ቀለም ያዘ ልቤ ! ከእምነት - ተለይቶ ከፍቅር - ተፋቶ ሰው ፈርቶ - ሰው ጠልቶ ቀለም ላይቀበል- ምሎ ተገዝቶ የተሸሸገውን የተደበቀውን አገኘሽውና የልቤ ስፍራውን ፣ አንኳኩተሽ - ብትከፍችው ከፍተሽ - ብታጸጂው አጽድተሽ - ብታጥኚው አጥነሽ - ብታጠምቂው የተሸሸገበት - ምሽጉን ናደና ፊደል አልቀበል - ማለቱ ቀረና ለእውቀት ተሸንፎ - ልቤ እጁን ሰጠና፣... በአንቺው ፍቅር ጠርቶ በአንቺው እውነት ጸድቶ በእምነትሽ ተረቶ "መውደድ" ተፃፈበት፦ ቀለም ያዘ ልቤ ፤ ልብሽን አግኝቶ። ገጣሚ ጌትነት እንየው ከዕውቀትን ፍለጋ የግጥም መድብል የተወሰደ @amharic_poems 6.9K viewsedited 17:30