ስለ ግእዝ ፊደላት የግእዝ ፊደላት ከሌሎች ቋንቋዎች ፊደል የሚለየው ፊደላቱ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ትርጉም ስላላቸው ነው። ለምሳሌ፦ ሀ - ማለት የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው፡፡ - ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እም ቅድመ ዓለም። ለ - ማለት የእኛን ሥጋ ለበሰ። - ብሂል ለብሰ ሥጋ ዚአነ። ሐ - ማለት ስለእኛ ታሞ ሞተ። - ብሂል ሐመ ወሞተ በእንቲአነ። መ - ማለት የእግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው፡፡ - ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር። ሠ - ማለት ከድንግል በሥጋ ተወለደ(ተገለጠ) - ብሂል ሠረቀ በሥጋ እምድንግል፡፡ ረ - ማለት በጥበቡ ፤ ሰማይና ምድር ረጋ። - ብሂል ረግዓ ሰማይ ወምድር፡፡ ሰ - ማለት እንደእኛ ሰው ሆነ። - ብሂል ሰብአ ኮነ ከማነ። ቀ - ማለት በመጀመሪያ ቃል ነበረ። - ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ። በ - ማለት ለዓለም ሁሉ ቤዛነት በትሕትናው ወረደ፡፡ - ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኩሉ ዓለም። ተ - ማለት ፍፁም ሰው ሆነ። - ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ። ኀ - ማለት ራሱን (ባህሪውን )ሰወረ (ሸሸገ) - ብሂል ኀብአ ርእሶ። ነ - ማለት ደዌያችንን ያዘል ሕማማችንንም ተሸከመልን። - ብሂል ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ። አ - ማለት እግዚአብሔርን ፈፅሞ አመሰግነዋለሁ። - ብሂል አአኲቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር። ከ - ማለት እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው፡፡ - ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር። ወ - ማለት ከሰማያት ወረደ። - ብሂል ወረደ እምሰማያት። ዐ - ማለት እግዚአብሔር ታላቅ ነው። - ብሂል ዐቢይ እግዚአብሔር። ዘ - ማለት እግዚአብሔር ሁሉን የሚይዝ (የሚገዛ ነው)። - ብሂል ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር። የ - ማለት የእግዚአብሔር ቀኝ ኀይልን አደረገች። - ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ። ደ - ማለት መለኮቱን ከሥጋችን ጋር አንድ አደረገ። - ብሂል ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ፡፡ ገ - ማለት ምድርና ሰማያትን የፈጠረ ነው፡፡ - ብሂል ገባሬ ሰማያት ወምድር። ጠ - ማለት እግዚአብሔር ጠቢብ ነው፡፡ - ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር። ጰ - ማለት ጰራቅሊጦስ የእውነት መንፈስ ነው፡፡ - ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፡፡ ጸ - ማለት እግዚአብሔር ጸጋና እውነት ነው። - ብሂል ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር፡፡ ፀ - ማለት እግዚአብሔር የእውነት ፀሐይ ነው። - ብሂል ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር፡፡ ፈ - ማለት በጥበቡ ዓለምን ፈጠረ። - ብሂል ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ። ፐ - ማለት የእግዚአብሔር ስሙ ፓፓኤል ነው፡፡ - ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለእግዚአብሔር። ይቀጥላል... #ፊደሎች https://t.me/Amdehaymanotzeortodoxtewahdo 327 views𝑛𝑒𝑡𝑠𝑎𝑛𝑒𝑡 𝑙𝑒𝑚𝑚𝑎, 05:09