Get Mystery Box with random crypto!

ጃቢር ባስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ ይላል፦ መልእክተኛው ﷺ ለዒድ ሶላት በሚወጡ ጊዜ (የሄዱበትን) መ | የዲነል ኢስላም ነኝ 🌙🌙

ጃቢር ባስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ ይላል፦
መልእክተኛው ﷺ ለዒድ ሶላት በሚወጡ ጊዜ (የሄዱበትን) መንገድ ይቀይሩ ነበር፡፡
[ቡኻሪይ ዘግበውታል]

መንገድ የመቀያየሩ ጥበብ ምንድ ነው?

ከኢድ ቀን ሱናዎች ውስጥ አንዱ መንገድ መቀያየር ነው። እንደሚታወቀው የአላህ መልእክተኛ ለኢድ ሶላት በወጡበት መንገድ ተመልሰው አይመጡም ነበር። ሲወጡ በሌላ ሲመለሱ በሌላ መንገድ ነበር። ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድ ነው? መልሱ ከኢብኑ ኡሰይሚን፦

ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ። በኢድ ሶላት መንገድ የምንቀይርበት ምክንያት፦
የአላህ መልእክተኛ ስለሰሩት እሳቸውን ለመከተል ነው።

ከፊል ኡለማዎች……
ምክንያቱ ለሙስሊም ባለሱቆችና በዛ አካባቢ ላሉ ሰዎች ይህንን የዲን መገለጫ ለማሳየት ነው ብለዋል።
ከፊል ኡለማዎች……
ምክንያቱ የውመል ቂያማ የሄድንበትና የተመለስንበት መንገድ እንዲመሰክርልን ነው ብለዋል።
ከፊል ኡለማዎች……
ምክንያቱ በሁለቱም መንገዶች ላይ ላሉ ምስኪኖችና ድሆች ሰደቃ ለማዳረስ ነው ብለዋል።

ምክንያቱና ጥበቡ ምንም ይሁን ምንም ውዱ ነብያችን ስለሰሩት የሳቸውን ፈለግ ህያው ለማድረግ ብለን ልንፈፅመው ይገባል።

https://t.me/analmuslimi