Get Mystery Box with random crypto!

#ዳዊት_ፅጌ #ቃል_ኪዳን ለውዲቷ ለእናት ኢትዮጵያ ታጥቄ ጠንክሬ የምሠዋላት ነኝ እኔስ ለ | Allen Online shopping

#ዳዊት_ፅጌ #ቃል_ኪዳን

ለውዲቷ ለእናት ኢትዮጵያ ታጥቄ ጠንክሬ
የምሠዋላት ነኝ እኔስ ለሀገሬ
ጠላቶቿን እቃወማለሁ አጥብቄ በብርቱ
ስለሀገር ፍቅር ገባኝ በእውነቱ
ቀርጿት ታሪክሽን ሲመሰክር ድንጋይ
ማንነቴን ክጄ ላንቺ አንሼ ብታይ
ከእድሜ ከህይወቴ ሰስቼ ብነሳሽ
ይራቀኝ ሰውነት ልርገፍ እንደጤዛሽ
ታሪክ ያድርገኝ ተወቃሽ

ለውዲቷ ለእናት ኢትዮጵያ ታጥቄ ጠንክሬ
የምሰዋላት ነኝ እኔስ ለሀገሬ

ሀገሬ

ስሜን ፍቅር አይጥራው ከክብርሽ አዳራሽ
ቀድሞ ካላረገኝ የከፋሽ ቀን ደራሽ
ነግሰሽ በአደባባይ ኑሪ በፍቅር እድሜ
ትንፋሼ ነውና ያንቺ ልምላሜ
አ...ሀ..ኢትዮ..ጵያ

አባት መመኪያዬ እንስፍስፏ እናቴ
ጥላ ወንድም ጋሼ እኔን ባይ እህቴ
በምድርሽ አኑረሽ ሁሉንም ሰጥተሺኝ
እንዴት ላንቺ አልወድቅም በደም ተዛምደሺኝ

ስሜን ፍቅር አይጥራው ከክብርሽ አዳራሽ
ቀድሞ ካላረገኝ የከፋሽ ቀን ደራሽ
ነግሰሽ በአደባባይ ኑሪ በፍቅር እድሜ
ትንፋሼ ነውና ያንቺ ልምላሜ
አ...ሀ ኢትዮ...ጵያ።። (x 2) "

ስሜን ፍቅር አይጥራው ከክብርሽ አዳራሽ
ቀድሞ ካላረገኝ የከፋሽ ቀን ደራሽ
ነግሰሽ በአደባባይ ኑሪ በፍቅር እድሜ
ትንፋሼ ነውና ያንቺ ልምላሜ
አ...ሀ ኢትዮ...ጵያ።። (x 2) "