Get Mystery Box with random crypto!

ለይለተል ቀድር ክፍል 4 የመጨረሻው ክፍል ስለ ለይለተል ቀደር ማጠቃለያ ============== | Muhe tube .com

ለይለተል ቀድር
ክፍል 4 የመጨረሻው ክፍል
ስለ ለይለተል ቀደር ማጠቃለያ
====================
ለይለቱል ቀድር በረመዳን የመጨረሻ 10 ቀናቶች በ 21, 23, 25, 27 እና 29 መሆኑን ሃዲሶች ያረጋግጣሉ።
አንድ ሰው ሁሌም በትጋት አስካልተጠባበቀ ከነዚህ ቀናቶች በየትኛው ሊሆን እንደሚችል እርግጠኛ መሆን አይቻልም።

ከምልክቶቹ በሐዲስ በተደጋጋሚ የተረጋገጠው የዚያን እለት ማለዳ
ፀሐይ ስትወጣ ቀይ መልክ ያላትና ብርሃኗ ደብዛዛ የነሃስ መልክ
ይኖረዋል፣ አስኪረፍድ ድረስ የሚለው በተደጋጋሚ ተገልጿል፣
ለምሳሌ 27ኛው ለሊት ከሆነች የረመዳን 26 ፀሐይ ማለትነው።
አላህ ይቺን ታላቅ ለሊት ያድለን፡፡ የምንጠቀምባትም ያድርገን፡፡
አሚን!
ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ለሌሎችንም ተጠቃሚ ያድርጉ፡፡
ደርስ ማስቀመጫ:
ለይለተልቀድር ለሴቶች
==============
ለይለተል ቀድር ለሰጋጆች ብቻ አይደለችም የወር አበባ ደም ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶችም፣ የዚች ለሊት ትሩፋት አያልፋቸውም፡፡
||
ባይሆን እህተቶችየ በዚክርና መሰል ዒባዳዎች ልትበራቱ ይገባል፣ ይህን የሚጠቁም ሀሳብም ከመልካም ሰለፎቻችን ተገኝቷል፣ በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛት ጥሩ ነው፡፡

እንዳውም ሱፍያኑ ሠውሪ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
«በለሊቷ ከሶላት ይልቅ ዱዓእ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው» ይላሉ
#ወሰላሙ ዓለይኩም

===========
አላህ ሁላችንንም ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን