Get Mystery Box with random crypto!

የሁለት ጣዕረሞት ወግ፧፧፧ ፨ ፨ ፨ 1 ፡ ሄይ ! 2 ፡ እሂ ! 1 ፡ እንዴት ነበር የሞ | ብታምኑትም ባታምኑትም በየቀኑ

የሁለት ጣዕረሞት ወግ፧፧፧



1 ፡ ሄይ !

2 ፡ እሂ !

1 ፡ እንዴት ነበር የሞትከው?

2 ፡ በስህተት ፍሪጅ ውስጥ ገብቼ ፣ ተዘግቶብኝ ነው የሞትኩት። በመጀመርያ 'የቀዘቀዘኝ መጣ ፣ ቀጥሎ በረዶ ሆንኩኝ ፣ ከዚያም በቃ!! መተንፈስ ተስኖኝ ፡ አየር ማስወጣት ና ማስገባት ስያቅተኝ ፤ ታፍኜ ሞትኩ።

1 ፡ ዋው!!...ያንተው በጣም ያሳዝናል።

2 ፡ አወ። ያንተስ እንዴት ነበር?

1 ፡ እኔ!! በልብ ድካም ነው የሞትኩት።

2 ፡ ማለት...እንዴት? ምን ተፈጠረ?

1 ፡ ምስቴ አማገጠችብኝ!!! የዛን ቀን ወደቤት ስመለስ ፣ ቤት ውስጥ የወንድ ጫማ አየሁኝ። በፍጥነት ወደአልጋ ክፍል ሮጥኩ ፤ እሷ ብቻ ነበርች ፤ 'ርቃኗን።
የሆነ ሰው እኔ ቤት እንደገባ ጎረቤተም ስለነገረኝ ፣ ሰውየው ቤት ውስጥ እንደተደበቀ አልተጠራጠርኩም ፤ እሷም ደንግጣ ና ፈርታ ነበር።

2 ፡ እ....ሺ!!!!

1 ፡ ከዚያማ! መፈለግ ጀመርኳ!! ሙሉ ቤቱን ማተራመስ ተያያዝኩ። አንዴ የልጆች ክፍል ፣ አንዴ ኩሽና ፣ ባኞ ቤት ፣ ሽንት ቤት መመገብያ ክፍል ፣ ቁምሳጥን 'ያልኩ ብሯሯጥም ላገኘው አልቻልኩም። በሩጫው ምክንያት እዛው ልብድካም ይዞኝ ፀጥ አልኩ።

2 ፡ ደደብ!! ፍሪጅ ውስጥ ቼክ አርገህ ብሆን ኖሮ'ኮ 'ሄነ ሁለታችንም በህይወት እንቆይ ነበር!!

Join us

@amharic_book_pdf_metsahaft