Get Mystery Box with random crypto!

የዘር አቆጣጠር ለማታውቁ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ #ልጅ ፣ #አባት ፣ #አያት ፣ #ቅድመ-አያት ፣ | ብታምኑትም ባታምኑትም በየቀኑ

የዘር አቆጣጠር ለማታውቁ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ

#ልጅ ፣ #አባት ፣ #አያት ፣ #ቅድመ-አያት ፣ #ቅም-አያት ፣ #ቅማንት፣ #ሽማት ፣#ምንዥላት ፣ #አንጅላት፣ #ፍናጅ፣ #ቅናጅ ፣#አስልጥ ፣ #አምስጥ ፣ #ማንትቤ፣ #ደርባቴ ፣፣ ይባላሉ ::

ምናልባት በጊዜው አስገዳጅነት መጠቀም ካለብኝ ብዬ በግጥም መልክ ለመጻፍ
ሞክሬ ፣ ስኩ ፣ የሳተውን ግጥሜን ጀባ ልበላችሁ ::


የኔ ትውልድ የዘር ቆጠራ
አያልፍም ነበር ካያቶቹ ተራ
የዛሬዎቹ ብልህ ናቸው
ከአዳም መለስ መቅረባቸው
ቅድመ አያት ፣ ቅም አያት
ቅማንት ፣ ሽማት ፣ አንጅላት
አናውቅም ነበር የተሃድሶ ጥራት
ፍናጅ ፣ቅናጅ፣ አስልጥ ፣ አምስጥ
ድሮ አልነበረም ወደ ጆሮ የሚሰምጥ
ማንትቤ ፣ ደርባቴ ብሎ ነገር
አናውቅም ነበር ዘልቆ መካረር
ከአዳም ወዲህ መጀመሩ
ምን ሊፈይድ ለነገሩ
ቦታ አስፍቶ በትንሣዔ
ካልጠፋ ቀን ለጉባዔ
ሁሉም ሕልም ከጀርባዬ
ከሰላምታ ጋር

ብስራት

@amharic_fun_bitamnutim_fact