Get Mystery Box with random crypto!

የሶላ ደብዳቤ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ammelakuletters — የሶላ ደብዳቤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ammelakuletters — የሶላ ደብዳቤ
የሰርጥ አድራሻ: @ammelakuletters
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.69K
የሰርጥ መግለጫ

ጣዕመ #ግጥሞች
#ደብዳቤዎች
#ድርሰቶች
#ወጎች ፤ አነቃቂ ፅሁፎች ለዛ ባለው አቀራረብ አዋዝተን እናቀርባለን። ኑ ከጥበብ ማዕዳችን እንቋደስ ...
<< ነገ ላይ ቀድሞ የሰፈረ የለም ፤ ተስፋ እስካለ ግን መኖር መልካም ነው >> #መፃፍ_ይቀጥላል ( ሶላ እንደፃፈው )
ግጥም የኪነጥበባት ሁሉ የደም ጠብታ ነው
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-06 22:23:48 ከህይወት ማህደር
ክፍል ገፅ-በገፅ ከሶላ ( @sola1612 )
It was pall lately...
@Ammelakuletters
1.0K views[SOLA#21] ኦ ጥበበ ሶሎሞን አይቴ ሀሎኪ , 19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 21:43:32
በህሊና ቋጥኝ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በህሊና ቋጥኝ ዘልቀው ሲራመዱ
ዳገቱን ለመግፋት ቁልቁል ከወረዱ
ሰማይ ደመና አዝሎ ተስፋን ካረገዘ
በኑሮ አንሳንሳር ላይ ብዙ ከተጓዘ
ሰው የለኝም ብለህ ፍለጋ አትውጣ
ከጠበከው ቦታ ራስህን ስታጣ
በምኞት ጉዞ ላይ ዙሪያህን ብቃኝም
ከአንተነትህ በላይ ሰውም አታገኝም !

ከሶላ
1.1K views፲፪ 12, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 11:31:28
ዋ... !
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የማርያም ልብ ወዳጅ ተነሱ ለፀሎት
እጅግ ተጨነቀች ጣልያን ግራ ገባት
ጦርነቱ ሲዋጅ በአውድማ ስፍራ
ከእግዜር እንዲላክ ጊዮርጊስ ተጠራ
ከንጉሱ በፊት ሰማዕቱ ቀደመ
በጠላቷ ሬሳ <ኢትዮጵያን> አቆመ
የሀገሬም ክብሯ በነጮች ልብ ላይ ላይፋቅ ታተመ

ዳግማዊ ምንሊክ ፤ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ
ባልቻ አባ ነፍሶ ፤ ንግስት ጣይቱ
ጀግኖች አለቻቸው ክቧ ዐለሚቱ

ቀድሞም አስተውሎ... ለተመራመረ
<< ዋ ! ዋ ብያለሁ ዋ ! ብሎ የተናገረ
በምንሊክ አምሳል አምላኳ ነበረ >>

ከሶላ

እንኳን ለ126ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ

@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
@Ammelakuletters
1.2K views[SOLA#21] ኦ ጥበበ ሶሎሞን አይቴ ሀሎኪ , 08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 20:00:14 ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንኳን ለአብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ።መልካም ጾም ይሆንላችሁ ዘንድ እየተመኘው ይሄን "ኤፍራጥስ ወንዝ" ከተሰኘ የዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ መፅሐፍ ላይ የተቀነጨበ "አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?" የሚል ፅሑፍ እጋብዛችኋለሁ።
የበረከት ጾም ይሁንልን።
"አብይ ጾምንስ እንዴት ትጾማለህ?"
ሶፊ

@bestletters
883 views , 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 20:14:57 "ተከራያችን "

