate formation ይሁን nation formation ወይም ለፖለቲካ እንደሚነገድበት ለMultination building ያልታደለች፡ ውስጧንና ዙሪያዋን መሬት ስትቀድ እና ስትሰፋ ቀጥላለች።
የሔዱ የመጡት ሁሉ ከአዲስ የstate formation አላማ ስለሚነሱ ፡ የNation/MultiNation ግንባታ ጉዳይ ሳይጀመር የሚጨነግፍ እንግዳ ነገር ሆኗል።

ረጅም የመንግስትነት ታሪክ ተሸክማ ፣ በቅኝ ገዢዎች ፈቃድ ሳይሆን በነገስታቶቿ አቅም፣ በአቢዮት እና ዝግመት ፡ግዛተ-መንግስቷን የመሠረተች ጥንታዊት አገ፡ ከትናንት አገር ጀመሪዎች በባሰ የውድቀት አዙሪት የምትወዛወዝ አሳዛኝ አገር ሆናለች።

ጉልበት ደግሞ የእቅዱ ማስፈፀሚያ ነውና የዜጎቿ ስቃይና ደም መፍሰስ ሁሌም እንደቀጠለ ነው።

አማራ፥ ለዘመናት በተለያዩ አካላት ፍላጎቶች የሙከራ ውጣ ውረድ ከመድማትና ከመቀጣት ወጥቶ ስለራሱም ስለኢትዮጵያም ለማሰብ የዘገዬ የቤት ሥራ ላይ ነው።

በኢምፔሪያል ኢትዮጵያ እንደነበረው ዘመን ያለ ሳይሆን፣ ከአማራዊ ፍላጎት የሚነሳ፡ የአማራ እና የኢትዮጵያ state formation እና Nation building አላማችንን በግልፅ ልንመክርበትና ልናሠምር ይገባል።
አስቸኳይነቱ ለትናንት ነው