Get Mystery Box with random crypto!

ወረዳዎቹን አስረክቦ ቁጭ ያለው የቤኒሻንጉል ክልል ፤ የማኦኮሞ ልዩ ወረዳ እና ያሶ ወረዳዎችን ' | አንሙት አብርሃም

ወረዳዎቹን አስረክቦ ቁጭ ያለው የቤኒሻንጉል ክልል ፤

የማኦኮሞ ልዩ ወረዳ እና ያሶ ወረዳዎችን "የኦሮሚያ ኃይል" ጠቅልሏቸዋል። ይሔንን ያወቀው የቤኒሻንጉል አመራር ቀደም ብሎ እንዲፈርስ ለተደረገው የማንነትና ወሰን ኮሚሽን ቢያሳውቅም መፍትሔ አላገኘም።

ቤኒሻንጉል ጉሙዝን ከጋምቤላ የሚያዋስነው የማኦኮሞ ወረዳ አሁን ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ጥቅለላና ወረራ ተፈፅሞበታል።
ከዚህ ቀደም በነበረው የአገሪቱ ካርታ ኦሮሚያ ክልል ከሱዳን የሚዋሰንበት አካባቢ አልነበረም። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መግለጫም " ክልሉን በደቡብ የጋምቤላ ክልል ያዋስነዋል" ይል ነበር። አሁን ግን በሁሉም የካርታ መረጃዎች ላይ ኦሮሚያ ከሱዳን በስፋት እንዲዋሰን ሆኗል። [ see Maps ]

ይህን ለማድረግ መጀመሪያ በአካባቢው ታጣቂ በማስረግ ጥቃት መፈፀም ቀጥሎም የተጠቁ ሰዎች ሲሸሹ በስራና መሰል ጉዳይ ሰዎች ማስገባት የአፈፃፀም ቅደም ተከተል ነው።
በማኦ ኮሞ ወረዳ በእርሻና በእጣን ለቀማ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ የተፈፀመው ጥቃትና አፍኖ መሠወር ተግባር የሚታወቅ ነው። አሁን ደግሞ ብልጫ ቁጥጥር በተያዘበት አካባቢ የኦሮሚኛ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ እየሆነ ነው።

መተከል ውስጥ አባይን ተሻግሮ ያለው ወምበርማ ወረዳ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያሶ ወረዳ እንጅ ከኦሮሚያ ጋር ድንበር አልነበረውም::
በካርታው ላይ በቀስት የተመለከተው የያሶ ወረዳ ክፍል ከተጠቀለለ በኋላ ግን የኦሮሚያ ድንበር አባይ ድረስ ሆኗል።
በወቅቱ ሁኔታውን የፃፈው Getahun kassahun እንዲህ ብሎ ነበር።
" The Oromia Region has annexed parts of the Benshagnul-Gumuz (BG) areas adjacent to the Abay River by stealth and are now administered by so-called Oromia region. In the process, Oromia Police forcefully displaced Gumuz residents from their places. For example, I have confirmed about 730+ Gumuz people were forced to flee to the low-laying areas of Womberma Woreda of Gojjam (metekel) across Abay River. "

በነገራችን ላይ፤

ከአሶሳ ወደ ነቀምት አድርጎ አዲስአበባ መምጣት ከተዘጋ አራት አመቱ ነው!!

Beles Media

#የታሪክ_ምርኮኞች
#Oromo
#FascistRegime
#Ethiopia