ክፍል፦፯

ደራሲ፦ሶፊ

" ምን እያልከኝ ነበር? " አለች ወደኔ እያየች

መድገም እየቀፈፈኝ እንደምንም ስሜቴን ታግዬ..."ምን ሆነሽ ነው የጠፋሽው? " አልኳት።
"ምንም አልሆንኩም...የጠፋሁበትንም ምክንያት ደጋግሜ ነግሬህ የለ ስራ ነው።" አለችና ዝም ስትል።
ከእንግዲህ ምንም መጠየቅ ትርፉ ድካም መስሎ ተሰማኝ፤አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም።ምንም ልትነግረኝ እንዳልፈለገች ሁኔታዋ ይናገራል።
"ጨከጨኩሽ አይደል?" አልኳት። መልስ አልሰጠቺኝም።
ከቢራዬ ጎንጨት ብዬ ጥያት የመሄጃ ሀሳብ አብሰለስል ጀመር።አንዳንድ ሰዎች መሄጃ ያጣን ይመስላቸዋል።ከእናቴ ጋር እያወራሁ ባመሽ በስንት ጠሀሙ፤የሚወዱኝን ጓደኞቼን ባገኝስ...ፊልም ባይ መፅሐፍ ባነብ ብዙ የምወዳቸውን ነገሮች ማድረግ እየቻልኩ።ከማይወደኝ ጋር ምን እሰራለሁ?
ይቀየራሉ ሰዎች ይቀየራሉ ማንም ባለበት አይረጋም።አፈቀርኩህ ያለችህ የወደደችህ መስሏት ይሆናል።ግራ ገብቷት ነው ግራ ያጋባችህ። ታዲያ ስትፈልገኝ ብቻ ነው የምትነግረኝ አልፈልግህም ተብሎስ አይነገርም? የምን ሽሽት ነው? እናቴም
"ስልኳ አሁንም አሁንም ይጠራል።"
ትቆያለሽ? እኔ ትቼው የመጣሁት ስራ አለ። (በልቤ እሱ ነው የሚያዋጣኝ አልኩ።) ትጠብቀኛለች። ትንሽ እቆያለሁ አለቺኝ። አስተናጋጁን ስጠራው ተወው ስወጣ እከፍላለሁ አለች። የአለማየሁ ገላጋይን "ሐሰተኛው~በእውነት ስም" የሚለውን መፅሐፍ ከጠረቤዛው ላይ አነሳሁና...ግርምት ባልተለየሁ ፈገግታ "ሰላም እደሪ አልኳት...መልእክት እየፃፈች የስልኳ እስክሪን ላይ እንዳፈጠጠች "ሰላም እደር አለቺኝ።" ደግሜ ላያት እደማልፈልግ ልቤን እያስጠነቀኩት። "ጎንበስ ብዬ ጉንጯን ሳም አደረኳት...ይሁዳስ እንደዛ አይደል ያደረገው? ለድሮ ማንነቷ አሳልፎ ሰጠዋት ?" ማን ነው ምንን አሳልፎ የሰጠው?
እኔ ምን አደረኩ ? እሷ ናት የተቀየረችብኝ።እያልኩ እራሴን ከወቀሳ ለማዳን መሯሯጥ ጀመርኩ።
እኔንማ ገድላኛለች የምወዳትን ትቼ ከእርሷ ጋር እንደሆንኩ ታውቃለች? የማልወዳቸውን ነገሮች ለእሷ ብዬ እንደማደርግ ታውቃለች? አታውቅም!
ለእሷ ብዬ ያደረኳቸው ያ ሁሉ ነገሮች ምንም ናቸው ማለት ነው። ባዶ መና ።
እሺ እንዴት ነው...እንደዛ ቀርባ አስለምዳኝ ብቻዬን የምችለው።
ብዙ የእኔ የምላቸው ነገሮች የእርሷ ስለሆኑ...እርሷን ማጣት ማለት ራሴን ማጣት መስሎ ተሰማኝና ራሴን ጨምድዶ ያዘኝ።

" ሰው የሰጡትን ቦታ ካላወቀ ምን ይደረጋል?"

