Get Mystery Box with random crypto!

ይሰምራል ሃሳቡ ይሽራል ህመሙ ያያቸው እንደሆን ነቢዩን በህልሙ ሲባል የሰማው ሰው ነቢዩን የማየት | የአስተሳሰብ ለውጥ✊

ይሰምራል ሃሳቡ ይሽራል ህመሙ
ያያቸው እንደሆን ነቢዩን በህልሙ
ሲባል የሰማው ሰው ነቢዩን የማየት ጉጉቱ ቢወርሰው ሼኽየው ጋር መጣ ምክርን ፈልጎ

ሃዘኔ ሚጠፋው ውጥኔም ሚሰምር
በሁለቱም ሃገር ተሽቆጥቁጬ ማምር
የሚፈካው ልቤ የሚሽር ህመሜ
ሳያቸው ነውና ነቢዩን በህልሜ
ይኼው በጠዋቱ መጣሁ አሰግስጌ
የልቤ እንዲሞላ ምክሮትን ፈልጌ

ሸኽየው ጠቢቡ ጥቂት አሰላስለው
ለርሱ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ደግሰው
ማለፊያ ምክርን ነገሩት ለዚህ ሰው

ከሼኹ አንደበት

ሦስት ቀን በሙሉ ውሃ ሳትጠጣ
ከቆየህ በኃላ ወደኔ እንድትመጣ
የሚል ትእዛዝ ወጣ

ነቢዩን ለማየት የከጀለው ያ ሰው
ከባዱን ጥም ፀንቶ እየታገሰው
ሁለተኛውን ቀን በጥማት ደረሰው
የመጨረሻይቱ ሶስተኛ ቀን ማታ የተኛው ይኸ ሰው እየተሰቃየ አንድ ህልምን አየ

ሲዋኝ ባህር ሰምጦ ሲራጭም ሲጠጣ
በውሃ ተከቦ ተውሃ እየገባ ተውሃ ሲወጣ
ታዲያ ሌት ነጋና ሼኽየው ጋር መጣ

ይኸው ሶስት ቀን ሙሉ ጥሙን ተቋቁሜ ከውሃ ሸሸሁም
ስቃዩን ታግሼ ጥማቴን ሸኘሁም
ታዲያ ግን ነቢየን በህልሜ አላየሁም
ሲል ቃሉን ሰበቀ

ታዲያ ምንድን አየህ ተብሎም ተጠየቀ
በውኃ ታጅቤ ስራጨው ስጠጣው ስገባው ስወጣው
ጥማቴን ስወጣው ሌቱን አደርኩና ወዳንቱ ጋር መጣው

ሼኹም ከተል አርገው አየህ አንተ ልጄ
ሶስት ቀኑን ሙሉ እጅግ የናፈቅከው
ስታስበው ውለህ ስታስብ ያደርከው
ውኃን ነበርና ልብህ ያሳረፍከው
ያው እንደናፈቅከው በህልምህ ጠጣኻው ጠገብከው
ታዲያ አንተ ልጄ ነቢም እንደ ውኃው ቢጠሙህ ቢናፍቁህ ብታስታውሳቸው
ቀን ሌቱን ተጠምተህ ጠንተህ ብትናፍቃቸው
እሳቸውን ሊያስብ ተከፍቶ ያንተ በር
ዘይንዬን ተጠምቶ ውስጥህ ቢንበረበር
እንደ ውኃው ሁላ ነቢዩንም በህልም ባየሃቸው ነበር
አየህ አንተ ልጄ ከሻትክ ልታያቸው የእውነት አፍቅራቸው
ናፍቅ አስታውሳቸው ተራብ ተጠማቸው
በማለት ተቋጨ ሸኽየው ምክራቸው

صلوات ربي وسلامه عليه
@hayuzizaa