Get Mystery Box with random crypto!

የመዓዛ መሐመድ ሽልማት፡ እሷ በግሏ ላደረገቻቸው ጥረቶች እውቅና የሠጠ ብቻ አይደለም። በሰሜኑ ጦ | አንሙት አብርሃም

የመዓዛ መሐመድ ሽልማት፡ እሷ በግሏ ላደረገቻቸው ጥረቶች እውቅና የሠጠ ብቻ አይደለም።

በሰሜኑ ጦርነት የአማራ ሴቶች ላይ የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን እንዲሁም በኦሮሚያ ደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ታግተው ደብዛቸው የጠፋ የአማራ ሴት ተማሪዎች ላይ የደረሱትን ጥቃቶች እውቅና የሰጠ ተደርጎ መታየት አለበት።
የአሳሪዎቿን ገመናም የገለጠ ነው።

የተፈፀሙ ግፎች አለምአቀፍ እውቅና ከተሰጣቸው በኋላ የተጠያቂነት እዳ የሚያስቀምጡ ናቸው።

መዓዛ የዚህ ምክንያት በመሆኗ እና ጥረቷ እውቅና በማግኘቱ እንኳን ደስ አለሽ እንላለን !!

ማስታወሻ፤
[ሌሎች ሙያተኞች እንዲሁም የአማራ የሙያ እና ሲቪክ ማሕበራት በየዘርፉ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን የተመለከቱ መረጃዎች ተደራሽ ለማድረግ ጥሩ ምሳሌ ሊያደርጉት ይገባል። ]