ቤት ስገባ እናቴን ሰላም ብቻ ብያት ትንሽ ራሴን እዳመመኝና ማረፍ እንደምፈልግ ነግሬያት ወደ መኝታ ክፍሌ ገብቼ...ሳስብ አደርኩ።
በመጨረሻም የመጣልኝ ሀሳብ ራሴን በሳምንት ነገሮች መጥመድ ነው።ከስራ በተጨማሪ ኦንላይን አጫጭር ትምህርቶችን መማር ጀመርኩ።
ሳልደውል እሷም ሳትደውልልኝ...ሶስት ሳምንት ሞላ በዛው ሳምንት እኔ ክፍለ ሀገር ለስራ ጉዳይ ሄድኩ 1 ወር የሚያስቆይ ስለነበር ደስ እካለኝ ነው የሄድኩት።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ወሩን ሙሉ ያለምንም እረፍት አሳለፍኩ።ደውላልኝ አታውቅም እኔም አልደወልኩላትም። ልመለስ አካባቢ እናቴ ድንገት ስለእርሷ ጠየቀችኝ ስለ እርሷ አንስታብኝ ስለማታውቅ ግራ ተጋባው። "ደውላልህ ታውቃለች" ብላ ነበር የጠየቀቺኝ።
"አዎ እማ ተደዋውለን ነበር ምነው አዲስ ነገር አለ?" ብዬ ጠየኳት ልቤ ፈራ እያለ። "አይ እንዲያው ነው" አለቺኝ ድምጿ ላይ ግን የሆነ ነገር እንዳለ ተረዳው።"ምንድነው እማ? አመማት እንዴ ?" አልኩ ይበልጥ እየተጨነኩ። "ኧረ እንዲያውም" አለች። "በጣም ትቀራረቡ ስለነበር ዝም መባባላችሁ አሳስቦኝ ነው።" ለዚህ መልስ ስለሌለኝ ዝም አልኩ። ሌላ ሌላ ነገር ስናወጋ ቆይተን ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ።ያልተዋጠልኝ ነገር አለ። ሁለት ቀን አይደለች ስሄድ እደርስበታለሁ ብዬ ተፅናናሁ።
፨፨፨፨፨የመጀመሪያው መጨረሻ፨፨፨፨፨፨፨፨
ከሁለት ቀን በኋላ ወደቤት ለመሄድ በለሊት ነበር የተነሳሁት እንደተለመደው በመስኮት በኩል ተቀምጬ ወቅቱ የአብይ ፆም በመሆኑ "ሕማማት" የሚል ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ የፃፈውን መንፈሳዊ መፅሐፍ የአምላካችንን ሕማም በሚገርም ብዕር ስለተከተበ በፍፁም ተመስጦ በአይነ ህሊና ተጉዤ..."ይሁዳ ሊሸጠው ሲያስማማ እንዴት አምላክህን አሳልፈህ ትሰጣለህ? እርሱ እኮ መምህርህ ነው እያልኩ እሞግታለሁ። አይነ ስውራንን ሲያበራ፥የተመለከቱ አይኖችህ እንዴት የአምላክህን ጌትነት ጋረዱብህ? አንካሶችይሁዳን ሲዘሉ፤ሽባ ሲተረተር ድዊያን ሲድኑ፤እንዳልተመለከትክ እግሮችህ እንዴት አምላክህን ለመክሰስ ተራመዱ እያልኩ። ወቀስኩ። በይሁዳ ውስጥ ራሴንም ወቀስኩ።መፅሐፉ ክርስቶስን ወደ ይሁዳ ለፍርድ እያንገላቱ ሲወስዱት በህሊና ወሰደኝ ጲላጦስ ፊት እያንገላቱ አቆሙት እኔን ጌታ ሆይ እያሉ የእየሩሳሌም ወዛዝርት ሲያለቅሱ ሳይ አብሬያቸው ላለቅስ ዳዳኝ...ከጲላጦስ ሄሮድስ ክርስቶስን እያንገላቱ ተቀባበሉት~በሁሉ የሚፈርድ እርሱ ላይ ይፈርዱበት ዘንድ አንዳች በደል አጡበት።ያዳናቸው ከሰሱት፤38 አመታት በደዌ ዳኛ ተይዞ የነበረው መፃጉህ ከእዚህ እስራቱ ያዳነውን አምላክ፤መላእክት ከመለኮታዊ ግርማው የተነሳ ፊቱ ስለሚያስፈራቸው በክንፍ የሚሸፈኑለትን የሚፈት የሚንቀጠቀጡለን አምላክ በጥፊ መታው።በሁሉ ላይ ለሚፈርድ ለእርሱ ፍርድን አጓደሉበት።"

በተመስጦ እያነበብኩ ቆየሁ። ልደርስ አካባቢ እናቴ ደወለች። እየመጣሁ ነው እማ አልኳት።ከሁለት ቀን በፊት የነበረው ሁኔታ አሳስቦኝ መፅሐፉን ወደ ሻንጣዬ መልሼ መብሰልሰል ጀመርኩ። ከባሱ እንደወረድኩ ታክሲ ለመያዝ ስጣደፍ አንድ የስራ ባልደረባዬ ክላክስ አድርጎ መኪናውን በእኔ አቅጣጫ ሲያቆም ተመለከትኩ።ጎንበስ ብሎ በመስኮቱ አጮልቆ እያየ "ሶፊ ወደ ሰፈር ነህ?" አለኝ። አዎ አልኩት እኔም አንገቴን በመስኮቱ አጮልቄ። እኔም ወደዚያው ነኝ ና እንሂድ አለኝ። ከፍቼ ገባው።እያወራን።ቤት አካባቢ ስንደርስ አቆመ።እንዲገባ ብለምነውም እንቢ አለኝ።ተሰናብቼው ለወሬ እየጓጓው ወደ ቤቴ አመራው የጊቡውን በር አልፎ ወደ ውስጥ ስገባ ያየውትን ማመን አቃተኝ።

ይ~ቀ~ጥ~ላ~ል።


@bestletters
944 views , 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 21:49:59 ቆንጆ ነኝ
ከበላይ በቀለ ወያ በሶላ
...All of ma people's are beautiful...especially me .



