Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ደብዳቤ ♡ ♡ ♡ 'ይድረስ ለሄዋኔ ' ኑሮ እንዴት ይዞሻል እንዴት ነሽ ሄዋኔ ይመስ | አንፍሮቹ Memes

የፍቅር ደብዳቤ



"ይድረስ ለሄዋኔ "
ኑሮ እንዴት ይዞሻል እንዴት ነሽ ሄዋኔ
ይመስገን ደህና ነኝ አታስቢ ለእኔ
..................ይልቅስ ሄዋኔ
ወጣትነት አልፎ እርጅና ሳይመጣ
ከቻልሽ ነይልኝ ካልሆነ እኔ ልምጣ
ግን ልትመጪ ከሆነ መንገድ ሳትጀምሪ
ማንነቴን ሰምተሽ ከቀረሽም ቅሪ
ወደ እኔ ለመምጣት ሀሳብ ስትሰንቂ
የሞላ ቪላ ቤት ፎቅ እንዳትጠብቂ
ጥሪትም የለኝም ወርሼ የማወርስሽ
ቤት ማጀቴ ባዶ ጮማ እንዳላጎርስሽ
ልብሴም ድሪቶ ነው ፊቴም ውበት የለው
ልቤም የእንባ ናዳ ክህደት ያቆሰለው
ግን ይህን ሁሉ አይተሽ መፀየፍ ሳይረታሽ
ንፁህ ፍቅሬ ገዝቶሽ ወደ እኔ ከመጣሽ
እ.ጠ.ብ.ቅ.ሻ.ለ.ሁ........በደስታ ፈንጥዤ በሰባራው ልቤ ንፁህ ፍቅርን ይዤ፡፡