@Ammelakuletters
1.8K views[SOLA#21] ኦ ጥበበ ሶሎሞን አይቴ ሀሎኪ , 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 11:18:12 የማርያም ንግስ እለት

ከኤፍሬም ስዮም

በሶፊ

@bestletters
1.0K views , 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-26 19:38:08 አታርቂያት ከቶ

ከሶላ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


የአንቺ እንዳልሆን ሲፈርድ ሆነሽ ቀናተኛ
ባለፈው ያየዋት፣
በጣም ነው ምታምረው የልብሽ ጓደኛ
እያልኩ ስነግርሽ፣
አንቺን ያልኩ ይመስል መስታወት ታያለሽ
ቁንጅና ሳይኖርሽ እንዳለሽ እያሰብሽ

ይልቁንስ ቀንተሽ፣
ቆንጆ ጓደኛሽን
እንዳልወዳት ፈርተሽ አታርቂያት ከቶ
ገና ድሮ ድሮ
ስታስተዋውቂኝ ውበቷ ገዝቶኛል ልቤን አሸፍቶ



አታርቂያት ...
ከቶ አታርቂያት አንቺ ግን እንዳሻሽ
ትርጉሙ ሌላ ነው ነይ ብዬ ስቀጥርሽ

ትርጉሙ ይሄ ነው
በርግጥ
እንቺን እንኳን ቢሆን መጀመሪያ ማውቀው
እውነቱን ልንገርሽ
የምወደው እሷን ያልኩት ግን አንቺን ነው!

ትርጉሙ ይሄው ነው ሌላ እንዳይመስልሽ
ይልቅ ከወደድሽኝ
እሷን ቅጠሪልኝ ነይ ብዬ ስቀጥርሽ


ግና ግና ቀንተሽ፣
ቆንጆ ጓደኛሽን
እንዳልወዳት ፈርተሽ አታርቂያት ከቶ
ያኔ ድሮ ድሮ
ስታስተዋውቂኝ ውበቷ ገዝቶኛል ልቤን አሸፍቶ



@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
2.3K views[SOLA#21] ኦ ጥበበ ሶሎሞን አይቴ ሀሎኪ , 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-19 21:38:07 እመነኝ ስትይኝ

ከሶላ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ድቡልቡል አይኖችሽ ከአይኔ ገጥመውኝ
እንደጠራ ኩሬ በጥዑም ልሳንሽ እመነኝ ስትይኝ
እወድሽ ጀመረ
ፍቅር ማለት ማመን ለልቤው እያልኩኝ



በሌላኛው እለት ሆነን በቀን ቅዱስ
በጥቅምቱ ንፋስ ተውበሽ በቀሚስ
ሳይሽ ውበትሽ አፍዞኝ
ከተክለቁመናሽ ትኩስ ፍቅር ይዞኝ
አንቺም የኔው ንዝረት ተሰምቶሽ መሰለኝ
በድንገት ስበሽኝ ከንፈሬን ስትሚኝ
ጠበበኝ ምድሪቷ
የወደድኳት አለም ኧረ የትአባቷ!

ግና ምን ይበጃል
ይሄ ሁሉ ስሜት ለአንቺ ቀልድ ኖሯል
መውደዴን ስነግርሽ ጠልተሽኝ ሞተሻል


ዳሩም አልጠፋኝም ሀገር ሙሉ ያውቃል
የሚያምንሽ ስታጪ እመነኝ ብለሻል
አላምንም እንዳልል ከንፈሬን ስመሻል
ዳሩም ግን አትሚኝ!
ውስጥሽ ቢነግርሽም ወደሽኝ እንዳጣሽ
እውነቱን ታውቂያለሽ
እንኳንስ ለልቤ ለህልሜም ሩቅ ነሽ


እስኪ ልጠይቅሽ ለራስሽ መልሽው
የሄደው ልብሽን በምን አስማቴ ነው ቀርቤ ምጎዳው?

እኔ አላውቅም ...


@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
2.7K views[SOLA#21] ኦ ጥበበ ሶሎሞን አይቴ ሀሎኪ , 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-14 21:15:14 ሰው ከአንድ እናት የተወለደው ወንድም ወይም እህቱን ምንም ቢበድሉ እና ቢከፉ የአንድ እናት ልጆች ነን ብሎ ይቅርታ ያደርጋል ፤ ከመውደድም አይሰንፍም! ከአንድ እናት ላልተወለዱት የፍጥረታት ሁሉ አባት እና እናት ከሆነው ጌታ የተገኙት እና የአንድ አምላክ ልጆች የሆኑት ወንድም ወይም እህቱ ግን ቢበድሉት ይጠላቸዋል ቢያስከፉትም ለመጥላት ከቶ አይዘገይም!

ከሶላ



@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
@Kehiwotmahder
2.2K views[SOLA#21] ኦ ጥበበ ሶሎሞን አይቴ ሀሎኪ , 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